mandag 4. februar 2013

ኦህዴድ ለሶስት ቡድኖች ተከፈለ

የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በአብዛኛው የኦሮሚያ ዞኖች በተለይም በምስራቅ ኦሮሚያና በአርሲ ዞኖች የሚገኙ የድርጅቱ አባላት ለ3 ተከፍለው እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው።
የክፍፍሉ መንስኤዎች በድርጅቱ እምነት ማጣት፣ ሙስናና የግል ጥቅምን ማሳደድ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
አመራሮቹ እርስ በርስ እየተባሉ ይገኛሉ ያሉት ምንጮች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የድርጅቱ ህልውና ሊያከትም እንደሚችል ጠቁመዋል።
በዞን ደረጃ የሚታየው መከፋፋል ዋናዎቹን የኦህዴድ አመራሮችን መጨመሩንም ለማወቅ ተችሎአል። ሰሞኑን በዝግ በከፍተኛ አመራሮች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ግምገማ የዚህ አካል መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ድርጅቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ መዳከሙን የገለጡት ምንጮች ክፍፍሉ እስከ ወረዳ መዝለቁንም ጠቁመዋል።
ጥር ዘጠኝ ቀን የነበረው የፓርላማ ውሎ ሁለት መልክ የነበረው ነው፡፡ አንደኛው ያለወትሮ ፓርላማው ከመንግስት የቀረበለትን ሞሽን በጥቂት ድምፆችም ቢሆን የተቃውሞ ድምፅ እና ድምፀ-ተአቅቦ ያስመዘገበበት ነበር፡፡ ጥሩ ፍንጭ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በተከበሩ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ በኩል የተለየ ሃሳብ ለምን ሰማው በሚል በእኔ እና በወከልኩት ድርጅት ላይ ፀረ-ህዝብ የሚል ፍረጃ ለማድረግ በፍፁም ያልሳሱበት ነበር፡፡ በምክር ቤት ውስጥ ያቀረብኩትን ሃሳብ እንደወረደ ለአንባቢ አቀርበዋለሁ፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar