fredag 15. februar 2013

ሕወሓት ያመለጥኩሽ ቀን.


.!!!
ከዚህ ቀደም በነበሩት ጊዜያት በተለያየ ጊዜ ሕወሓት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የሚያደርሰውን ጫና እና ዘለፋ እንዲሁም አርፈው እንዲቀመጡ የሚል ቀጭን ትእዛዝ በተለያየ ጊዜ መግለጣችን ይታወሳል:: ይህንን ተከትሎም በ መኖሪያ ቤታቸው የድምጽ መቅጃ መሳሪያዎች መገኘታቸው....ልጃቸው ዮሃና የመለስ ዜናዊ ፕሮቶኮል የነበረውን ሰው በግዳጅ እንድታገባ መሞከር....ባለበታቸው ወይዘሮ ሮማን በፖለቲካ ሂደቱም ሆነ በሰብኣዊ መብቶች ዙሪያ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ማዘዝ....የሃዋርያት አማኞች የጸሎት ቡድን ወደ ቤተ መንግስቱ እንዳይገባ መደረግ....ወዘተ...ካላቸው የስልጣን እርከን ጋር የማይደረጉ ጫናዎች በበታች ሚኒስቴሮች እየተደረገባቸው እንደሆነ ገልጸን ጽፈናል::
ከአቶ ሃይለማርያም ጀርባ ሆነው አገሪትዋን የሚመሩት ደብረጺሆን እና በረከት እንዲሁም ተዎድሮስ አድሃኖም ሲሆኑ የ ተዎድሮስ ጫና እምብዛም የማይታይ ቢሆንም ሳሞራ የኑስ እየተጠቀመበት እንደሆነ እና ለዘብተኛ አቋሙን ጠንከር እንዲያደርገው ካልሆነ ተጠልፎ ሊወድቅ እንደሚችል ለ ወዲ አድሃኖም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው መረጃዎች ጠቁመዋል::
ቴዎድሮስን እንዲቆጣጠር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመደበ ሲሆን ቴዎድሮስ ማንኛውንም ጉዳይ ከማየቱ በፊት ብርሃነ ሳንሱር አድርጎ ለፊርማ ብቻ እንዲደርስ ያደርጋል:: ይህንን ተከትሎ አሁንም ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ቴዎድሮስ አድሃኖም "ለሰፊው ህዝብ" የሚል አስተሳሰብ እንዳይኖረው  ማስጠንቀቂያ ደርሶታል::
በወያኔ ውስጥ የተከሰተው አጣብቂኝ እንደማያገባው እየተናገረ ያለው ወዲ አድሃኖም በደርግ ርእዮተ አለም የተመረዘ ቢሉትም በደብረጺሆን እና ቡድናቸው እንዲሁም በጌታቸው በኩል ድጋፍ ስላለው እየተመከረ እንዲቀትል ተደርጓአል:;
ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተደረገው አስቸኳይ የወያኔ ስብሰባ አቶ ሃይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ የድል አጥቢያ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን የኦህዲድ ነገር ያልተፈታ እና የተካረረ ነገር ስላለው በዛ ጉዳይ የሚሰራ ቡድን ሕወሃት ማደራጀቱን አቶ ጌታቸው ሲገልጡ..አቶ በረከት በበኩሉ አንዱ ካለአንዱ መተንፈስ ስለማይችል ለመፈረካከስ የምታደርጉትን ጥረት እንድታቆሙ ሲሉ የደቡቦችን እና የኦሮሞ ባለስልጣናትን አስጠንቅቀዋል::
ይህንን ተከትሎ በግል ከአቶ ሃይለማርያም ጋር የተወሰኑ የወያኔ በልስልጣናትና የጦር ጄኔራሎች ያደረጉት ውይይት ጠ/ሚኒስትሩን በማስፈራራት እና በመዝለፍ ተጠናቋል:: አቶ ሃይለማርያም ካነሱት ጥያቄ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን እና የሙስሊም ኮሚቴዎችን ጉዳይ ሲሆን .እንዲሁም ያላቸውን ስልጣን በህገ መንግስቱ መሰረት መጠቀም  ካልሆነ በሰላማዊ ሽግግር ብለን ስልጣን ማስረከብ እንደሚፈልጉ የጠየቁ ቢሆንም ...አቶ ደብረጺሆን እና ኣቶ ጸጋዬ እየተፈራረቁ ..ያስቀመጥንህ እኮ ለ2 አመት ነው :: የምታቀርባቸው ጥያቄዎች እኮ አንተ አይደለህም ታጋዮች እንኳን ደፍረው አያቀርቡትም...ስልጣን ለመልቀቅ እሞክራለሁ ብለህ ኢህኣዴግን አደባባይ ላይ ብታጋልጥ ባንተ እና በዘርማዘሮችህ ላይ ለሚደርሰው ተዘዋዋሪ ጥቃት ራስህ ትጠየቅበታለህ:: ...በሚሉ እና ተራ አነጋገሮችን በመናገር ሲያስፈራሩት በወቅቱ የነበሩት የብኣዴን ሰዎች እና ዶ/ር ቴዎድሮስ ነገር በማረጋጋት እየተመካከርን እንጓዛለን :: በማለት ሰላም ቢያወርዱም የሕወሓት ሰዎች ግን ጥርሳቸውን እንደነከሱ  የከፈቱትን የጠ/ሚ. ቢሮ በር ሳይዘጉት ወተዋል::
አቶ ሃይለማርያም የስልካቸው መጠለፍ እንዲሁም የትእዛዝ መብዛት እና መብታቸውን እንዳይጠቀሙ የሚደረገው ጫና እንዳሳሰባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል::እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን እንደ ተራ ሚኒስትር ታይተው ምንም አይነት መረጃም ሆነ የሃገሪቱ ጉዳይ በተመለከተ እውቀት እንዳይኖራቸው እየተደረገ ሲሆን በትንሹም ቢሆን የሚግባቡት ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar