mandag 4. februar 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ/(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎ

Respond to this post by replying above this line




jihad harakat
 
ማክሰኞ ኢቲቪ ድግስ አለበት
ክርስቲያኖችም ሙስሊሞችም ልባችሁን ጠብቁ
“እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ” የማስታወቂያው ፍንጣሪ ሃረግ ነው። በአብዛኛው የማህበራዊ ድረገጾች አስቀድመው የሚያስተላልፉት መልዕክት ደግሞ “ክርስቲያኑም ሙስሊሙም ልባችሁን ጠብቁ የሚል” ነው። ኢቲቪ ድግስ አለኝ ሲል ለማክሰኞ ቀጠሮ የያዘለት ዘጋቢ ፊልም አክራሪነት ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ቀደም ብሎ የተሰራጨው ማስታወቂያ ያስረዳል።
ከኢህአዴግ አፈጣጠርና የፕሮፓጋንዳ ልምዱ በመነሳት ለማክሰኞ በቀጠሮ የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም “አኬልዳማ ቁጥር ሁለት” በሚል ብዙዎች ሰይመውታል። አንዳንዶች ደግሞ “አዳዲስ ሆዳሞችን እንተዋወቃለን” ሲሉ ፊልሙ በደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ይገልጻሉ። “የውሸት አባት ኢህአዴግና ወዲ ስምዖን የቆመሩት ቁማር” ሲሉ የሚገልጹትም ጥቂት አይደሉም።
“ጂሃዳዊ ሃረከት” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ ዘጋቢ ፊልም ምንም ይሁን ምን ሙሉውን ለመመልከት ፍላጎት ያላቸው ትችቱ ባይቀድም ጥሩ ነው የሚል አቋምም እያራመዱ ነው “የአገራችን ጉዳይ የተወሳሰበ ነውና ልባችንን በመጠበቅ በጥበብ ነገሮችን ልንመረምር ይገባል” የሚል አስተያየት የለጠፉም አሉ። ብዙ እየተባለለት ያለው ይህ አዲስ ፊልም ከመውጣቱ በፊትና በኋላ በመላው አገሪቱ ያሉ ሙስሊሞች ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ፍቅር እንዲሰጡና ኢህአዴግ ሊፈጥረው ያሰበውን የጥርጣሬ አመለካከት መስበር እንደሚገባ ተዘግቧል።
ኦማር አል በሺር ኢሳያስን ሊጎበኙ ነው
(ፎቶ:xinhuanet.com)
ዓወት የተሰኘው ድረገጽ በ3/2/2013 ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመጎብኘት የሱዳኑ ኦማር አልበሽር አስመራ መግባታቸውን ዘግቧል። በሽር በመከላከያ ሚኒስትራቸውና በደህንነት ሃላፊያቸው ታጅበው ለጉብኝት ሲጓዙ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንደተለመደው በደህንነት ሃላፊያቸውና በመከላከያ ሚኒስትራቸው እንዳልታጀቡ ዓወት አስታውቃል። የስራ ጉብኝቱ ለአንድ ቀን እንደሆነም ተመልክቷል።
በኤርትራ አኩራፊ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስትርን በመቆጣጠር ህገመንግስታዊ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ በመሪ ደረጃ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ለመገናኘት ቀዳሚ የሆኑት ኦማር አል በሽር የመጀመሪያ መሆናቸውን የጠቆመው ዓወት ስለ ጉብኝቱ አበይት ጉዳይ አለው ነገር የለም። ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች በተመሳሳይ ውስጥ ችግር ውስጥ እንዳሉ ያመላከተው ዜና የሁለቱን ጎረቤት አገር መሪዎች የጋዳፊና የሙባረክ እጣፈንታ እንደሚጠብቃቸው አመልክቷል። የአልበሽር ያልተጠበቀ ግንኙነት የሱዳን ወዳጅና ጠበቃ ለሆነችው ኢትዮጵያ ምን እንደምታ ሊኖረው እንደሚችል በዘገባው አልተጠቆመም።
ዳቦ” አመጽ አክሱም ዩኒቨርስቲ ደረሰ
(ፎቶ: ከዩኒቨርሲቲው ድረገጽ)
ዩኒቨርስቲዎች በዳቦ አነሰ፣ ሩዝ ሰለቸን፣ ስጋ አልታኘክ አለን … ጥያቄ አድማ እየመቱ፣ ፖሊስም ወዲያው እየደረሰ ሲደቁሳቸው ጩኸታቸውን መስማት የተለመደ ነው። ይኼው የተለመደ የዳቦ አነሰ ጥያቄ “የተበላሸ የዳቦ ዱቄት” በሚል ተሻሽሎ አክሱም ዩኒቨርስቲ መድረሱን የዘገበው ሪፖርተር ነው። ጥያቄውን ያቀረቡት አስር ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው እንዲባረሩ መደረጉን ተከትሎ ያመጹት ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ ከተማ ሲወጡ አለመግባበት ተፈጥሮ ነበር።
ተማሪዎቹን አነጋግሮ የዘገበው ሪፖርትር፣ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ከተማ ተሰልፈው ሲወጡ ፖሊስ ጥይት ተኩሶባቸዋል። የደረሰው ጉዳት ባይገለጽም ተማሪዎቹ ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው፤ በርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። ከዳቦ ዱቄት መበላሸት ጥያቄ በስተቀር ከጀርባቸው ምንም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ እንደሌለ ያስታወቁት ተማሪዎች ጥያቄው የመልካም አስተዳደር ስለሆነ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት ለጥያቄያቸው መፍትሄ እንዲያፈላልግ ተማጽነዋል።
ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሲታደስ በሰዓት 20 ኪሜ “ይከንፋል”
(ፎቶ: ቢቢሲ)
የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ የኢትዮ ጅቡቲን የምድር ባቡር ድርጅት የሞተ፣ የማይጠቅም፣ መፍረስ አለበት በማለት መግለጻቸውን የሪፖርተር የፓርላማ ጋዜጠኛ ጽፏል። “የማይጠቅም ነገር ዝም ብለን ማንከባለል አይጠቅምም” በማለት ድርጅቱ እጣ ፈንታው መፍረስ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።
በሌላ በከል ለዚሁ መስመር እድሳት የተገኘ ገንዘብ ስራ ላይ ስለመዋሉ ተጠይቀው ሲመልሱ የባቡር መስመሩ ስራ እንዲጀምር በጅቡቲ በኩል ፍላጎት ስላለ ከድሬደዋ ጅቡቲ ያለው የባቡር መስመር ተጠግኖ ስራ እንዲጀምር ከስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል። በስምምነቱ መሰረት አሮጌዎቹ ባቡሮች ተጠግነው ስራ ሲጀምሩ ስለሚኖረው ሁለኔታ ሲያስረዱ “ባቡሮቹ ተጠግነው ስራ ሲጀምሩ የሚጓዙት በሰዓት 20 ኪሎሜትር ነው” ብለዋል። አክሳሪና በሙስና የተወሳሰበ ድርጅት እንደሆነ ሚኒስትሩ የገለጹት ይህ ተቋም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደሞዝ በማጣቱ ቀደም ባሉት ሚኒስትር ትዕዛዝ መሬት የማከራየት ስራ ይሰራ ነበር። በዓለማችን ፈጣን ተብለው ከአንድ እስከ አስር ደረጃ የተሰጣቸው ባቡሮች፤ አስረኛው በሰዓት 300ኪሜ አንደኛው ደግሞ 485 ኪሎሜትር ይጓዛል፡፡
የነጻ ሚዲያ ‘ፎቢያ
ቀደም ሲል የፍትህ ጋዜጣን በተልካሻ ምክንያቶች የዘጉት ክፍሎች በተመሳሳይ አዲስ ታይምስ መጽሔትን ከህትመት ውጪ አድርገዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህንኑ አስመልክቶ በተለያዩ ድረገጾች ላይ ባሰራጨው ጽሁፍ ውሳኔው ከአምባገነንነት እሳቤና ከጭፍን ፍርሃት እንደሚመነጭ አመልክቷል።
አገርቤት አገዛዙ አፍንጫ ስር በመሆን ኢህአዴግን በሰላ ብዕር በመተቸት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን አቶ መለስ ከአንድ ክፍለጦር በላይ የተለየ ሃሳብና ነጻ ሚዲያ እንደሚፈሩ ይናገራል። ወራሾቻቸውም ከእርሳቸው በባሰ አምባገነኖች እንደሆኑ ያመላከተው ተመስገን ለነጻ ሚዲያ ካላቸው ፍርሃቻ የተነሳ ጭፍን አምባገነን መሆናቸውን ገልጿል። ከዚህ አቋማቸው የተነሳ “አገሪቱን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየገፏት ነው” ብሏል፡፡
“የመለስ ራዕይ በአዲስ ራዕይ መጽሄት ተተገበረ” በሚል ርዕስ ተመስገን ባሰራጨው ጽሁፍ ለአዲስ ራዕይ መጽሄት መዘጋት የቀረቡት ሶስት ምክንያቶች ተራና ፍጹም ተልካሻ መሆናቸውን አንባቢ እንዲፈርድ በዝርዝር አስቀምጧል።
አስራት ጣሴ ሬድዋንን አወገዙ
(ፎቶ: የአስራት ጣሴ Facebook)
ለምርጫ ቦርድ ቅሬታቸውን አቅርበው መልስ ስላልተሰጣቸው ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉት 39 ፓርቲዎች ተወካይ አቶ አስራት ጣሴ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሬድዋን ሁሴንን አወገዙ። አቶ አስራት ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ማብራሪያ አቶ ሬድዋን ለመንግስት መገናኛዎች በሰጡት መግለጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ክብር ነክተዋል፤ ተሳድበዋል። ይህ ደግሞ “ከኢህአዴግ የሚጠበቅ አይደለም” ብለዋል። ከኢህአዴግ የሚጠበቀውን ስነስርዓት ግን አልጠቆሙም። እሳቸው አይግለጹት እንጂ ኢህአዴግ የሚምልበት የምርጫ ስነምግባር ኮድ ፓርቲዎችን ማውገዝን አጥብቆ ይከለክላል።
አቶ አስራት ጣሴ እንዳሉት “ብዙዎች ፓርቲዎች አባላትና ጽ/ቤት የላቸውም። በህይወት የሌሉና አንድ ሰው የሚመራቸው ናቸው” በማለት አቶ ሬድዋን የሰጡትን ቃለ ምልልስ ተከትሎ እሳቸው የሚያስተባብሯቸው ፓርቲዎች በህብረት የተቃውሞ መግለጫ አውጥተዋል። አብዛኞቹ ፓርቲዎች ከ1984 ዓም ጀምሮ እስካሁን የዘለቁና በርካታ ደጋፊ ያላቸው መሆኑንን ያመለከቱት አቶ አስራት፣ “ቢሮ ስንከራይ በዶዘር እስከመጥረግ ይደርሳል። አከራዮችን በማስፈራራት ያከላክላል” ሲሉ ኢህአዴግን ይከሳሉ። በማያያዝም ኢህአዴግ የፓርቲዎች ደራጃ መዳቢ መሆኑንን አውግዘዋል። ድርጊቱ ፓርቲዎችን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት እቅድ ለመኖሩ ማስረጃ እንደሆነ አመልክተዋል።
የታፈኑት ተማሪዎች የት ደረሱ?”

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar