lørdag 2. februar 2013


ወያኔ ኢህአዴግ በመጪው ሚያዚያ ወር አካሂዳለሁ ላለው የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ ከተሞች እና የክልል ምክር ቤቶች እና የወረዳዎች ምርጫ ተብየ ድራማ በርካታ ሰዎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ቤት ለቤት ቅስቀሳ እያካሄደ ሲሆን ለሚቀሰቅሱለት ካድሬዎቹ የቀን ውሎ አበል እና የስብሰባዎችና ድግሶች የሚያወጣው ገንዘብ አስደንጋጭ እየሆነ መምጣቱን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ በላከልን ዘገባ አመለከተ።
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ወያኔ ኢሃዴግ ቤት ለቤት እንዲቀሰቅሱ መልምሎ የላካቸው በርካታ ሰዎች በዝቅተኛ ገቢ ላይ የሚገኙ እናቶችን፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን ከሴቶች ሊግ፣ ከወጣቶች ሊጎች እና ፎረምና ወጣት ማህበራት እና ዝቅተኛ የየአካባቢው ካድሬዎቹን ሲሆን በቀን ከሃምሳ ብር እስከ 250 እንደ ቀኑ ውጤታቸውና ደረጃቸው እየከፈለ መሆኑ ታውቁአል።
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን በድህነት አለንጋ መገረፍ እንደ መጠቀሚያ መሳሪያ እየተገለገለበት የሚገኘው ጨክላኝ አገዛዝ ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶችን የአንበሳ አቡቶቡስ ቴኬት ቆራጭነት፣ በየሴክተርና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በተላላኪነት፣ በአትክልተኝነት፣ በጥበቃ ሠራተኝነት ለመቅጠር ቃል በመግባትና የድጋፍ ደብዳቤ በመስጠት እንዲሁም  ነቃ ያሉ ወጣቶችን ደግሞ ተደራጅተው በሚፈልጉት የሥራ መስክ እንዲሰማሩ የገንዘብ ብድርና የመሥሪያ ቦታ ለማመቻቸት ቃል እንደገባላቸው ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቱአል።  እንዲህም ሆኖ የወያኔው ኢሃዴህግ ያስቀመጠው የምርጫ ኮታ ባለመሙላቱ በልዩ ልዩ ምክንያት ላልተመዘገቡ ሰዎች በሚል ሽፋን ምርጫ ቦርድ ለተወሰኑ ተጨማሪ ቀናት ምዝገባውን እንዲቀጥል በውስጥ ደብዳቤ ማዘዙን ዘጋቢያችን አክሎ ገልጹአል።
ዘጋቢያችን ይወያኔ ኢሃዴግ የውስጥ አዋቂ ምንጭ አነጋግሮ ባገኘው ምላሽ ከፋፋዩ የወያኔ አገዛዝ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስትራቴጂው ሳይወዱ በግድ ያደራጀው፣ በምርጫ ወቅት የምርጫ ካርድ ያወጡ ሰዎችን እንዴት አድርጎ የምርጫ ካርዳቸውን ወደ እራሱ የድምጽ ኮሮጆ የሚያስገባበትን የተጠና ዘዬ ለመተግበር ዝግጅቱን በማጠናቀቁ ነው ማለታቸውን ገልጹአል።
ይህ በንዲህ እዳለ ወያኔ ኢህአዴግ ሊያካሂድ ባሰበው የአካባቢ ምርጫ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳይሳተፍ 39ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ ማቅረባቸውን ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቱአል። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ፓርቲዎቹ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀረቡት ”ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ  ባወጡት መግለጫ ነው። እነኝሁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መላው የአገራችን ህዝብም የምርጫው አካል በመሆን ኢዲሞክራሲያዊና ኢህገ-መንግስታዊ ለሆነ አካሄድ ይሁኝታ እንዳይሰጥ ጥሪ እናቀርባለን በማለትም ህዝቡ በምርጫው እንዳይሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።  ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ማጠቃለያ በተባበረና በተቀናጀ ህዝባዊና ሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት፤እንዲሁም ከድርጅታችን ይልቅ ለአገራዊ የህዝብ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት በትብብር ለመሥራት ቃላችንን እናድሳለን ማለታቸውን ዘጋቢያችን አክሎ ገልጹአል።
  • facebook
  • google_buzz
  • twitter
  • rss
  • print
  • bookmark
  • email

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar