torsdag 25. juli 2013

ዲሲ እንደጎረቤት የሚኖርበት


(ከታደለ መኩሪያ)
ከሐምሌ አንድ እስከ ሐምሌ ሰድስት 2013 እ ኤ አ፣ ለኢትዮጵያውያን ሰላሰኛውን ዓመት ለሚያከብረው የእግር ኳስ ውድድር በዲሲ ተገኝቼ ነበር። ይህ 
በዓል በኢሳት ተነግሮ ሰለነበር በዓለም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሣይቀር ዲሲን እንደ ቁለቤ ገብርኤል ልንሣለማት እንደ ድሬ ሼክሁሴን ሙዳ ልንላት ተገኝተናል። 
በአገራችን ከማንኛውም ክፍለሃገር ዛሬ ጎረቤት አገር ከተባለችው ኤርትራ ሣይቀር የሐረሩን የቁልቤ ገብርኤል የባሌውን ድሬ ሼክሁሴን እስላም ክርስቲያን 
ሳንል የዘር ሐረግ ሳንቆጥር በአንድነት በፍቅር አክብረን ነበር።
ከጹሑፌ እንደምትረዱት ከዲሲ አይደለሁም፤ ስለጉዞዬ ስለስፖርቱ 
ክንዋኔ ፤ ስለዲሲ ኗሪዎች፤ በቀደም ተከለተል በየአላችሁበት 
እንዲደርሳችሁ ይሁን። ከሃገር ከወጣሁ የ ESFNA ዕድሜ ያህል ነው፤ 
በቅርብ ከሃገር የወጣን ሰው አንዳንድ ነገር መጠየቃችሁ አይቀርም፤ 
አንድ ቀን የዳላሱን ዘመዴን ኢሊያሰን ሰለ አክስቱ ልጅ ጓደኛዬ ጠየኩት፤ 
‘አለማየሁ የደርግን እሥር ቤት ገፈት ቀማሹ’ ብሎ ጀመረ፤ ‘ከወረዳችን 
ተመርጦ ኢሣፓ ምስረታ ላይ የተገኘውን ተወካያችንን ከእውቶቢስ 
ሲወርድ ጠብቆ፤ እጆቻቸውን በመሳሳም ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ 
ወደ ሕዝቡ ዞር ብሎ ‘የፕሬዘዳንት መንግስቱ ኃይለ ማሪያምን እጅ 
የጨበጠውን የጓዱን እጅ፤ ስሜአለሁና የእኔን እጅ ከሳማችሁ 
የፕሬዘዳንቱን እጅ እንደሰማችሁ ይቆጠራል ፤ጓዱን አታስቸግሩት ይላቸዋል። ይህቺን ጹሑፍ ካነበባችሁ እንደ GPS ሣችሁ ዲሲ እንዳደረሳችሁ ቁጠሩት። 
እኔና ጓደኛዬ ከልጁና ሌላ ዘመዱ ጋር አይሮፕላን ላይ የወጣነው ከሴያትል ሲሆን መነሻችን ቫንኮበር ካናደ ነበር። ዲሲ ሬገን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ 
ስንደር ስልኬ ቀጨል አለች። ወደ ዲሲ መጣለሁ ካልኩኝ ጀምሮ ጓደኛዬ ሽመልስ ባለቤቱ አስቴር በየዕለቱ ጥሪያቸው አልተቋረጠም። ደርሻለሁ አልኩት፤ 
አናገረው አለኝ፤ ታናኝ ወንድሙ ኢሊያስ ነበር፤ ባለቤቱ አልመጣችም፤ ሁለት ልጆቹን ይዞ ከዳላስ እስከ ዲሲ እየነዳ መምጣቱን ነገረኝ።ልጆቹ ስፓርቱን 
እንዲያዩ ከዘመድ አዝማድ እንዲተዋወቁ እኔንም አባት እናቶቻቸውን እንጂ እነርሱን የማላውቃቸውን የዘመድ ልጆች ወልደው ከብደው በዲሰ የሚኖሩትን 
ሊያስተዋውቀኝ ዕቅዱ ሰለነበር ደስ አለኝ።
አብሮኝ ተጓዡ ጓደኛዬ መምጣት የለባቸውም መኪና ስለምንከራይ ማሪዎት ሆቴላችን ጠብቁን በላቸው አለኝ። የዲሲው መስተንግዶ ሊጀምር ነው። 
ከመኪናው ማከራያ የሚሰራ ኢትዮጵያዊ አገኘን። ሱፕርቮዘሩን በጎሪጥ እያየ ሰለሃገራችን ጫወታ ጀመርን፤ በሰው ሃገር ኖሮ ስለሃገር ቢያወሩት አይጠገብ። 
ከሌሎች ተጓዦቼ አስተዋውቄው ሻንጣችንን አግዞን ከተከራየና መኪና ስንደርስ የጓደኛ ልጅ በጇ ዶለሩን ጨበጥ አድርጋ ስትጉሽመው ተናነቁ፤ አባቷና እኔ 
እኛ ብንሆን አናስበውም ተባባልን፤ ‘በአደግንበት ባህል ለአንድ ወገናችን መልካም ስናደርግ እርሱም ለሌሎች ያንኑ እንደሚያደርግ ስለምናስብ ነው’ ስለው፤ 
‘ልንዝናና ነው የመጣነው ተወና!’ አለኝ። ለገዛህኝ አንድ ነገር ሣልነግረው ዘነጋሁ፤ ያች በዶለር ልትቦክስህ የሞከረችው ልጅ ፎቶዋ በኢትየጵያ አየር መንገድ 
ፖስተር ላይ ጉደሮ ወይም ደበሌ የነበረቸው ምጥጥየዋ ልጅ መሆኗን አልነገርኩትም።
ማሪዎት ሆቴል ስንደርስ ሽመልሰና ኢሊያስ በመዘግየታችን እሳተ ጎርሰው እሳት ልሰው አገኘናቸው። ‘ሦስተኛ ጊዜያችን ነው’ አሉ፤ ይህ ሁሉ የናፍቆት መሆኑ 
ገበኛ። እርቦናል፤ በጉዞው ምግብ አይቀርብም፤ something to drink እያለች አሣላፊዋ ውኃ ሰትግተን ነው የዋልነው። መጠጫዋ ደግሞ ፍንጃል የምታክል 
ጨው ወይም አንቆቆ መሸጫ ቀስቲር የምታክል፤ ቡናቸው ቁርስ የሌለው ፤ ‘አሜሪካንም ረሃብ ገባ እንዴ’ የሚያሰኝ! 
ሽመልስና ኢሊያስ ይህን የተራበ ባታሊዎን ከማሪዎት ሆቴል ብዙም ከማይርቀው የኢትዮጵያውያን ሬስቶራን እየመሩን ገባን። ከዚያንማ በኋላ የሆነውን 
እናንተው ገምቱ። የሚገርመው ሽመልስ ካለ ሒሣብ ሲባል አቅራቢዎቹ ተደርድረው ሒሣቡን ለእርሱ ነው የሚሰጡት፤ጋባዡ ሌላ ሰው ቢሆን እንኳን፤ 
እርሱ ግን በደስታ ይከፍለዋል፤ መደኃኒት ቀማሚ እንጂ ባንከር ነው ማን አንዳላቸው አይታወቅም። ሌላው ከሃገር ቤት ዞሮ ዲሲ የገባ ወሬ አለ ይባላል፤ 
ካናዳዎች ለቲብ ነፍጎች ናቸው ተብሎ ሃገር ቤት ተወርቷል የሚሉም አልጠፉም። ‘ይህ ማማሞቂያ ነው ድል ያለ ድግስ ከቤቴ እሁድ ተዘጋጅቶ 
ይጠብቃችኋል’ ብሎ ሒሣቡን ዘግቶ ሄደ። እኔም ሆቴል ብይዝም ከኢሊያስ እንደማንለያይ ያውቃል፤ ከሥራ ውጪም አብሮን ነው። ኢሊያስና እኔ ብዙ 
ሥራ ይጠብቀናል፤ ሲወለዱ እንኳን ሃገር ቤት ያልነበርኩት ዛሬ ዲሲ መጥተው ትዳር መሥርተው የሚኖሩት ሊያስተዋውቀኝ GPSን እያሰተካከለ 
የዋሽግተንን አስተዳደር ዞርነው፤ እንደወግ ላውራው፤ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አያቶቻችንን ከአጽመ ርስታቸው ያልቀነቋቸውን ዛሬ ምን ነካን የልጅ 
ልጆቻቸው እንደጨው ዘር ተበተን? መማራችን ጎዳን? ከመቃብር ተነስተው ቢያዩ ምን ይሉ? 
እኔና የቫንኮቨሩ ጓደኛዬ ከስፓርቱ ሥፍው ተገኘን፤ በሁለተኛው ቀን መሆኑ ነበር። ሁለታኝንም ወደ ኢሳት ድንኳን አመራን፤ ኢሳትን ከጀመረ ጀምሮ 
በቴክኒክ እውቀቱ በገንዘብ ማሰባሰብ ቶቦላ በመሸጥ ታከተኝ የማይለውን ኦሪዮን በኢሳት ድንኳን ልናገኘው ጎራ አልን። እሀት ከዳላስ ይሄኛው ከፖስተን 
እነዚህ ከዲሲ ብሎ አስተዋወቀን። ለኢሳት ዕቃዎችን በመሽጥ ጉድ ጉድ ሲሉ ተመልክተን ደስ አለን። ኦሪዎን ርቦት እንደሆን ለመገመት አንድ ከረጢት ቆሎ 
በአራት ዶሎር ገዝቼ ሰጠሁት፤ቆሎውን እንደቆሎ ቃመው። አንድ ኩንታል ገብስ በሶስት ብር ከአምሣ ሲሸጥ ነው ከሃገር የወጣሁት።ሁለተኛው ትኩረቴ 
የኢትዮጵያውያ ሴቶች ድንኳን ተክለዋል ማለትን ሰለሰማሁ ወደዚያ አመራሁ፤ ECADF የኢትዮጵያውያ ውቅታዊያ ጉደዮች መወያያ ማዕድ፤ ከኮፒተር 
ጀርባ በድምፅ፣ የማውቃቸውን በአካል ለመገናኘት ነበር፤ ድንኳኑ ተጥሎ ባገኘውም እኛ አይደለም አሉኝ። የኢሳት ና የሴቶች ድንኳን እንደምንገናኝ ፍንጭ 
ሰጥቼ ነበር፤ አልተሳካም።ዳላስ የተዋወኩት የእዚሁ የመወያያ ክፍል ተሳታፊ የሆነውን አገኘሁት፤ እርሱም እኔ የምፈልጋትን እህት ኖሯል የሚፈልገው 
እንደላገኛት ነገረኝ፤ እርሷን ካገኘናት ሌሎችን በዲሲ አካባቢ ያሉትን እናገኛቸዋለን ነበር ሐሣባችን፤ ብዙዎቹ ነባር የእዚህ መወያያ ክፍል ተካፋዮች ኢሳትን 
በመርዳት ሃገር ቤት ድረስ ዘልቀው ለወገኖች ዕርዳታ በማድረግ የታወቁ ናቸው። የሰሩትን በእዚች አጭር ጹሑፍ ገልጬ አልጨርሰውም፤ ግን ክፍሉ 
ከአፍ እስከ ገደፍ ጢም ይበል እንጂ ተግባሪያውያን በጣም ጥቂቶች ናቸው። የገንዘብ ሐብታሞች አይደሉም፤ አንዳንዶቹ ሥራቸውንም ገቢያቸውንም 
በግልጽ ይናገራሉ፤ ሆኖም የተግባርና የፀጋ ሐብታሞች ናቸው። እነዚህ ጥቂት ሰዎች በማንኛውም ቦታ ዕርዳ ለጋሾች ናቸው።በእጅ የሚቆጠር የገንዘብ 
ክምችት የላቸውም። በአንድ ወቅት የእዚህ ክፍል ቋሚ ተሳታፊና ቃለ መጠይቅ አቅራቢ ጋዜጠኛ ሞያዬ ምስክረ ለአንድ ፕሮፌሰር የሃገራችንን ጉዳይ 
አስመልታ ብዙ ጥያቄዎችን ካቀረበች በኋላ ‘የኢሳት የአምስት መቶ ብር ትኬት በመግዛት ይረዱናል? ስትል ጠየቀች፤ አምስት መቶ ብር የለኝም ነበር መልሱ፤ ይህን ክፍል የምወደው በአፍ ሸንግለው በሌላው ታታከው ዝናና ክብር ለሚመኙ የራስ ምታት ነው። በኦሮመኛ አንደ ተረት አለ ‘አፋን ጉዶ ሐረካን 
ጢቆ’ በአፉ ቸር በእጁ አይቸር ይላሉ።በቤሔር፣ በመደብ፣ በሃይማኖት፣ ክፍል ከፍተው ስለሃገር ተቆርቋሪ መስለው የሚያወሩ በዙዎች ናቸው፤ በተግባር 
ዜሮ። ይህ ሁኔታ በፖለቲካው በየስብሰባዎች በስፓርቱም ቢሆን ይጸባረቃል። በተለይ አስተናጋጆችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ 
ይኖርናቸዋ።በECADF ቋሚ ተሳታፊዎች ለዚህ ምሳሌ ናቸው።ቃልና ተግባር አብረው ካልሄዱ ሁሉም ነገር ከንቱ ይሆናል።ጓደኛዬ በስቲዲሙ ከተደረደሩት 
ሱቆች አረጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቲ ሸርቶች አይቶ ለመግዛት ሲያነሳው በትንሹ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እብድ የጫረው የሚመስል ነገር አየ። ‘ይህ አያቶችህ የሞቱለት 
ስንደቃ ዓለማ ነው ወይ?’ ብሎ ጠየቀ መልስ አልነበረም ፣በማግስቱ አስተካክሎ ኦርጂናሉን አመጣልን።
ስለጠቅላላው ዝግጅት ለመተቸት አንተ ማነህ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፤ እውነት ነው ካልመረጥህ አታማር ይላሉ፣ በዲሞክራሲውም አገር፣ ተሳትፎ 
ካላሳየህ ማለታቸው ነው። ለሰላሳ ዓመት ይህን ድርጅት እየወደቁም እየተነሱም እዚህ ያደረሱት አመራሮች ፣ ተጫዋቾች በየከተማው የሚኖረው ሕዝብ የነፃ 
አገልግሎት ሰጪዎች፤ የአሜሪካንም መንግሥት ሃገራችን የተነፈግነውን ነፃነት ያገኘንበት ሰለሆነ ሊመሰገን ይገባዋል። መረሳት የሌለበት እየኖርን ያለነው 
እንደቤታችን ሳይሆን እንደጎረቤት ነው። ብዙ ዓመት ተደራጅቶ ከኖረ ሕብረተሰብ እኩል ልኑር ሲባል ብዙ የሚያስከፍለው ዋጋ አለው። ምናልባት 
በገንዘብ እንጠግነዋለን ቤተሰብ በመመሥረት እንካሳለን በማለት ያንን ለሟሟላት ሽቅብቁልቁል እንላለን። የስፓርቱንም በዓል የዚያ አካል ነው።እንዲህ 
ከየአቅጣጫው ስንሰባሰብ መለያየታቸንንም አሰበን ነው፤ግን ተበታትነን እንደንቀር አሰተማማኙ ቦታ ሃገር መሆኑን አንርሳ። ESFNA የሰላሳ ዓመት ተመክሮ 
ያ እሲኪሆን አሰባስቦን እንደሚቆኝ አንጠራጠርም። በአሜሪካና በካናዳ ሰንት ፕሬዘዳንቱችና ጠቅላይ ሚነስተሮች በሕዝብ ምርጫ ተለውጠዋል። ምን 
ሰርተው አልፈዋልሐ ESFNA ማን ያውቃል የጨርቅ ኳስ የሚጫወቱት የሃገራችን ወጣቶች በቆዳ ኳስ ያጫውታቸው ይሆናል። ቆዳው እነደሆነ በሃገራችን 
የተተረፈረፈ ነው፤ ዛሬ ወቅቱ ባይፈቅድ ነገ ይሆናል በማለት ላልም፤ በአሜሪካና ካናዳ ከቤተሰብ አስተዳደር እስከ ሃገር አመራር በቢሊዮን የሚያቀሳቅሱ 
ድርጅቶች የአሰራር መሠረቱ አንድ ነው። ጉደዮች ሁሉ በወይይት ፣ በመደማመጥ ሐሣብን በሐሣብ በመሞገት፣ ይበራዩና ከዚያም ድምፅ ይሰጣል።፣ 
በድምፅ ያለፈውን ጉዳይ በተተለመለት መሠረት ሥራ ላይ ይውላል፤ የሚሠሩት ሁሉ በግልጽነት በሃላፊነት ለተጠያቂነት ዝገጁ በመሆን ስለሆነ እድገት አለ። 
ለምሳሌ ESFNA ይህን መንገድ ተከትሎ የተጓዘ ድርጅት ከሆነ እንኳስ ይህን የእስፓርት ድርጅት የሃገር መምራት ብቃት ይኖረዋል። በፍቃደኝነት የነፃ 
አገለግሎት ሊሆን ይችላል፤ ሳየው ትልቅ ሐላፊነት ነው፤ ገቢያቸውን አገናዝበው ቋሚ ሠራተኞች መቅጠር የግድ ሳይል አይቀርም።
ስለ ዲሲ ኗሪ ትንሽ ልበል፤ የዲሲን ሕዝብ ይሄ ነው ብዬ በነቂስ መናገር አልችልም። ቆሎው፣እንጀራው ቢራው ከሃገር ቤት ተከትሏቸው እንደመጣ 
ታዝቢአለሀ፤’ ዲሲ ፣ጋንዲ ተበሏል፤’ ‘ሴቱ ኢትዮጵያ አርግዞ የሚለደው ዲሲ ነው’ ነፍሱን ይማረውና ደራሲው አቤ ጎበኛው ‘ ‘አለወለድም’ በሃምሳዎቹ 
ዓመተ ምህረት የፃፈው ተዝ አለኝ። የሃገር ባለቤትነት የሚጠይቅ መሆኑ ነበር የገባኝ። ከዲሲ ስመለሰ ፕሮፌሰር መስፈን ወልደማሪያም ‘የሚወለዱበት ፣
የሚሞቱለትና የሚሞቱበት’ በሚል የፃፉትን ሳነብ አዘንኩ፤ሐዘኔ ልባቸው የቱን ያህል መድማቱን በማሰብ ነው።ጓደኛዬን የዲሲ ሰዎች ፈገግታ ተርባችኋል 
‘ስለው፣ ፈገግ ለማለት ከናፍሮቹ አልገለጥ አሉት፤ የኢሳት ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ተገኝቼ ነበር ፤‘ቀልድ ለበስ ቁምነገር ታማኝ ሲናገር ይስቃሉ ብዬ ገምቼ 
ነበር አለሆነም’፤ የዲሲ ኗሪ ለጡረታዬ ትንሽ ልሸቅል ብሎ፤ የአባይን ቦንድ የገዙ ኮንዲሚኒየም የተመዘገቡ አዲሰ አበባ ደርሰው ሲመለሱ ያላቸውን 
ፈገግታ በአባይ ወልዱ ኩርፊያ ለውጠውት ይመጣሉ። የሚገርምህ ሁኔታውን ይገነዘባሉ የምትላቸው ሁሉ በወያኔ ፕሮፓጋንዳ እንደ ገበቴ ወኃ ሲዋልሉና 
ታያለህ። ት ወለጋ ውስጥ ዶክተሮች በሽተኛ ገላችኋል ተብለው ወያኔ ወሕኒ ሲወረውራቸው እየሰሙ ሪፈራል referral ሆስቲታል አናቋቁማለን ብለው 
ከዲሲ አዲሰ አበባ ሲጓዙ ታያለህ፤
ሌላው በነፃ የሚለቀቀው ETV አስተወፆ አድርጓል ለኩርፊያው፣በቲቪው የምታያቸው ሁሉ ያኮረፉ ናቸው። ሃገር ቤትም ከወያኔ ሰዎች ጋር ቢዝነስ 
እንሰራለ ብለው ፈገግ ያሉትን በእኔ ነው የምትስቀው ተብለው ጥፊ የላሱም አልጠፉም። በፈገግታው የታወቀው ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ወዶም 
አላለቀሰም፤ ከጎራ ፈርዳ በአማራ ስም ሕዝብን ያፈናቀለውን ሽጉጤነ አላየህም በ ኢቲቪ ሲያለቅስ? በወያኔ ለቅሶ ለሾመት ተብሏ፣ ሻለቃ ኃይሌም ፕሬዚዳት 
ሌሆንልህ ነው አለኝ።
ዲሲን መሰናበቻዬ ሰለደረሰ በጥሪው መሠረት ከሽመልስና ከባለቤቱ አስቴር ግብዣ ላይ ከሲያትል የተጓዝነው በሙሉ ተገኘን። ኢሊያስ የነገረኝ ትዝ አለኝ 
ከሊሊ ቤት ባለቤቷና እርሷ ጋብዘውን በያነቱ ምግቡ መጠጡ ቀርቦ ሳለ ‘ኢትዮጵያውያ በስፖርት ስም በሚሰባሰቡበት አንድ ሰምንት ውስጥ የሚሸጠው 
የመጠጥ ገቢ በዳላስ ውስጥ በዓመት ውስጥ የሚሸጠውን ያህል ነው ብሎኝ ነበር። የሽመልስና የአስቴር ዝግጅት ያንን አጠናክሯል። ከመጠጡ ከምግቡ 
ግብዣ ላይ ከሃገር ቤትም የመጡ አናትም ስለነበሩ፤ቀደሞ እንዳልኩት ወላጆቻቸውን እነሱን የማላውቃቸው ስለነበሩ፣ስለኖርበት ሕብረተሰብ ብዙ 
ተጫውተናል፤ በኃይለሥላሴ ጊዜ የተሠሩ ትምህርት ቤቶች እየፈራረሱ ሰለሆነ በውጭ ያለን ገንዘብ ለማሰባሰብ ቅሰቀሳ ላይ ነበርን። አያቶቻችን አባቶቻችን 
በኦጋዴን ጠረፍ ከኢጣሌያ ከፈረሳይ ከኢንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች ተዋግተው በማቆየታቸው ምንም አስተዋፆ ባላደረጉ ክፍሎች ነፍጠኛ ቢባሉም፤ደንቁርናን 
ለማጥፋት በምናደርገው ጥረት የመፈለጉትን ይበሉን በማለት የተቻለንን በማድረግ በመጣር ላይ መሆናችንን ሐሣብ ለሐሣብ ለመለወወጥ አጋጣሚውን 
ተቀቅመንበታል። ለነፍጠኛ ባዮች ዛሬ ከአፅመ ርስታቸው ላይ የነቀላቸውን የበይ ተመልካች ያደረጋቸውን ለአረብ፣ ለየሕንድ፣ ለቻይና መሬት 
የሚቸበችበው የወያኔ ተወካይ ኦዴድ ኦሮሞ ነን ባዮች ትምህርት ቤት ሲያስገነቡ አላየንም። ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል አንድም 
ሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አልተሠራም፤ የነበሩትም እየፈረሱ ነው። ሕዝቡን በድነቁርና እስከወደኛው ተገዠ እንዲሆን የሚያደርጉት የወያኔን 
ተልኮ የተቀበሉ ኦሮሞ ነን ባዮች ናቸው። ዲሲ እንደስፖርቱ የውጪው ፖለቲካ መዓከል ናት። ለተቃዋሚ ደርጅቶች ከሰጠናቸው በላይ ታምር አንጠብቅ፤
መሪዎችም ቢሆኑ የረዳናቸውን ያህል እናውቃለን፤ ከረዳናቸውና ከአለው ተጨባጭ ሁኔታ በላይ ሰራን ቢሉን እንደዋሹን እንቆጥራለንና እወነቱን እየተናገሩ http://www.ethiomedia.com/2013report/dc_ende_gorebet.pdf
ይስሩ፤ ብሩሕ ዘመን እንዲመጣ በየመስኩ ለምትሰሩ እግዜር ይርዳችሁ።ኢትዮጵያ በልጆቿ በዓምላኳ ኃይል ተከብራ ትኑር! 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar