tirsdag 19. februar 2013

Tamagne

  ከጀርባ ሾኬ ባዮቹ እስከአሁን የተሳካላቸው አይመስለኝም ፡፡ ታማኝ ገና እግሩ ይደርስበታል በተባለው አገር ፣ ገና ከማለዳው ጀምረው ነበር በኢሜል የሰው ኮምፕዩተር ማንኳኳት የጀመሩት ፡፡ የቀቢጸ ተስፋ ሙከራቸው የትም አላደረሳቸውም ፡፡ ይበልጥ ሙቀት እንደተጠጋው ላስቲክ እየተጨራማመቱ ነው የቀሩት ፡፡ እጅግ የምናከብራቸው አንቱታን የተላበሱ ሰዎች ሳይቀር በሰዎች ኬሚስትሪ አለመግባባት ሰሞኑን   ኢሳት የተባለውን ተቋም ለመገርሰስና ለመሸርሸር አንዳንድ ቡድኖች ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም ፡፡  ኢትዮጵያኖች ጋሽ ዩሱፍ እንዳለው እንዲህ እንደአሁኑ ከተረባረብን- ኢሳትን- አልጀዚራ የማናደርግበት ምንም ምክንያት የለም ፡፡ ይህን ኢሳትን በተመለከት ብዙ ጊዜ ከወዳጆቼ ጭምር ሳይቀር የምንተራክበት ጊዜ ብዙ ነው ፡፡ ለኔ ኢሳት የብርሃኑ ነጋ ሆነ የአንዳርጋቸው ጉዳዬም አይደለ ፡፡ ኢሳት በአሁኑ ጊዜ እየሠራ ያለው ምንድነው ነው ትኩረቴ ፡፡ እንደ አይጋ ፎረምና እንደ ዋልታ ወይም ሬድዮ ፋና የግንቦት ሰባትን ሥራና ፕሮፓጋንዳ ብቻ የሚሰራ ከሆነ ያን ጊዜ እንጠያየቃለን ፡፡ ያን ጊዜ አባላቶችህ ይርዱህ ማለት እንችላለን ፡፡ አሁን ግን ኢሳት እየሠራ ያለው ከፓርቲዎች ወገነተኝነት ውጪ.. ሊጠቀሙበት የፈለጉ ሌሎች ፓርቲዎችን ጭምር እያገለገለ ነው ፡፡ 


  ለምሳሌ ከአንዴም ሁለት ጊዜ የኢህአፓን ከፍተኛ አመራር አባሎች ስለፓርቲያቸው ሁኔታ ለህዝብ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ እድል ሰጥቷል ፡፡ ለዶክተር አረጋዊም ሆነ ለሸንጎ መሪዎች እንዲሁ እድሉን ሰጥቷል ፡፡ ጉድለትና ሰንኮፍ ካለበት ደግሞ ኢንስቲትዩሽኑ ወይም ተቋሙ እንዳለ ሆኖ ድክመቱንና ችግሩን አሳይቶ ይበልጥ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እኩል እድሉን ሰጥቶ የኛ አልጀዚራ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በጓሮ በር አሉባልታ መንዛት ራስን ዝቅ ያደርጋል ፡፡ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ሳመራ-አንድ ነገር ስለታማኝ ልበል ፡፡ በአንድ አጋጣሚ ዋሽንግተን ዲሲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ ፣ የታማኝ ባለቤት ሶስት ወንዶች ልጆቹን አቁርባ ስትወጣ አየኋት ፡፡ በፈረንጅ አገር ልጆች የወለደ ሰው ጉዳዩን በቅርበት ይረዳል ፡፡ እንደ አገር ቤት ልጅ የብር ኳስ ሰጥቶ ሂድና ተራኩተህ ና !! የሚባልበት አገር አይደለም ፡፡ 

እያንዳንዷ ቀን ከልጆች ጋር ስፖርት፥ ኳስ፥ቲኒስ፥ ዳንስ እየተባለ ትንፋሽ የምታስጨርስ ነገር ናት ፡፡ በዚህ ላይ ቅዳሜና እሁድ የትምህርት ቤቶቻቸው ጓደኞች ልጆች ቤት ልደት እየተባለ የሚያልቀው ጊዜ ቀላል አይደለም ፡፡ይህን ሁሉ ጥሎ ከወር በላይ በየአህጉሩ መዞር - ለታማኝ ብቻ የእናት አባቱ እዳ አይደለም ፡፡ ከአሉባልታው በፊት ወሬ የሚያወሩ ሰዎች ! እኔ ይህንን የመሰለ ሥራ መሥራት እችላለሁ ወይ ብለው መጠየቅ አለባቸው ፡፡ በዚህ ቪድዮ ላይ ታማኝ የሚያዝገነዝበውን አቢይ ነገር መስማቱ ራስን እንድንፈትሽ ግድ ይላል ፡፡ በፖለቲካ ፓርቲ አባልነትም ሆነ መሪነት የሚኮፈሱ ሰዎችን ታማኝ ትልቅ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል  ውጡና ሥሩ ፡፡ ሠርታችሁ አሠሩ ፡፡ ህዝቡ የት ናችሁ እያለ ነው  ብሏል ፡፡ 

አዎ ብዙ ጊዜ ጭብጨባ አደገኛ ነው ፡፡ ታማኝ ደግሞ የዚህችን  ጭብጨባ ምንነት በሚገባ ስለተረዳት- ወደ ትዕቢት እንዳትወስደኝ ፈጣሪዬን እለምናለሁ ብሏል ፡፡ የሠራ ይጨበጨብለታል ፡፡ያልሰራ ደግሞ ራሱ ይንበጫበጫል ፡፡ ኖርዌይ ውስጥ ሌላ አገር የምናየው የሰዎች የኬሚስትሪ አለመግብባትና መናቆር እዚህ ግባ የማይባል ነው ፡፡ እዚህ ኖርዌይ የሚኖር ሰው ደግሞ ጭብጨባ የትም እንደማያደርስ ያውቃል  የአገር ቤት ጭቃ ሹምነትን እዚህ አሳዩኝ ማለት ከንቱነት ነው ፡፡ እዚህ በመንገድ ላይ ካርል ዮሃንም ሆነ ኦስሎ ሲቲ የዚህን አገር ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እየተጋፋ የሚሄድ ህብረተሰብ ባለበት አገር ፥ የሚያስከብረው ሥራ እንጂ ሹመት እንዳልሆነ ሁሉም ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡ ማጠቃለያው ! ስለዚህ ! ስለዚህ ኢሳት የህዝብ ጆሮና ልሳን ሆኖ እንዲዘልቅ ወገብን ጠበቅ አድርጎ ! ግመሎቹ ይጓዛሉ ውሾቹ ይጮሃሉ ብቻ ነው ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የታማኝን ቃል አድምጡና የአዋራ- አምባው ዳዊትን በኢሳት ላየ የተካሄደ ፕሮፓጋንዳ አፒታይቱ ካላችሁ ሄዳችሁ ጎብኙት 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar