onsdag 20. februar 2013

የአዲሱ የፓሪያርክ ምርጫ በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ በወሰነው መሰረት የካቲት 21 የፓትሪያርክ ምርጫ ይካሄዳል። የካቲት 24 ደግሞ በአዕለ ሲመቱ ይከበራል።
የምርጫው ሂደቱን በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን የህዝብ ግንኙት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት- አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስን ልደት አበበ አነጋግራቸዋለች። የአስመራጭ ኮሚቴው የደረሰበትን በመግለፅ አቶ እስክንድር ይጀምራሉ።
በትክክል ስለ 5ቱ የፓትሪያርክ እጩዎች ማንነት የሚታወቀው በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 16 መሆኑን አቶ እስክንድር ገልፀውልናል። ይህም የሚሆነው መላው የሲነዶስ አባላት በተገኙበት የአስመራጭ ኮሚቴው እጩ አድርጎ የተቀበላቸውን ሰዎች ይፋ ካደረገ በኋላ ነው። የ6ኛው ፓትሪያርክ ምርጫ በዕጣ ሳይሆን በድምፅ አሰጣጥ እንደሚሆን አቶ እስክንድር አስረድተዋል።
በመጨረሻ ለአቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ያነሳሁላቸው ጥያቄ በሀይማኖቶች አባቶች መካከል የተጀመረው ዕርቅ ሳይጠናቀቅ ወደ አዲስ ፓትሪያርክ ምርጫ መሄዱ ለወደፊቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ምን አይነት ሚና እንደሚኖረው ነው።
Audios
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar