onsdag 18. desember 2013

ኃያሉ አፄ ሚኒሊክ ለሴቶች እኩልነት ተግባራዊነት ዓለምን የቀደሙ ንጉሥ


ከሥርጉተ ሥላሴ 12.12.2013

ያን ዘመን ሳስበው ዛሬን መስለባችን ያስለቅሰኛል። ያን ፈርጣማ ዘመን ሳስታውሰው ዛሬ ውስጣችነን መሳሳቱ ያቃጥለኛል። ያን
ገድላማ ብቁ፣ ሥልጡን፣ ልዑቅ የአመራር ጥብብ ሳናግረው ግን መጽናናትን፣ ሙላትን ያጎናጽፍልኛል። ክብራቻን፤ ማንነታችን፤
ተፈሪነታችን፤ መሪነታችን፤ ብልህነታችን፤ እርግጠኛ ያደረጋል፤ የቀደምቶቹ ብቃት የሰማይ ገደል ለዛሬ ፍንጣቂ ማስተዋል ቢልክልን
አምላኬ ምን አለበትም እላለሁ። የባዕዳን ግራሞት ጭብጥ፤ የእርስ በርስ ችግራችውን ዋጥ አድርገው በጋራ ቆመው ትንግርትን
ሰማዕታት ማዘከራቸው የህሊናችን ዳኛ ሆኖ እኛን ሊገራን ባለመቻሉ ግን የልቤ ክናድ ይዝላል። ነገ ሌላ ቀን ነውና ነገን
እንዲመርቅልን ህይወቱ ያላቸው አበው ሱባዬ ቢይዙበት ምኞቴና ናፍቆቴ ነው … አንደ ዕምነታቸው።

ዓለም ስለ ሴቶች ብቃት ብጣቂ እውቀት ባልነበረበት ጊዜ የኛው አፄ ኃያሉ ንጉሥ ሚኒሊክ ደማቸው - መንፈሳቸው - ሙሉዕ
ፈቃድ ሰጥቶ ተግባር ላይ የዋለ በኽረ ጉዳይ ነበር የሴቶች እኩልነት። ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት። ኢትዮጵያ ገድል ናት። ኢትዮጵያ
ዓለም - ዓቀፍ ህግ ናት። ኢትዮጵያ የቀደመች ሥልጡን
መምህርት ናት። በዘመኑ የጣሊያን ተጋፊነት፤ የኢትዮጵያ
ጥበበኛው መሪ የአፄ ሚኒሊክ አመራር ደግሞ ዕርቅና ሰላም
ፈላጊነት ዓለምን ያሰደመመ መረቅ ትውፊት ነበር። ምርኮኛን
ተንከባክቦና መርቶ ወደ ሀገሩ መሸኘትም አብነታዊ የአፄ
ሚኒልክ ልዑቅ በኽረ ተግባር ነበር። ዛሬ ያሉት ሰበነካዊ
ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች መሰረተ ጥንስስ ብቻ ሳይሆን ዓላማው
ቀድሞ ኢትዮጵያ መሬት ላይ በድርጊታ ላይ የዋለው
በድንቅነሽ አንባ ነበር - በብጡሎቹ።

ሀ. የእኩል ተሳትፎ ፈቃድ ... ለሴቶች።

የጣሊያን ከመቀሌ አልፎ መስፋፋትን መመረጡ
ያልተማቻቸው ንጉሥ ሚኒሊክ አልጋቸውን ለአጎታቸው ለራስ
ዳርጌ አደራ ሰጥተው፤ ረዳትም ደጃዝማች ኃይለማርያምንና
የወህኒ አዛዡን ወልደ ጻድቅን ጨምረው ሊነሱ ሲያስቡ
ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ አልለይም ሲሉ ሙሉ እምነትና
ፈቃድ ሰጡና እቴጌ ጣይቱ አብረው ዘመቱ። „ … ከጃንሆይ
ጋር እቴጌ ጣይቱ አልለይም ብለው ጦራቸውን ይዘው
ተጓዙ“ (ገጽ 100*) „ „ወንድ ያለ ዕለት - በዕለት፤ ሴት ባለ
በዓመት“ የሚለውን የሴቶችን መብት ደፍጣጭና ተጫኝ
ኮስኳሳ ብሂል ቅስሙን እንኩት አድርገው የአካላቸውን ክፋይ
የማይገሰስ ክብር ሰጥተው፤ ፈቃዳቸውንም ተንከባባክበውና
አልምተው የታሪክ ዐይነታ ታዳሚ አደረጉት። ዘመናቸውንም
ሙሉና ጌጣማ አደረጉት። የቀደመና የሰለጠነ መክሊት
ባላጸጋው የንጉሦች ንጉሥ አፄ ሚኒሊክ የተግባር ምሰሶና
ዋልታ ነበሩ ለሁለመናችን።

ለ. የጦር ጄኒራልነት፣ የአዋጊነት፣ የመሪነት፣ የአዝማችነት ጥንድ የእኩልነት ዕውቅና እና ዕሴቱ - ለሴቶች።

ዓለምዓቀፉ የቅኝ ግዛትን ቅስም የሰበሩት ክቡር አፄ ሚኒሊክ „ሴትና አህያ በዱላ“ የሚለውንም ሥነ - ቃል ጨፍልቀው ከጠላት
ጋር ለጦርነት ዐዲማህለያ ላይ በ10 ግንባር ካሰለፉት 30 ሺህ ጦር ውስጥ የልዕልታችን፤ የንግሥታችን የእመቤት ጣይቱ ግንባር
ከ3ሺህ ጦር ጋር አንዱ ግንባር ነበር። ይህ በዬትኛው የዓለም ታሪክና መዘክር የሚገኝ ጣዝማዊ ገቢር ነው። ማንም ሀገር እንዲህ
በዚያ ዘመን የተግባር ዲታ የሆነ የሴቶች የእኩልነት ታሪክ የለውም። አባታችን፤ መሪያችን፤ መኩሪያችንና ንጉሣችን አፄ ሚኒሊክ
ግን እኩልነትን የተቀበለ፤ እኩልነት በድርጊት ያዋለ፤ እኩልነትን ያከበረ - ያስከበረ - ያደመጠ፤ እኩልነትን በጥንግ ድርብ ካባ
ያንቆጠቆጠ የመኖራችን ልዩ የታሪክ ጉልላት እንዲያብብ ፈቀዱ።

ስለዚህ አፄ ሚኒሊክ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች ብቻም ሳይሆን ዓለምን በድርጊት ያስተማሩ ድንቅ የኢትዮጵያዊነት አንዱ ታላቅ
ሚስጢር ናቸው። ንጉሥ ሚኒሊክ ለሴቶች እንደ አደራጅነተቻው የክብር አባላችን ሰንደቃችን ናቸው።
ኃያሉ የአፍሪካ ቀንዲል ንጉሥ ሚኒሊክ የሴቶችን የብቃት ሚስጢር መንፈስ ቅዱስ ስላቀበላቸው ውጤቱ አዲስ የጥቁር
የማይደፈር የድል ፕላኔት ሆነ። በውጊያውም ሳይደክሙ እቴጌ ጣይቱ ከአካላቸው ጎን ሆኑ በፋመው ውጊያ ላይ “ ... በዚህ ጊዜ
ዐፄ ሚኒሊክ የጦር ወታደራቸውን በሚያበራታታ ቃል ሲያደፋፍሩ፤ እንዲሁም እቴጌ ጣይቱ እንደ ወንድ በጦርነቱ መካካል
እዬተላላፉ የቆሰለውን ሲያነሱ፤ ለተጠማው መጠጥ፤ ለተራበው ምግብ ሲሰጡ ዋሉ“* ይሉናል ሊቁ ጸሐፊ (ገጽ 110 )የተደራጀ
የቀይ መስቀል ተግባር በእናትነት ተፈጥሯዊ ክህሎት በቅሎ፤ በአጋርነት ጸድቆ፤ እንሆ ... ሚስጢር ይቀዳል ከድንቅነሽ አንባ ….
ከእግዚአብሄር በታች እኩልነታችን ያፀደቁ ብቸኛ መሪ፤ የእኩልነታችን መሸሸጊያ የልብ አድርስ እረኛ ፤ አስተዋሽ ጌታ ንጉሥ ሙሴ
አፄ ሚኒሊክ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar