mandag 11. februar 2013

“ማህበረ ቅዱሳንን” ያያችሁ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል


ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል | February 8th, 2013
በአንድም በሌላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ተከታይ ሆኖ ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ ነፍሰ ገዳይ ሳለ መንፈሳዊ ጭምብል አጥልቆ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሆነ ንዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሳቅርሶች ከዬ ገዳማቱና አድባራቱ እያደነ ከመዝረፍና ከመመዝበር አንስቶ ለዓላማው ያልተንበረከኩ ሊቃነ ጳጳሳት: ካህናትና ዲያቆናት በማሳደድና ነፍስ እስከ መግደል ድረስም የተሰማራ የጥቁር ራስ ስብስብ መሰሪ ድርጅት የማያውቅ ሰው ይኖራል የሚል እምነት የለኝም፡፡
በእርግጥ ማህበሩ በመላ ሀገሪቱ ባሰማራቸው ለዓመታት በስለላ የሰለጠኑ  አባላቱና በተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ቦታዎች የተቀመጡ ግለሰቦች ጭምር በመጠቀም “ማህበረ ቅዱሳን የተቃቃመው ጥንታዊትና ሐዋሪያዊት የሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ስርዓተ አምልኮ ለትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡ ዓላማውም አበው ትተውልን ያለፉት ትውፊት፡ ደንብና ስርዓት ጠብቆ ማስጠበቅ ነው።”  ሲሉ በነጋ በጠባ ቁጥር ሳይታክቱ እንዲለፍፉ በማድረግ በሰራውና እሁንም ድረስ እየሰራው ባለ ፕሮፖጋንዳ “ማህበረ ቅዱሳን” ሲባል “ብዙዎቻችን” የምናወቀው ሃጢአት የማያውቃቸው፡ ቅዱሳን፡ ንጹሐንና የመላእክት ዘር ያለባቸው ንኡዳን አድርገን በመቁጥር ነው። እንግዲህ ይሄው ቀኑ ደረሰና “የቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ትውፊት ጠብቆ ለማስጠበቅ የቆምኩ መንፈሳዊ ማህበር ነኝ” እያለ ሕዝብ ሲያደኖቅር ዓመታት ያስቆጠረ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎች እየፈጸሙት ላለው ጥፋት ይሄው ጭራሽ መራጭና አስመራጭ ሆኖ በመሪ ተዋናይነት ተሰልፎ ሽርጉድ እያለ ይገኛል። (ስም ማጥፋት ወይንም  ደግሞ ተራ ውንጀላ አይደለም እየተባለ ያለው ለማረጋገጥ ከተፈለገ የሚቀጥለውን ሊንክ በመጨቆን እውነቱን  ሊያረጋግጡ ይችላሉ። http://www.ethiotube.net/video/24565/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Church-to-elect-its-6th-Patriarch-on-February-28--February-7-2013)

ውድ አንባቢ! በእርስዎ ቤት “ስርዓት መጠበቅ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቃሉም እንዴት እንደሚተረጉሙት እርግጠኛ ባልሆነም በበኩሌ ግን፡
ስርዓት መጠበቅ ማለት ስርዓት ማፍረስ ከሆነ፤
ስርዓት መጠበቅ ማለት ቀነኖ መጠስ ከሆነ፤
ስርዓት መጠበቅ ማለት የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት ማለት ከሆነ፤
ስርዓት መጠበቅ ማለት እንዳሻህ መሆን ከሆነ፤
ስርዓት መጠበቅ ማለት ለሕግ አለመገዛት ማለት ከሆነ፤
ስርዓት መጠበቅ ማለት የወደድከውን ማድረግ ማለት ከሆነ ቀድሞውንስ ትውፊት አክባሪ ስርዓት ጠባቂ/ጠበቃ ብሎ ማህበር ማቋቋም ለምን አስፈለገ? ብዬ እጠይቆት ዘንድ ግድ ብሎኛል። መቼም ስርዓት ሲጣስ፡ ቀኖና ሲፈርስና የአበው ትውፊት ሲዘነጋ የሕግ ያለህ! በማለት “ስርዓት ለመጠበቅ፤ የአበው ሐዋሪያዊ ግብር ለመዘከር እንዲሁም የቅዱሳን ትውፊት ለትውልድ ለማስተላለፍ የቆምኩ ነኝ ባይ ማህበር “ማህበረ ቅዱሳንን ያያችሁ!” በማለት ጮክ ብዬ ስጮክ አብረውኝ “ማህበረ ቅዱሳንን” ፍለጋ ለመውጣታቸው አልጠራጠርም፡፡ ነገሩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የመታደግ ጉዳይ ነውና!
“ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ እቺ ቤተ ክርስቲያን  ድሮ ድምጥማጥዋ ጠፍታ ነበር” ለምትሉ ተሳላሚዎች “ቤተ ክርስቲያን” ከዚህም በላይ መበጣጠስ ነበረባት/አለባት ከሆነ ቁጭታችሁ “አልተሳሳታችሁም” ከማለት ውጭ በመላእክት ቋንቋም ቢሆን መግባባት ስለማንችል ፍርዱ ለአንባቢ ትቸዋለሁ።
በተረፈ ይህ ሀገር የመበተን እንዲሁም ትውልድን የማኮላሸት ልዩ ተልኦኮ ይዞ የተነሳ ማህበር በየትኛው ህገ ደንብና  ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሰረት ፓትሪያሪክ ለመሾም በሚቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለና እንደገባም ሌላ አዲስ አባባ በሚገኘው የክፋት ሁሉ ማከፋፈያ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አከባቢ የነገሰውን ስርዓት አልበኝነትና የተንሰራፋውን የውንብድና ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነጥብ ቢኖር እንደው ስንዴውንና እንክርዳዱ መለየት ያቃተው ብዙሐኑ ሕዝብ በሚገባው መልኩ ለመግለጽ ተሞከረ እንጅ “ማህበረ ቅዱሳን” ዛሬ ይህን ቢያደርግ በግሌ ምንም የሚደንቀኝ አይደለም፡፡ እያደረገው ያለው ሁሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ለማፈራረስ ይዞት የተነሳውን ዓላማ አንዱ ክፍል በመሆኑ ሲፈለግ በትክክለኛ ስፍራው መገኘቱ ለመግለጽ እወዳለሁ። ይህን ሲያደርግ ደግሞ በፓትሪያሪክ መርቆሬዎስ ለሚመራው በውጭው ዓለም ለሚገኘው  ጉባኤ እያተላለፈው ያለው መልእክትም ኣንስተዋለን የሚል እምነት የለኝም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar