mandag 29. april 2013

የትግሬ-ናዚዎች አዋጅ፦ “ዐማራን ከምድረ-ገፅ እናጠፋለን!” – ሞረሽ



. ናዚዝም በጀርመን ፣ ፋሽዝም በጣሊያን ቢቀበሩም በኢትዮጵያ ትንሣኤ አግኝተዋል (PDF)


ናዚዝም እና ፋሽዝም በአውሮፓ እንዲያቆጠቁጡ ምክንያት የሆናቸው አንድ ዓይነት መንስዔ ብቻ ነበር ብሎ ለመደምደም ያስቸግራል። ሆኖም ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት በተባባረው የእንግሊዝ እና ፈረንሣይ ኃይል ተደቁሳ፣ ወርራ ከያዘቻቸው የቅኝ ግዛቶቿ በተጨማሪ ከራሷም ግዛት እንድታጣ በመደረጉ፣ እንዲሁም ጦርነት መቀስቀሷ ምክንያት ተደርጎ ለአሸናፊዎቹ ለእንግሊዝ እና ለፈረንሣይ እንድትከፍል የተገደደችው የጦርነት ካሣ ቁልል ኢኮኖሚዋን መቀመቅ ከትቶት ሰለነበረ በጀርመኖች ዘንድ «ተጠቃን ፣ ተዋረድን ፣ የእኛ የነበረውን አሣጡን» የሚል ቁጭት እንዲፈጠር አድርጎ ነበር። ስለዚህ አዶልፍ ሒትለር እና የፖለቲካ አጋሮቹ ያንን የጀርመን ሕዝብ ቁጭት፣ የተከሠተውን ኢኮኖሚያዊ ችግር፣ እርሱንም ተከትሎ በጀርመን ሕዝብ ላይ የደረሠውን የተመሠቃቀለ የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ በፈጣን እና «በአስተማማኝ የጀርመን ብሔረተኝነት» መፍትሔ ለመስጠት እንደሚችሉ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ማዝነብ ጀመሩ። በቤኔቶ ሙሶሊኒ ይመራ ለነበረው ለጣሊያን ፋሽስቶች አነሣሥም አመቺ ሁኔታ የፈጠረላቸው ከሮም አገዛዝ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አዲስ ከተዋቀረችው የኢጣሊያ ሪፓብሊክ አመሠራረት ጀምሮ የዘለቀው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሲሆን ያም «ፈጣን ለውጥ እናመጣለን» ለሚሉ አጭበርባሪ ፋሽስቶች የተመቻቸ የፖለቲካ ድባብ መፍጠሩ አልቀረም።

ናዚዝም እና ፋሽዝም በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተፈጥረው በሁለት የተለያዩ ሥያሜዎች ቢጠሩም መገለጫ ባህርይዎቻቸው ተመሣሣዮች ነው። ናዚዝምም ሆነ ፋሽዝም የፓርላማ ዲሞክራሲን አይቀበሉም። ለእነርሱ ብሔረተኝነት የሚገለፀው በዘር (በጎሣ ወይም በነገድ) ላይ በተመሠረተ መሥፈርት ላይ ስለሆነ የርዕዮታቸው መሠረት ሁሉ ዘረኝነት ነው። ለናዚዎች እና ለፋሽስቶች የቡድን ማለትም «የጎሣ ወይም የነገድ» መብት ከሁሉም መብቶች በላይ ስለሆነ የግለሰብ መብት ሥፍራ የለውም። በተለይ ደግሞ ናዚዎች «ምርጥ የሆነው የአርያን ዘር ነን» ብለው ስለሚያምኑ ዘራቸውን ከሌላው ዘር ሣያቀላቅሉ ማራባት መርሆዋቸው ነበር፣ ነውም። ናዚዎች ለፖለቲካ ግባቸው መቀስቀሻ ፀረ-አይሁዳዊነት ዋና መፈክራቸው ስለነበረ ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዶችን በአሠቃቂ ሁኔታ በግፍ ጨፍጭፈዋል። ለፋሽስት ጣሊያኖች ዋና ጠላታቸው «ኢትዮጵያዊ» በተለይም ደግሞ «ዐማራ» የሚባለው ዘር ስለነበረ ኢትዮጵያን በወረራ በያዙበት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ፤ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በእሣት በማጋዬት እና በሌሎችም አሠቃቂ መንገዶች ጨፍጭፈዋል። በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በፋሽስት ጣሊያኖች በብዛት የተጨፈጨፉት ዐማራዎች ነበሩ። ናዚዎች እና ፋሽዝቶች በነፃ ገበያ መርሆ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት አይቀበሉም። ስለዚህ የመሠረቱት የኢኮኖሚ ሥርዓት በዘር ትሥሥር እና በሥውር ሤራ ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ካፒታሊዝምን የጀርባ አጥንት አድርጎ የሚንቀሣቀስ የማፍያ ካፒታሊዝም ነበር። በፖለቲካ አመለካከታቸውም ዜጎቻቸውን ለፍፁም አምባገነናዊ አመራር ታዛዥ የሚያደርግ ሥርዓትን ያራምዳሉ። ስለሆነም የሊበራል ዲሞክራሲንም ሆነ በተፃራሪ የቆመው የግራ ርዕዮተ-ዓለም «ኮሚኒዝምን» አምርረው የሚጠሉ እና የሚታገሉ ነበሩ፣ ናቸውም። ሁለቱም እኒህን የርዕዮተ-ዓለማቸውን ምሦሦዎች ያቆሙት «ውሽት ሲደጋገም ወደ እውነቱ ይጠጋል» በሚሉት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ላይ ነበር። ከላይ የተዘረዘሩትን ለሚመለከት የትግሬ-ወያኔዎች ቀዳሚውን የርዕዮተ-ዓለም መሠረታቸውን ያገኙት ከጀርመን ናዚዎች እና ከጣሊያን ፋሽስቶች መሆኑን ለመገንዘብ ይችላል። ለትግሬ-ወያኔዎች ሁለተኛው የርዕዮተ-ዓለማቸው መሠረት ደግሞ የኮሚኒዝም አመለካከት ነው። አንድ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው «እንዴት ተደርጎ እኒህን ሁለት ፍፁም ተፃራሪ የሚመስሉ ርዕዮቶች አንድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት በተጣመረ ሁኔታ መርሆ አድርጎ መቀበል ይቻላል?» ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ ተገቢ ጥያቄም ይሆናል። መልሱ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔዎች በሚሄዱበት አቅጣጫ ከተሄደ ይቻላል፤» ነው። ለዚህ እንዲረዳ የትግሬ-ወያኔዎችን የመጀመሪያውን የ1968 ዓ.ም. ማኒፌስቶ በከፊል መመልከቱ ይጠቅማል።

የቀድሞው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የአሁኑ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) ወይም በተለምዶ አጠራሩ
«ወያኔ» በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ በግልፅ እንዳሠፈረው፦

«ትግራይ ኣክሱም እስከወደቀችበት ጊዜ ድረስ የኣክሱም መንግሥት እየተባለች ትጠራ ነበር። ኣክሱም ከወደቀች በኋላም እራሷን በማስተዳደር ለብዙ ጊዜ ብትኖርም ቅሉ ኣልፎ ኣልፎ ባካባቢዋ ለነበሩት ነገሥታት ግብር መክፈሏ አልቀረም። በኣፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ኃይሏ በርትቶ ባካባቢዋ የነበሩትን ነገሥታት በቁጥጥሯ ሥር አውላ ነበር። ይሁን እንጂ አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ ኣማካኝነት ትግራይ በሸዋው ማእከላዊ ግዛት ሥር ወደቀች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው የኣማራው የመሳፍንት ቡድንና ተከታዮቹ የትግራይን ነፃነት ገፈው የሕዝቧን አንድነት ያናጉት። ግልጽና ስውር በሆኑ ዘዴዎችም [ሸዋዊ ዘይቤዎች] የትግራይ ሕዝብ በድንቁርና ፣ በበሽታ ፣ በረሃብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት። በተለይም ትግሬነቱን በፍጥነት እንዲክድና ያለውድ በግድ “አማራ ለማድረግ” ያልሞከሩት ዘዴ ባይኖርም መሬቱ ተቆራርሶ ስለተወሰደበትና የተደራረበ ጭቆና ስለደረሰበት አገሩን ጥሎ ተሰደደ። ባጠቃላይ ባሁኑ ጊዜ ትግራይ ነፃነቷ የተገፈፈች ፣ መሬቷ ተቆራርሶ የተወሰደባትና የተወሳሰበ ችግር የደቆሰው ሕዝብ የሚኖርባት ጭቁን ብሔር ናት። (ገፆች v-vi)
ሀ – ራስ ን መጣል (ዲ -ሁማ ናይ ዜሽ ን )፦

ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሚሄደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ በሰፊው የትግራይ ህዝብ ላይ ድሕነት ፣ ረኃብና ውርደት እየተደጋገመ እንዲደርስ አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ ለረጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈጸምበት ቆይቷል። ይህም በደል ጨቋኝዋ የአማራ ብሔር ሆነ ብላ እንደመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን ፋሽስታዊ ደርግም በባሰና በመረረ መንገድ ቀጥሎበታል። ከዚህም የተነሳ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ኑሮው እንዲቆረቁዝ ተደርጓል። በዚህ ምክንያት የሥራ ማጣት ችግር ፣ ሽርሙጥናና ስደትን ከማስከተሉም በላይ ራስን መጣልና መንከራተት የትግራይ ሕዝብ ዕለታዊ ተግባሩ ሆኖ ይገኛል። ስለሆነም ሕዝቡ ተጠርጣሪና የተጠላ እንዲሆን በመደረጉ በህብረት መኖር የማይቻል ሆኖ ይገኛል። (ገፅ 15)

ለ – የህብረተሰ ቡ ወደኋ ላ መቅ ረትና ዕረፍት ማ ጣት

ሰፊው የትግራይ ህዝብ ሥራ አጥቶ በሽርሙጥናና በስደት ወ.ዘ.ተ. ብቻ

ሳይሆን በረኃብ ፣ በድንቁርናና በበሽታ እየተሰቃየ ይኖራል። እነዚህም ችግሮች ወንጀል እንዲፈጽም ይገፋፉታል። ለችግሩ መሠረታዊ ምክንያት ኢምፐርያሊዝምና ባላባታዊ ሥርዓት ይሁኑ እንጂ ጨቋኝዋ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚ ብዝበዛና የፖለቲካ ጭቆና ታክሎበት ነው። ከዚህም በላይ የሚያኮራው የህዝባችን ታሪክ ፣ ባህልና ቋንቋ እንደዳከምና ተዳክሞ እንዲጠፋ ወይም የአማራ ብሔር የገዢ መደብ ጥቅም እንዲጠብቅ የ3ሺ ዓመታት ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ይገኛል። ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሔር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ታሪክ እንደሌለው ሕዝብ እንዲያስቆጥረው የተደረገ የመንግሥት መመሪያ ነው። ቢሆንም የትግራይ ህዝብ ቂሙንና ተቃውሞውን በቁጣና በጥላቻ በብዙ መንገድ ደጋግሞ ገልጸዋል። ይሁንና ይህንን የመሳሰሉ አድሃሪ ድርጊቶች አሁን ያለው ፋሽስታዊ መንግሥትም ስለቀጠለበት ሰብዓዊ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ትግሉን አያቋርጥም። ጨቋኝዋ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋ እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰብዓዊ እረፍት አታገኝም። (ገፆች 15-16)

ሀ – ዓላማ ውና ሥራው ፦

የትግራይ ህዝብ ብሔራዊ ትግል ፀረ-የአማራ ብሔራዊ ጭቆና ፣ ፀረ-ኢምፐርያሊዝም እንዲሁም ፀረ- ንኡስ ከበርቴያዊ ጠጋኝ ለውጥ ነው። ስለዚህ የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ሥርዓትና ከኢምፐርያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ማቋቋም ይሆናል።» (ገፅ 18)

ሰለሆነም ወያኔ የተመሠረተበት ዓላማ እና ተልዕኮ ከላይ በድርጅቱ ማኒፌስቶ በግልፅ የሠፈረው አቋሙ ነው። ወያኔዎች ተዋጊዎቻቸውን ከሚቀሰቅሱባቸው መፈክሮች «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ» የሚል ይገኝበታል፤ ትርጉሙም «የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቀበሪያ ይሆናሉ» ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬም ዐማሮችን በነገዳቸው ለይቶ መፍጀት ከዚህ የትግሬ-ወያኔዎች የትግል መግለጫ የመነጨ፣ ግቡም የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት እንደሆነ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባም።

2. የዐማራ ሕዝብን ሠቆቃ እና ህልውና ለመካድ «የዐማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ብሎ ማደናገር

ሠሞኑን ከጎልማሣዎቹ የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ ድርጅቶች ጀምሮ እስከ ጨቅላዎቹ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ድረስ እየተቀባበሉ በሚያቀርቧቸው መግለጫዎች ላይ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቀሉ» የሚል አዝማች ቃል አላቸው። ለመሆኑ «ዐማራ» የሚባል ነገድ እና ሕዝብ የለም ወይ? የትግሬ-ወያኔዎች እና ተባባሪዎቻቸውስ በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅሙት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ተግባር የለም? ችግሩንስ በዚህ መልክ አድበስብሶ ማቅረቡ እና ማደናገሩ «ለማን ደስ ይበለው» ተብሎ ነው? የተፈናቀሉት «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ከሆኑ እኮ አፈናቃዮቹ እና ጨፍጫፊዎቹም ሟቹ የወያኔዎቹ ጣዖት መለስ ዜናዊ ፣ የደቡቡ የወያኔ ሎሌ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ በመተከል እና በአሶሳ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው አህመድ ናስር ጭምር አማርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው የሚናገሩ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ናቸው። ሰለዚህ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» የሆኑት ሹሞች «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን አፈናቀሉ» ለማለት ተፈልጎ ይሆን? በተቃራኒው ግን እኒህ የፖለቲካ ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ወያኔዎች በሌሎች ነገዶች ላይ ለሚፈፅሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል በስም «ይኼ ነገድ ወይም ጎሣ በወያኔዎች ተጨፈጨፈ» ብለው መግለጫ ያወጣሉ። ስለሆነም እኒህ «በሕብረ-ብሔር ፖለቲካ እናምናለን» የሚሉት ድርጅቶች በሚያወጡት መግለጫ ግልፅ በሆነ ቋንቋ «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከሚሉ ድረስ መጠበቅ የለባቸውም። ምክንያቱም አሁን ለተጋፈጥነው ችግር መባባስ አንዱ ሠበብ «የዐማራ ነገድ የኢትዮጵያ ችግር ምንጭ እንጂ የችግሩ ሠለባ ሆኖ አያውቅም» የሚለው እና ላለፉት 40 ዓመታት የኢትዮጵያ የግራ-ዘመም እንዲሁም ራሣቸውን «የሕብረ-ብሔር ፖለቲከኞች ነን» ብለው የሚጠሩት በቀዳሚነት ሲያቀነቅኑት የቆዩት የፖለቲካ አመለካከት ያለማንም ሞጋች እንደወረደ በይሉኝታ ተቀባይነት አግኝቶ በመቀጠሉ ነው።

3. የትግሬ-ወያኔዎች እስከዛሬ በዐማራው ላይ ምን አደረጉ?

የትግሬ-ወያኔዎች ገና ክጥንስሣቸው ጀምሮ ለዐማራ ሕዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ያንንም የመረረ ጥላቻቸውን እስከ ዘር ማጥፋት በሚደርስ እርምጃ ከመግለፅ የቦዘኑበት ወቅት የለም። ይህ ያልተገለፀለት ሰው ቢኖር ከገሃዱ ዓለም ወጥቶ በተምኔታዊ የቅዠት ኅዋ ውስጥ ራሱን

የደበቀ ብቻ ነው። የትግሬ-ወያኔዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ ከፈፀሟቸው አያሌ ከሆኑት ናዚያዊ ተግባሮቻቸው መካከል ዋና ዋናዎቹን አለፍ አለፍ እያሉ መጥቀስ ለማስታወስም ያህል ይረዳል።

ገና ሲሽፍቱ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀሱበት የመጀመሪያዎቹ ሦሥት ዓመታት እነርሱ ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረጓቸው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። እንዲያውም ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለትግሬ-ወያኔዎች ግን እኒያ ሰዎች ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ እየለቀሙ ጨፈጨፏቸው።
ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ ወደ ጎንደር የመስፋፋት ጦርነት አድማሱን ሲያሠፋ የመጀመሪያ እርምጃው በወልቃይት እና ጠገዴ የሚኖሩ የጎንደር ዐማሮችን በጅምላ መፍጀት ነበር። እስከዛሬ ምን ያህል የወልቃይት እና የጠገዴ ዐማሮችን እንደጨፈጨፉ በአሃዝ ለይቶ ለማስቀመጥ ቢከብድም በ20 ሺህዎች የሚቆጠሩትን ከምድረ ገፅ እንዳጠፉ፣ ከ70 ሺህ የማያንሱትን ደግሞ ከጥንት አባቶቻቸው ርስት አፈናቅለው ስደተኛ እንዳደረጓቸው ይታወቃል። ወያኔዎች የጎንደር ግዛት የሆነውን የወልቃይት ፣ የጠገዴ እና የፀለምት አካባቢዎችን «የትግራይ ክልል» ብለው ነጥቀዋል። በአካባቢውም ከተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ያመጧቸውን የራሣቸውን ዘር አሥፍረውበታል።
ሥልጣን ከያዙበት ከግንቦት 1983 ዓም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ ዐማሮችን፦ «ነፍጠኞች፣ ትምክህተኞች፣ አድሃሪዎች፣ ጨቋኞች፣ የትግራይ ሕዝብ ደም መጣጮች፣ ወዘተርፈ» እያሉ ከአገራቸው አፈናቅለዋል፣ ጨፍጭፈዋል። በተለይም ከግብር አጋሮቻቸው ከሻቢያ ፣ ከኦነግ እና ከኦብነግ ጋር በመሆን በሐረርጌ (በበደኖ፣ በሐብሩ፣ እና ሌሎች ሥፍራዎች)፣ በአርሲ (በአርባ ጉጉ እና ጢቾ)፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በባሌ፣ በሲዳማ፣ በጌድኦ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በጉራፈርዳ፣ በመተከል፣ በአሶሳ እና በሌሎችም አካባቢዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በአሠቃቂ ሁኔታ ፈጅተዋል።
ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ «ብረት ማስፈታት» በሚሉት ዘመቻ ዐማራው ሙሉ በሙሉ ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጓል። በተለይም «የዐማራ ክልል» ብለው በሠየሙትና አብዛኞቹ የዐማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ይህንን ዘመቻ በበላይነት የመራው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ነው። ዛሬ ዛሬ የዐማራ ተወላጅ እንኳን የጦር መሣሪያ ይቅርና የብረት ጅንፎ ያለው ዱላ መያዝ ጦር መሣሪያ እንደመታጠቅ ተቆጥሮበት ራሱን ከትንሽ አውሬ የሚከላከልበት ዱላ እንኳን መያዝ አይችልም።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. ባካሄዱት «ሽፍታ ምንጠራ» ብለው በሠየሙት ዘመቻ ከዐማራው መካከል ንቃተ-ኅሊናቸው ከፍ ያሉትን እና «ለትግሬ-ናዚያዊ አገዛዝ አይንበረከኩም» ብለው የሚያስቧቸውን ዐማራዎች እየለቀሙ አሥረዋል፣ ደብዛቸውን አጥፍተዋል፣ ገድለዋል።
ከ1986 እስከ 1987 ዓ.ም. ዐማራውን በሦሥት መደቦች ከፋፍለው፦ የወያኔ ኮር አባል፣ ተራ ዜጋ እንዲሁም ቢሮክራት እና ፊውዳል ብለው መድበው መሬት አከፋፍለዋል። የመሬት ድልድል ሲያደርጉ በገጠሩ የዐማራ ማኅበረሰብ መካከል የመደብ ልዩነት በመፍጠር ዐማራው እርስ በእርሱ እንዲፋጅ ሲያደርጉ፣ በተለይም ደግሞ አብዛኛውን ዐማራ የኢኮኖሚ ዐቅሙ የተዳከመ እና ፍፁም በድነህት የሚማቅቅ ምስኪን አድርገውታል።
ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች «የጦር መሣሪያ ታጥቃችኋል፣ የኦሮሚያን መሬት ለግላችሁ አድርጋችኋል፣ የኦሮሚያ የቦታ ሥሞችን የዐማራ ስም አውጥታችሁላቸዋል፣ የከብት ዝርፊያ ትፈፅማላችሁ፣ ደን ትመነጥራላችሁ» እና የመሣሠሉትን ሠበቦች በመደርደር ከ12 ሺህ የማያንሱትን አፈናቅለዋቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ደግሞ የአካባቢው የወያኔ ሎሌ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ታጣቂዎች ፆታ እና ዕድሜ ሣይለዩ በአሠቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈዋቸዋል። የተፈናቀሉት ዐማሮች ከነበሩበት ሥፍራ ተባርረው ጎጃም ክፍለሀገር አገው ምድር አውራጃ ውስጥ ጃዊ የሚባል እጅግ ሞቃታማ እና በወባ ወረርሽኝ በሚጠቃ ወረዳ እንዲሠፍሩ ተደርገው አብዛኞቹ በወባ ወረርሽኝ እንዲያልቁ ተደርገዋል።
ከሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ወዲህ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች “የግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎች ናችሁ” ተብለው ከታሠሩት ከ37 በላይ የሲቪል ፣ የደህንነት ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የወታደር እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ዐማሮች ናቸው። በእኒህ እሥረኞች ላይ የወያኔ መርማሪ ፖሊሶች ካደረሱባቸው ዘግናኝ ግርፋት ዓይነቶች መካከል፦ የወንድ የዘር ብልት ማኮላሸት፣ በኤሌክትሪክ መጥበስ፣ ጥፍር መንቀል፣ ከባድ ድብደባ፣ በአስጨናቂ ሁኔታ በካቴና ጠፍሮ ማሠር እና ከጣሪያ ላይ ማንጠልጠል፤ እንቅልፍ መከልከል፣ በርሃብ እና በውኃ ጥም ማሠቃዬት፣ ጫካ ውስጥ ወስዶ ግድያ እንደሚፈፀምበትና ሬሣው ለአውሬ እንደሚጣል ማስፈራራት ይገኙባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በአካል የተሠቃዩት ሣያንስ እጅግ ቅስም-ሠባሪ ዘለፋ ለመስማትም ተገድደዋል፦ ከወያኔዎቹ አረመኔ ገራፊዎች ከሚወጡት ቃላት ውስጥ፦ “ትምክህተኛ ዐማራ፣ ግም ዐማራ ፣ ብስብስ ዐማራ፣ ሽንታም ዐማራ፣ ፈሪ ዐማራ፣ በኤድስ ቫይረስ የተበከለ ደም እንወጋሃለን፣ ከሃምሣ ጋይንት አንድ አጋንንት ይሻላል አንተ ሆዳም ጋይንቴ፣ ዘር-ማንዘርህን ቀሚስ አልብሰን የወጥ-ቤት ሠራተኛ አድርገን እንገዛዋለን፣ አንተ ደም መጣጭ ጎጃሜ እናቃጥልሃለን፣ ዘረ-ቆሻሻ ዐማራ፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ይገኝባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በወያኔው የጨረባ ፍርድቤት እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
እነዚህ ሁሉ የትግሬ-ወያኔዎች የዐማራ ጭፍጨፋ ድርጊቶች ከራሣቸው አንደበት እና ዘገባ ማረጋገጥ የተቻሉ ናቸው። በተለይም በ1999 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔዎች ባካሄዱት የሕዝብ ቆጠራ «አረጋግጠናል» ብለው ለሕዝብ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት ከ1989 እስከ በ1999 ዓ.ም. በነበሩት 10 ዓመታት ብቻ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ዐማሮች የደረሱበት አልታወቀም ብለዋል። በእርግጥ ይህ የአሃዝ አገላለፅ ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በራሣቸው በወያኔዎች የታመነውን ጉዳይ ከማስተባበል ይልቅ ከጨፈጨፏቸው የዐማራ ነገድ ተወላጆች መካከል ከዚህ ቁጥር ውስጥ ያልተካተቱት ምን ያህል እንደሆኑ ማጣራቱ ይበልጥ ትርጉም ይኖረዋል።

4.የእነርሱን የጥፋት እርምጃ ለመግታት እስከዛሬ ምን ተደረገ? ውጤት ተገኘበት ወይ?

የትግሬ-ወያኔዎችን ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ ለመመከት እና ዐማራውን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን በድርጅት በታቀፈ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉልህ እንቅስቃሴውን የመሩት ሟቹ መሪ ፕሮፌሠር አሥራት ወልደየስ ነበሩ። ፕሮፌሠር አሥራት የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን (መዐሕድ) በ1984 ዓ.ም. ከትግል ጓዶቻቸው ጋር ሲመሠርቱ የዐማራው ሕዝብ በትግሬ-ወያኔዎች የተጋረጠበትን ከምድረ-ገፅ የመደምሰስ አደጋ በውል ተገንዝበው ነበር። ሆኖም ፕሮፌሠር አሥራት የሚመሩት መዐሕድ ከውጭ በግልፅ በወያኔ እና በሻቢያ ፣ ከውስጥ ደግሞ ሥውር የሆነ መንገድ በወያኔ-ተላላኪ ሠርጎ ገቦች የደረሠበትን ቡርቦራ መቋቋም አልቻለም። መዐሕድ በተመሠረተ ሁለት ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወያኔ ፕሮፌሠር አሥራትን «የጦርነት ቅስቅሣ አድርገሃል» ብሎ ለእሥር ዳረጋቸው። ከዚያም በእሥር እያሠቃየ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን በማከም፣ አልፎ ተርፎም የሕክምና ባለሙያዎችን በማሠልጠን ሰብዓዊ ሕይወትን ለ40 ዓመታት ሲታደጉ የኖሩትን ታላቅ የሕክምና ሊቅ ሕክምና ነፍጎ፣ በግንቦት 1990 ዓ.ም. ለሞት አበቃቸው። ከፕሮፌሠር አሥራት መታሠር በኋላ ለዐማራው ሕዝብ ቋሚ ጠበቃ ሆኖ ጠንክሮ የሚታገል ድርጅት ለማፍራት አለመቻሉ ብቻ ሣይሆን የዐማራውን ጉዳይ «ጉዳዬ ነው» ብሎ በኃላፊነት የሚመራ ስብስብ እንኳን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች ፍሬ አልባ ሆነው ቆይተዋል። ለዚህ ሠበብ ሆነው የሚቀርቡ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም አንዱ የብዥታ ምንጭ የዐማራው ልሂቃን ከራሣቸው ነገድ ህልውና ይልቅ «በይስሙላ የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ» ጥልፍልፍ ውስጥ ተዘፍቀው የራሣቸውን ወገን ችግር ችላ በማለታቸው ነው። የሚያሣዝነው የዐማራው ልሂቃን ራሣቸውን ከገሃዱ ዓለም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ አግልለው፣ በሌሉ ተምኔታዊ የማኅበራዊ ሣይንስ ፍልስፍናዎች ውስጥ ተጠምደው፣ በትግሬ- ወያኔዎች የሠቆቃ አገዛዝ ሥር ለሚማቅቀው ለዐማራው ወገናቸው ጠቃሚ አስተዋፅዖ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

ለዐማራ ሕዝብ መከራ መራዘም እና ለኢትዮጵያውያንም የወደፊት ተስፋ ማጣት ሌላው ምክንያት የፖለቲካ ልሂቃኑ የሚከተሉት ውል- የለሽ እና ውጤት-አልባ የትግል ሥልት እንደሆነ ግልፅ ነው። በውጭ በሥደት የሚኖሩት ዐማሮች ግማሾቹ በሰላማዊ ሠልፎች ጋጋታ እና በኢንተርኔት መድረኮች እርግማን ብዛት ብቻ የትግሬ-ወያኔዎችን አገዛዝ መጣል ይቻል ይመስል ትኩረታቸውን በዚያ ላይ ወስነዋል። ግማሾቹ ደግሞ «ወያኔን በትጥቅ ትግል እናስወግዳለን» ብለው አጉል ተስፋ ያስጨብጡና «በመሣሪያ ትግል የምንጀምረው በሻቢያ ድጋፍ ከኤርትራ መሬት በመወርወር ነው» ይሉናል። በመካከሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋው «ጉም መጨበጥ» ሆኖበት ይበልጥ ግራ ተጋብቶ እንዲቀመጥ ተገድዷል። በአገርቤት የሚገኙት የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ከወያኔ መሞዳሞዱ እንዳይቀርባቸው ስለትግል ሥልታቸው የቃላት ጨዋታ ይዘዋል፦ ሲጀምሩ ሰላማዊ ትግል የሚል ቃል ይጠቀሙ ነበር። ወያኔ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ ከፊት «ሕጋዊ» የሚል ቃል ጨምረው «ሕጋዊና ሰላማዊ ትግል እናካሂዳለን» ይላሉ። ነገር ግን የትግሬ-ወያኔዎች በሚገዟት ኢትዮጵያ ሕጋዊነትም ሆነ ሰላማዊ ሁኔታ የለም፣ አይኖርምም። ስለሆነም የትግሬ-ወያኔዎችን አገዛዝ ለማንበርከክ በመጀመሪያ በትግል ሥልት ላይ ግልፅ እና ለውጤት የሚያበቃ አቋም መያዝ ያስፈልጋል።

5.ምን መደረግ አለበት?

የትግሬ-ወያኔዎችን ናዚያዊ አገዛዝ ከሥሩ መንግሎ ለመጣል በአገርቤት ያለው ዋናው የሕዝብ ክፍል እና በውጪ በሥደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ እንደሚኖሩበት አካባቢ ተጨባጭ ሁኔታ መወጣት የሚገቧቸውን ሚናዎች ለይተው ሊያውቁ ይገባል። ለምሣሌ አገርቤት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በአገዛዙ የሚደርስበትን ጭፍጨፋ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በአካል ቀርቦ ለማስረዳት አይችልም፣ ክስ ለመመሥረትም አዳጋች ይሆንበታል። ምክንያቱም ግልፅ እና የማያሻማ ነው፦ ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ እንዴት ተደርጎ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተኖረ በወያኔ ላይ ክስ ማቅረብ የሚቻለው? በውጪ በአንፃራዊ ነፃነት ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያውያን ግን እንዲህ ዓይነቱን ኃላፊነት ለመወጣት ጊዜውም፣ ገንዘቡም፣ ዕውቀቱም፣ አማራጩም አላቸው። በሌላ ወገን ደግሞ አገርቤት ያሉቱ ሕዝቡን በቃላት ጨዋታ ከሚያደነዝዙት እና ራሣቸውንም ከፖለቲካ ትግሉ ጡረታ ባያወጡ ይበጃቸዋል። በግልፅ ቋንቋ እርባና ያለው የፖለቲካ ሥራ መሥራት ካልቻሉ እና በተቃዋሚነት ከሚቀጥሉ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ቢቀመጡ ቢያንስ የጥፋቱ ተባባሪ ከመሆን ይድናሉ። «ለዐማራው ሕዝብ ብሶት ቆመናል» የሚሉት ደግሞ ከትግሬ-ወያኔዎች ወገን የሚደርስባቸው ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ፣ ፈተናቸውም ከባድ ነውና ያላቸውን ግልፅ አደረጃጀት እንደገና ሊያጤኑት ይገባል። የዐማራን ነገድ ተወላጆች የሠቆቃ ዘመን ለማሣጠር እና የኢትዮጵያንም ዳግም ትንሣኤ ዕውን ለማድረግ እያንዳንዱ የዐማራ ተወላጅ በቦታ፣ በጊዜ፣ በገንዘብ፣ በቁሣቁስ፣ በድርጅት፣ በአጠቃላይ በሁሉም በሚችለው መንገድ አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅበታል። ያለበለዚያ ግን የመከራው ዘመን መራዘሙ ብቻ ሣይሆን ዐማራው ከምድረ-ገፅ እንደሚጠፋ በትግሬ-ወያኔዎች እና በተባባሪዎቻቸው ከተያዘው የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ መገንዘብ ያስፈልጋል።http://welkait.com/?p=634

 <http://www.zehabesha.com/

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar