onsdag 27. februar 2013

በአያና ከበደ ከኖርዌይ፡ አገርማለት



አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየትከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት የሚጥቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት ንዲጋኝባት በማድረጉ አገር እየጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆንች እናት ማለት ነው ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ ባቶች በሕህወትና በሞት የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኒ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው ገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህንትና ጥቃት በመጣ ቁጥር ስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ያት ከቅድም  አያትና ከአባቶች በጥብቅ ተሰጠያደራ ገንዘብ ነው   ፡፡
በአሁኑ ወቅት ስንቶቻችንነን የተጣለብንን አደራ  በትክክል የተወትጣን  የሞት ሞት ያባትን አደራመብላት ነው አንዳንዶቻችንማ በአንደበታችን የሚንናገረውን ስናታውስ ምን ነካን ያሰኛል  ፡እኔ ክርስቲያን ነኝ  ያገር ጉዳይ አይመልከትኝም የቤተክሪስቲያስን እንጅ የሚሉ ስፍርቁጥር የላቸውም. ያለአገር ሀይማኖት አለምኖሩን  አልተርዱም ልበል ?ስንቶቻችንነን በተላየዩ ምክናየት በስደት ለይ ሀይማኖታችንን የተነጠቅን.፟፡ በተቃራኒው በአሁኑ ወቅት የአገር ትርጉም  የገባትቸው ብዙ  ጀግኖች  አሉ ፈለጋቸውን ልንከተለው የሚገባን  ለማሳሌ ብጠቅስ 21 አመታት  በትግል ላይ ያለው  የጭልጋው  አንብሳ  በቅጥል ስሙ የቁር ቀን የኢትዮጵያልጅ የሚባለው  እና የመለስ ኢቮላ  የመሳሰሉትን  ጀግኖች  ልንከተላቸው   ይገባል፡፡
ስለ አገር ብዙ ነገሮችን መዘርዘር ይቻላል  ሃገር ፍቅር ነው ፣ሃገር ኩራት ነው ፣ሀገር የአንድነት ግንብነው ፡በአሁኑ ውቅት እኛ ኢትዮጵያን  ፍቅርን ሰላምን፣ አንድነትን በማጣት እርስበርስ በመወነጃጀል የሀገ ትርጉሙ ጠፍቶብን እንገኛለን .
በመጀመሪያ ስለ አንደነታችን  ልንታገል ይገባናል ከመካክላችን ገብቶ አንድነትን የነሳንን የወያኔን  ስረዓትን ማስልቀቅ  አልብን አንድነት ከሌለ  ስለነጻነት፣                                                                           ስለዲሞክራሴ.፣ስለእኩልነት፣ስለፍትህና ስለሃገር ባለቤትነት ማንሳት  በጣም አስቸጋሪነው ፡፡የሃገር የወድፊት እድገ የሚለካው በሃገሪቷ መልካም አስተዳርድር
ላይ ተመስርቶነው ፡፡ለዘህም ነው አንድነት የአንድ ሃገር ህልወና መሰረት ነው የሚባለው ፡፡
                             እምየ ኢትዮጵያ
                         ከኔስ ምን ትሻለች
                    ውድ እናት አገሬ ከኔስ ምን ትሻለች ፣
                   ውድ እናት አገርህ ከአንተስ ምትሻለች፣                                 
                   ዘረፉኝ እያለች ጥሪ ታሰማለች ፡፡
                  ተነሳ ወገኔ አሁን ነው ሳዓቱ ፣
                  ሌባውን ለመያዝ  ሰላም ለማምጣቱ ፡፡
                           መከራን መቻል፣
                           ድልያመቻቻል፣
                           አገርን መጣል  ፣
                          ውርደት ያመጣል፡፡                                                                                  
                    በስዴት ወጥቶ ከመንከራተት ፣
                    ለናት ሃገሩ ከዳሯ መሞት፡፡
    
ወድ ወገኖቼ  ላንዳድ የፊደላቶች ስህተትይቅርታ እጣይቃለሁ  ከለፉት ጽሁፎች ጭምር ፡፡ 
   ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን እግዚአብሔር  ይባርክ !!!
       ፀኃፊውንለማግኘትእናአስተያየለመስጠት፣ ayanakebede@hotmail.com,
ዲሴምበር፣ 26/12/12





                                                                                                                                                              

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar