torsdag 25. juli 2013

ሰሞንኛው ደሴን በጨረፍታ

ከአቶ ብስራት ወ/ሚካኤል
ከአዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር በስተሰሜን በምትገኘው ታሪካዊቷ የወሎ ክፍለ ሀገር(የአሁኑ ደቡብ ወሎ ዞን)ከተማ ደሴ ልክ እንደ አዲስ አበባ የክረምቱ ዝናብና ብርድ ቢያስቸግርም የነዋሪዎቿ እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የምን አዲስ አበባ ያሰኛል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ሲዘፈንላት የኖረው የነዋሪዎቿ ውበት፣ ተግባቢነትና በሙስልም ክርስቲያኑ በፍቅር ተግባቦት የሚያስቀና ኑሮ እንጉርጎሯዊ አድናቆት ይሰማል፡፡ ይህ ደግሞ በተግባርም እውነት መሆኑንን ስመለከት አቦ ደሴዎች ትመቻላችሁ! ከማለት ውጭ ምን ይባላል? በተለይ የሙስሊሙ የረመዳን ቅዱስ ወር ፆም መጀመር ደግሞ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንቅስቃሴዎች ፀጥ ረጭ እንዲሉ ያስቻለ ይመስላል፡፡ የኦርቶዶክሱም ቢሆን ፆመ ሐዋርያት(የሰኔ ፆም መያዝ ሳይረሳ ማለት ነው፡፡)
በርግጥ ደሴ የመጣሁበት ዋናው ምክንያት አንድነት ፓርቲ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ለጠራው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴና የአስተዳዳሪዎቹ በተለይ ከከንቲባው እስከ ካቢኔ አባላትና የፀጥታ ኃይሎች ያለውን ቀና አመለካከት ስመለከት አዲስ አበቤ አስተዳዳሪዎች ምን ይማሩ ይሆን ያሰኛል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮችና አባላት ለሰላማዊ ሰልፉ ሽር ጉድ ይላሉ፤ በተለይ ፖስተር በመለጠፍና ከ 50 ሺህ በላይ በራሪ ወረቀቶችን ከአዲስ አበባ ከመጡ የፓርቲው አመራር ልኡካን ጋር እየተንቀሳቀሱ ሲያድሉ የከተማው ነዋሪ ወጣቶች(አባላት እንዳልሆኑ ተነግሮኛል) በራሪ ወረቀቶችን ከፓርቲው አባላትና አመራሮች ጋር በጋራ ሲበትኑ መመልከት ችያለሁ፡፡

በአሁን ወቅትም ለሐምሌ 7 ቀኑ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑንና ሁሉም የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆኑ ተነግሮኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የደሴ ከተማ ሸዋበር መስጅድ አሰጋጅ(ኢማም) ሼህ ኑሩ ይማም ሰኔ 27 ቀን 2005ዓ.ም. ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሉ ገዳዩን ለማደን እየተሯሯጠ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ይህ ደግሞ ለአንድነት ፓርቲ የፀጥታ ችግር እንደማያጋጥመው ተናግሮ በሼሁ መሞት ፓርቲው ማዘኑንና ገዳዮቹም ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው እንደሚያምን፣ ድርጊቱንም አጥብቆ እንደሚያወግዘው እንዲሁም ከአዲስ አበባ የመጡ ልዑካንም ሼሁ ቤት ልቅሶ በመድረስ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናት እንደሚመኙ መግለፃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ደሴ ደስ የሚል ፀባይ ያላቸው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ደስ የሚል በተራራ የተከበበች ከተማ በመሆኗ መልከዓምድሯና ከኮንቦልቻ ደሴ ያለው 25 ኪሎ ሜትር አስገራሚው የተራራ ላይ ቆረጣ የአስፓልት መንገድም ያስገርማል፣ይሄ መንገድ ከእድሳት ውጭ ከመቶ አመታት በላይ እንደሆነውም ተነግሮኛል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከንቲባና የፀጥታ ኃላፊዎች ለጋዜጠና ተጠየቁትን ለመመለስ እንደ አዲስ አበባ ቢሮክራሲ ባለማብዛታቸው የገባቸው ናቸው ያስብላል፡፡ ህዝቡም ለሰላማዊ ሰልፉ መዘጋጀቱን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
ለማንኛውም ደሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ባያትም ነዋሪዎቿ እንደሚመቹ ሁሉ ከተማዋም ትመቻለች፤ ዝናቡና ብርዱ ግን ከአዲስ አበባ የተከተለኝ መስሎኛል፡፡ሰሞንኛው ደሴን በጨረፍታ

ለማንኛውም ደሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ባያትም ነዋሪዎቿ እንደሚመቹ ሁሉ ከተማዋም ትመቻለች፤ ዝናቡና ብርዱ ግን ከአዲስ አበባ የተከተለኝ መስሎኛል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar