mandag 29. april 2013

ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪ በዘመነ ሰላቶ


….ምንይልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ግዜ አበሻ…….
 ……….በግዜው ይህንና ይህንን የመሳሰሉ ልዩ መልዕክት ያላቸው የግጥም ቋጠሮዎች የተደረደሩት ወራሪው  የኢጣልያ ሰራዊት ከነበረው የቅኝ ግዛት ፍላጎት መስፋፋት በመነሳት በኢትዮጵያ ላይ አካሂዶት በነበረው ወረራ  የደረሰበትን ሽንፈት ለመግለፅ፤ በዘመኑ የነበሩ ነገስታትና ሰራዊታቸው ያሳዩትን ጀግንነት ለማወደስ፤ በአጠቃላይ  ባርነትን ፍፁም ሊቀበሉ ያልቻሉ ጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ዛሬ ላይ ሆነን የነፃነትን አየር ለመተንፈስ  መብቃታችንን ለመመስከር ነው። በእርግጥ ከዚያ ቀደም ይሁን ከዛ በሗላ የነበሩ አባቶቻችንም ቢሆኑ በየወቅቱ ግዜ  እየጠበቀ በተለያየ አቅጣጫ የመጣብንን ባእዳን ወራሪ በተደጋጋሚ አሳፍረው መመለሳቸው ባይካድም፤ በአድዋ ጦርነት  ግዜ የተገኘው ውጤት ግን፤ ለኛ ኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጥቁር ህዝቦች እንደ ነፃነት ተምሳሌት ሆኖ  ይጠቀሳል። በዚህም ድል መላው የጥቁር ህዝቦች እጅግ ከፍ ያለ ኩራት ሲሰማቸው ይኖራል። ከዚህ በተፃራሪው በዚያ  ቀውጢ ዘመን ራሳቸውን በጥቅማጥቅም ለማኖር ሲሉ ባርነትን አሜን ብለው በመቀበል ሀገርን ለጠላት አሳልፈው  የሰጡና በራሳቸው ወገን ላይ ፊታቸውን አዙረው የዘመቱ ጥቂጥ ባንዳዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። ዛሬም እነዚያ የሞሰለኒ  አሽከሮች ካደረሱብን በደል በላይ በከፋ መልኩ ሀገርና ታሪክን እያጠፉ ያሉት፤ የኢጣልያ ባንዳ ከነበሩት ከአቶ አስረስ  ተሰማ የልጅ ልጅ ሟቹ መለስ ዜናዊ ጀምሮ በርካታዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት የባንዳ ልጆች (ሰላቶዎች) መሆናቸውን  መገንዘብ ይኖርብናል።
(በ ይታያል እውነቱ) ሆላንድ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar