ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ዝርዝር ጥልቀት ያለው ሐተታ ቀርቶ የውጣ ቃልም ብትሆን ስለ ኢሳት አንጻራዊ አመለካከት ማንጸባረቅ፡ ተቋሙ እየተከተለው ያለውን አሰራርና እየሄደበት ያለው ማንንም የማይጠቅም መንገድ እንደ ዜጋ በግልጽ መናገር: ትንፍሽ ማለት በተለይ “ይውደም!” ከተባለ “ይውደም!”- “ይቅደም!” ከተባለም እንዲሁ በተመሳሳይ ድምጽ “እንዴትና? ለምን?” በሌለበት ሁኔታ “ይውደም!” በማለት ድምጹን በማስተጋባት በሚታወቀው ማህበረሰብ አካባቢ ዘንዳ ምን ዓይነት ስም ሊያሰጥ እንደሚችል በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የደርግ ወታደራዊ መንግስት ቀን ጨለማ ሳይል የንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ ሲያደርግና በገዛ ሕዝቡ በአደባባይ በጥይት ሲደበድብ/ሲረሽን አገኘሁበት የሚለው ክስ አንዱ “ጸረ አብዮት ነው!” በማለት ነበር ሲሉ ከሞት ያመለጡ ምስክሮች እንደሚናገሩት ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ መስመሩ ስለ ለቀቀና አቅጣጫው ክፉኛ ስቶ ስለሚገኘው: ታማኝነት የጎደለበት፡ ከምንም በላይ ደግሞ የሞያው ስነ ምግባር በሚጣረስ መልኩ ሆነ ተብሎ እየተደረገ ያለው የኢሳት አሰራር ጭብጥ ላይ የተመረኮዘ ተጨባጭ ሃሳብ ይዤ መመጎቴ ተከትሎ በጸሐፊው የ/ለሚለጠፉ ታቤላዎች አግባብነት የለውም ችግሩም ይቀርፈዋል የሚል እምነት የለኝም።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመልከተ በተለይ ከወቅቱ ጋር በተያያዘ የሃይማኖት መሪዎች የእርስ በርስ የመተረማመሱ ነገር እንዲሁም በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች በኩል ከመንፈሳዊነት ይልቅ እልከኝነት የተሞለበት ስብእናቸው አይሎ ከመውጣቱ የተነሳ የከሸፈውን እርቀ ሰላም በኢሳት በኩል ያለ አንዳች ተጨባጭና ደረቅ ማስረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ለማድረግ የተሰሩ “ዜናዎችና ሐተታዎች” ብዛቱ ስፍር ቁጥር የለውም። ይህ የምለው ደግሞ እንደ ወንጌል አገልጋይነቴ እውነቱ እውነት ለማለት እንጅ ለመንግስት ጥብቅና ለመቆም ቃጥቶችም አይደለም። ቀደም ሲል በእኔ በኩልም ሆነ በሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና መምህራን አማካኝነት ከዚህ ሁሉ የሃይማኖት መሪዎች ትርምስ ጀርባ ለመልካም ነገር የሚያበቃ አቅም ባይኖረውም ለሁከትና ለረብሻ ግን የሚስተካከለው የሌለው “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት ራሱን የሚጠራ ስመ መንፈሳዊ አጽራረ ጽድቅ ድርጅት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የማፈራረስ ዓላማ አንዱ ስትራቴጂ መሆኑ በተጨባጭ ሲነገር መክረሙን የምንዘናጋው እውነት አይደለም።
ሰሙኑ ከወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ ግልጽ እንዳደረገው ደግሞ ይህ ግብረ እከይ ማህበር (“ማህበረ ቅዱሳን”) አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ሳይቀር ራሱ ጨምሮ በአባልነት እንደሚገኝበት ነበር በይፋ የተነገረው። ታድያ ይህን የመሰለ ሕዝብ ሊሰማውና ሊያውቀው የሚገባው ጥብስ የሆነ ዜና በኢሳት ዘንድ በዝምታ መታለፉ ብቻ ሳይሆን የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ታይቶኝ ነገሩ አግራሞት ስለጣለብኝ ነው ኢሳት ይጠየቅልኝ! የሚል ጽሑፍ ይዤ ብቅ ለማለት የወደድኩ።
የመንግስት ባለ ስልጣን ስም ጠርታችሁ “አቶ እገሌ በጳጳሳት መካከል ተገኝተው እንዲህ ብለው ተናገሩ” በማለት አሉባልታ ከመዝራት ያልተመለሳችሁና ያላሳፈራችሁ ሰዎች እውነት ቢያንቃችሁ ምን ይደንቃል? የገዛ ራሳችሁ የፈጠራ ስራ “ተባለ: ተሰምቶል: የተገኘው ዜና ያብራራል” በሚል ፈሊጥ ያልተነገረና ያልተባለ የጽሑፉም ሆነ የድምጽ ማስረጃ በማታቀርቡበት: “ተባለ” ሲል ዜና ሰርቶ ያቀበላችሁ ሃላፊነት የሚወስድ ግለሰብም ሆነ የዜና ምንጭ በሌለበት “ትላንት በአዲስ አበባበተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባቶች አቶ አባይ ጸሀዬ በግልጽ እንዳስታወቁት አቡነ መርቆሪዮስ ወደመንበራቸው ይመለሱ ማለት መንግስቱ ሀይለማሪያም ይመለስ ከማለት ተለይቶ አይታይም ማለታቸው ተሰምቶል። …አንዳንድ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ጳጳሳት በተለይም ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመለሱ ከሆነ እኛም አክሱም ላይ የራሳችንሲኖዶስ እናቆቁማለን በማለት ቤተክርስቲያኒቱን በግልጽ በዘር መስመር ለማስቀመጥ ሀሳብ መሰንዘራቸውን የተገኘው ዜናያብራራል።“ ለማለት ግን የቀደማችሁ ማንም አልነበረም። (የኢሳት አማርኛ ዜና » ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ http://ethsat.com/2013/01/15/
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
|
fredag 15. februar 2013
ኢሳት ይጠየቅልኝ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar