mandag 19. august 2013

ሪፖርተር ሶማሊያ ስለተከሰከሱት አውሮፕላኖች ሲዘግብ ስለመንሰኤው አለመጠየቁ – በክፍሉ ሁሴ

የአቶ አማረ አረጋዊ ጋዜጣ ብቻ እንዲዘግበው በተፈቀደው መሰረት በቀደም ሶማሊያ ላይ ተከስክሶ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አንቶኖቭ 12 የተባለው ሩሲያ ሰራሽ አውሮፕላን አደጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው አደጋ መሆኑን እ.ኤ አ በኦገስት 11,2013 ባሰፈረው ዘገባው ይነግረናል።ሌሎች ይህን ቢዘግቡት ምስጢር በማባከን የ”ብሔራዊ ደህንነትን”ሆነ ብሎ አደጋ ላይ በመጣል ወይም በዚያ በፈረደበት የሽብርተኛ ፍርደ ገምድል ሕግ ዘብጢያ ይወርዱ ነበር።ያም ሆነ ይህ ሪፖርተር በአንቶኖቩ ላይ ይህ አደጋ ከመከሰቱ ጥቂት ቀናት በፊት ሌላ ኤል 100 የተባለ የ”አየር ሃይሉ”አውሮፕላን እዚያው ሶማሊያ ተከስክሶ መሰባበሩንና አብራሪዎቹም የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሆኑ፤የዚያ አውሮፕላን ዳፋም ስብርባሪውን ሊያመጣ ለሄደው ለዚህኛው አንቶኖቭ እንደተረፈው ዘግቧል።በነፃ ጋዜጣ ስም የቁርጥ ቀን የወያኔ አፈ ቀላጤነቱን የማይዘነጋው ሪፖርተር የ”አየር ሃይሉ”አውሮፕላኖች እንደደርግ ጊዜ ሳይተኮስባቸውና ቦምብ ሳይቀበርባቸው ባገር ጤና በየሳምንቱ በየሄዱበት ባፍጢማቸው ለምን እንደሚደፉ አጠያይቆ ሊዘግብ አልሞከረም።እሱ ባይዘግብ እኛ እንጠያይቅና የመጠይቃችንን ውጤት እንመልከተዋ! Read story in PDF…

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar