Why this ad?
Learn Norwegian Online - norwegiancourse.no/online - Learn Norwegian online with our state of the art e-learning tool.

Print all
In new window

digging for truth one nation ,and one country ethiopia
Inbox
x

DIGGING FOR TRUTH ONE NATION AND ONE COUNTRY ETHIOPIA noreply@blogger.com via google.com 
20:26 (2 minutes ago)
to me
Images are not displayed. Display images below - Always display images from noreply@blogger.com

digging for truth one nation ,and one country ethiopia



Posted: 06 Feb 2

Posted by |February 6, 2013|
                                                                                                                             
አቶ ገብረመድህን እርአያ

Gebremedhin Araya former TPLFህወሃት ከጥንሥሱ ጀምሮ እንደተልዕኮ እና መመሪያው ለዘመናት ከብዙ የውጭ ወረራዎች እና ያልተሳኩ የቅኝ ግዛት ጥረቶች በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት ለማፍረስ ፤ ህዝብን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የቋንቋ እና የዘር ልዩነት ከፋፍሎ ለብቻው የትግራይን ሪፖብሊክ ለማቋቋም ፤ ኤርትራን መገንጠል ፤ ትግራይን ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነጻ ማውጣት ፤ ኢትዮጵያ የምትባል በአጼ ምኒሊክ የተፈጠረችን አገር ከአለም ካርታ ላይ ማጥፋት ፤ የሚሉ እና ሌሎች ዝርዝር ግቦችን እና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ድርጅት እንደነበር ባለፉት በርካታ አመታት እኔ በግሌ ስገልጽ እና ሳስረዳ ህወሃትም አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግብር ይህንን እኩይ ምግባሩን ሲያሳየን ቆይቷል:: ይኸው ኢትዮጵያዊነትን ከፊት በመሆን ከውጪ ወራሪዎች በጽናት ተጋድሎ አቆይቷል ብሎ የሚወነጅለውን የአማራ ብሄርን የተመቸው ሲመስለው ከ1971 አንስቶ በቀጥታ በሰሜን ጎንደር በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጸለምት እንዲሁም በሚቆጣጠራቸው የትግራይ ቦታዎች እንዳደረገው በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ፤ ሳይመቸው ሲቀር ደግሞ በተላላኪዎቹ አማካይነት በጉራ ፈርዳ እንዳደረገው ከአካባቢው አማራን የማጽዳት ስራ ሲያደርግ ይኸው ብዙ አመታት ተቆጠሩ::

ወያኔ ህወሃት የደርግ ስርዓት መዳከምን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዮች መገጣጠም ጋር ተያይዞ በተፈጠረለት እጅግ አሳዛኝ ታሪካዊ ኹነቶች ታግዞ በ1983 ዓ.ም. አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ቻለ:: በደደቢት ተቀፍቅፎ በሽምቅ ጥቃት የሚቆጣጠረውን ግዛት በተለያየ ጊዜ እያሰፋ የመጣው ህወሃት በገባባቸው እና አንድ ፣ አንድ ጊዜም ተቆጣጥሮ በሚቆይባቸው ቦታዎች በዋናነት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የመንግስትን ካዝና ማራገፍ እና መዝረፍ ነበር:: የዚህ ዘረፋ ዋና አስተባባሪ እና ተቆጣጣሪም ስብሓት ነጋ ነበር::

 ከስብሓት ጋርም ዘረፋውን ያቀናጁ የነበሩት አርከበ እቁባይ ፣ አባይ ፀሃየ እና ሟቹ ክንፈ ገብረመድህን የነበሩ ሲሆን ፤ ዘረፋውን ከላይ ሆኖ በስብሓት በኩል ያዝ እና ይቆጣጠር የነበረው ደግሞ መለስ ዜናዊ እንደነበር በበረሃ በነበርኩበት ወቅት በተለያዩ አጋጣሚዎች የማየት እና በቅርበት የመታዘብ የታሪክ አጋጣሚ ነበረኝ:: ህወሃት በወርሃ ግንቦት 1983 ዓ.ም. አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ወታደራዊ ቁጥጥር እና የማረጋጋት ስራን ከመስራት ጎን ለጎን በገንዝብ ሚኒስቴር ጠቅላይ ግምጃ ቤት ፣ በንግድ ባንክ እና በብሄራዊ ባንክ የነበረውን ገንዘብ በጠቅላላው በማጋዝ በሚኒሊክ ቤተመንግስት አስቀመጠ:: እንደወርቅ ያሉ በአይነት የተቀመጡ እና በገንዘብ ሊተመን የማይችል እጅግ ብዙ ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ቅርሳ ቅርሶችንም ሰብስቦ በዚሁ በቤተመንግስት በጊዜያዊነት ባሰናዳው የዘረፋ ጣቢያ ላይ አከማቸ::

ከማዕከላዊው ባንክ ግምጃ ቤት ተጭኖ ወደዚሁ የዘረፋ ማከማቻ የተወሰደው ወደ 800 ኪ.ግ. የሚመዝን ወርቅ የዘረፋውን ትልቅነት እንደማሳያ ሊጠቀስ የሚችል ነው:: በግንቦት መጨረሻ ሳምንት አዲስ አበባን ተቆጣጥረው ለቀጣይ ሁለት ወራት የተደራጀ እና ከፍተኛ የዘረፋ ስራ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በቤተመንግስት ያስቀመጡትን እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብን ጨምሮ በአይነት የተደለደሉ እጅግ ብዙ ብር የሚያውጡ ብርቅ መአድናት እና ቅርሳቅሶችን በአውሮፕላን እና በመኪና በመጫን ወደ ትግራይ አጓጓዙ:: እንግዲህ ለድርቅ የተመደበ እርጥባንን ከደሃ ጉሮሮ በማህበረ ረድኤት ትግራይ — ማረት በኩል በመንጠቅ እና በተከታታይም የህወሃት ጦር በገባበት ከተማ እንደዚህ በተደራጀ የዘረፋ ስራ የአገር እና የመንግስትን ግምጃ ቤት በማራቆት በተገኘ ገንዘብ ነው በ እንግሊዘኛው ምጽአረ ቃል ኢፈርት(EFFORT) በትግሪኛ ደግሞ ት.እ.ም.ት. ወይም ትካል እግሪ ምትኻል ትግራይን ለቀጣይ የተደራጀ ዘረፋ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ያቋቋሙት::

ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የተቋቋሙት መሰቦ ሲሚንቶ ፣ አልመዳ ጨረቃጨርቅ ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ፣ ኢዛና ማይኒንግ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ ወጋገን ባንክ ጨምሮ እስከ ቱሪስት አስጎብኚ እና መጽሃፍ ችርቻሮ የደረሰ የንግድ እና የዘረፋ መዋቅር የተዘረጋው በጠራራ ጸሃይ በተደረገ ዘረፋ እና ኋላ ላይ ያለ ማስያዣ ከሃገሪቱ የመንግስት ባንኮች በብድር ስም በሚወጣ ገንዘብ እንደመሆኑ እነኚህ ኩባንያዎች የሁሉም ኢትዮጵያውያን ንብረቶች መሆናቸው በፍጹም ሊዘነጋ የማይገባው ሃቅ ነው::

ለነገሩ እነ ስብሓት ነጋ በተለይ በረሃ በነበሩበት ወቅት የተለያዩ ከተማዎችን ወርረው ሲቆጣጠሩ ይዘርፉ እና ያዘርፉ የነበረው የመንግስትን ንብረት ብቻም አልነበረም:: መጠኑ ይነስ እንጂ ድርጅቱ መሰሪ የሆነ አላማዬን አይደግፉም ፣ ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድነት አላቸው ፣ በኤርትራ ጥያቄ ላይ ከህወሃት ሃሳብ ጋር አይስማሙም ብለው የመደቧቸውን ንጹሃን ዜጎችን የተለያየ ስም በመስጠት እና በመወንጀል በሃለዋ ወያኔ(ስውር እስር ቤቶች) በመወርወር ንብረታቸውን ይወርሱ ነበር:: እነኚህ ዜጎች መጨረሻቸው በተለያዩ ጊዜያት ከነኚህ እስር ቤቶች ውስጥ በመውጣት መረሸን ነበር:: ስብሓት ነጋ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢፈርት በኢትዮጵያ ሃብታሙ ድርጅት እንደሆነ እና ህወሃትም ያለ ምንም ማፈር ‘ኢፈርት መር ኢኮኖሚ’ እየገነባ እንደሆነ ነግሮናል:: በተለያየ ጊዜ በዘረፋ የሰበሰቡት እና ያከማቹት ሃብት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አስበውት ይሁን አዳልጧቸው ከሚነግሩን ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ሊል ይገባል::

እነሆ ላለፉት 22 አመታት ማዕከላዊ መንግስቱን ተቆጣጥሮ ያለው ይህ የአጥፊ ወሮበሎች ቡድን በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ሲፈጠር ጀምሮ አጠንጥኖ የመጣውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲሰራ ሲመቸው በይፋ በህዝብ መገናኛ ብዙሃን ትዕቢት በተቀላቀለው ድንፋታ ሳይመቸው ሲቀር ደግሞ በተጠማዘዘ እና ግራ በገባው የፖለቲካ ፍልስፍና በማደንዘዝ እና ግራ በማጋባት ሲሰራ ኖሯል::

 ዛሬ ፣ ዛሬ ደግሞ በበረሃ ጀምሮ በተጋነነ ፣ ተጠምዝዞ በተተረጎመ እና አንድ ፣ አንድ ጊዜም ከሜዳ ተጠፍጥፎ በተሰራ የሃሰት እና ክህደት ሸፍጥ ሲያጠቁት እና ሲያንኳስሱ የኖሩትን የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አዲስ እንጽፋለን ብለው በስብሓት ነጋ በኩል በይፋ ማወጅ ጀምረዋል:: የህወሃት መሪዎች አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በ1993ቱ ክፍፍል ከስልጣን የተባረሩትም ጭምር በተለያዩ ጊዜያት ይህን በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ያደባ የታሪክ ክለሳ እና እንደ አዲስ የመጻፍ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ሃሳባቸውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ዋና አቀንቃኝም ሆነው ሰብከዋል::

 እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ያቺ አገር እና በወቅቱ የነበሩ መንግስታት ብዙ አፍሪካዊያን በጭለማ በሚኖሩበት ዘመን እንደ ዜጋ በሰጧቸው በጎ እድል ተምረው ሰው መሆን የቻሉ የትግራይ ምሁራን ፍጹም ምሁራዊ እና የዜግነት ሃላፊነታቸውን በወያኔያዊ ዘረኝነት እና ሆዳቸው ለውጠው የዚሁ እኩይ ምግባር አይዞህ ባይ ፣ ምሁራዊ ድጋፍ ሰጪ እና አንዳንድ ጊዜም ፊታውራሪ ሆነው መገኛታቸው ነው:: ከሃገር ውጪ ሆነው አንዳንዶቹም ሃገር ቤት ገብተው ለዚህ እኩይ አላማ ከተሰለፉ ምሁር ተብዬ ዜጎች ውስጥ ዶ/ር ገብሩ ታረቀ ፣ ዶ/ር ሰለሞን እንቋይ ፣ ዶ/ር አሳየኸኝ ደስታ ፣ ጎርፉ ገብረመድህን ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኪሮስ ፣ ዶ/ር ክንደያ ገ/ሂወት ናቸው:: ዛሬ ፣ ዛሬ ካሸነፈ ጋር ያደሩ መስሎዋቸው ህሊናቸውን ሸጠው በክህደት ቢኖሩም ነገሮች ዞር ያሉ ለት ለትውልድም ሆነ ለህሊናቸው ምን መልስ ሊሰጡ እንደሚችሉ ያሰቡበትም አይመስልም::

የኢትዮጵያ ታሪክ ፍጹም ጥልቀት ያለው እና በአመዛኙ እምብዛም መከራከሪያ ሳይቀርብበት በግልጽ ባሉና በጽሁፍ ተመዝግበው በተቀመጡ ድራሳናት ፣ ቅርሳ ቅርሶች ፣ እና መዛግብት አስረጂነት ሊጠና የሚችል እና እስካሁንም በተለይ በውጪ የታሪክ አጥኚዎች በመጽህፋ መልክ በብዛት የተጻፈበት ነው:: ይህንን ታሪክ አጣሞ ለመተርጎም እና እነ ስብሓት ነጋ እንደሚሉት እንደ አዲስ ለመጻፍ መነሳት መሞከር ሊሳካ የማይችል ነገር ግን ብዙ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል የመጨረሻው የጥቃት ሙከራ ነው::

በታሪክ ኹነቶች ላይ በታሪክ ምሁራን በኩል ደረጃውን የጠበቀ እና ጥብቅ የሆኑ ሳይንሳዊ መንገዶችን በመከተል የትርጓሜ ክርክር ማንሳት ይቻላል:: የተከሰቱ የታሪክ እውነታዎችን በመካድ ታሪክን እንደፖለቲካ ማጥቂያ መሳሪያነት ለመጠቀም መሞከር ግን እጅግ ከፍተኛ መዘዝ አለው:: መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ መቶ አመት ነው ብሎ በይፋ በተናገረ ጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያውያን በይፋ በምርጫ ካርዳቸው የሱን ዘረኛነት አንፈልግም ወግድ ባሉት የምርጫ 97 ማግስት አይኑን በጨው አጥቦ ኑና ሚሊኒየም እናክብር ያለው ክስተት መቼም የሚረሳ አይደለም::

የኢትዮጵያ ታሪክ የሶስት ሺህ አመት ታሪክ ነው ሲባል ዝም ብሎ በአፈታሪክ ወይም በዘልማድ የሚነገር ነገር ሆኖ አይደለም:: የግዛት ስፋቱ ይጥበብም ይስፋ የአገራችን ታሪክ 3000 አመት ለመሆኑ የሚያሳዩ የተለያዩ ማስረጃዎች በመኖራቸው ነው:: ይህንን ሃቅ ለመካድ መነሳት እንደነ መለስ እና ስብሓት እኩይ አላማ አርግዞ የመጣ ቡድን ወይንም ጭልጥ ብሎ አእምሮውን የሳተ ሰው መሆን አለበት:: በውጭ አገራት በፖርቹጋል ፣ ግብጽ ፣ እስራኤል ፣ ጣልያን ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን ፣ እና ስፔይንን ጨምሮ በብዙ አገራት የአገራችንን የተለያዩ ዘመናት ታሪክ ሊያሳዩ እና ሊይስረዱ የሚችሉ የታሪክ መዛግብት እና ማስረጃዎች ይገኛሉ::

ዛሬ ፣ ዛሬ የኢትዮጵያ ማዕከሉን በዘር እና በሃይማኖት ከፋፍሎ ከመታ እና ካዳከመ በኋላ በዝርዝር ሌሎችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወደማጥቃት በስፋት ተሰማርቷል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓትርያርክ አንስቶ ሌላ መሰየም:: የተሰየሙትም በእግዚያብሄር ቁጣ ሲወሰዱ ሌላ ለመሾም ድራማ መስራት ፣ ኢትዮጵያዊ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን የእምነት ትምህርት በካድሬዎች ለመጻፍ መሞከር አማኒያኑም እምቢ ሲሉም መግደል ፣ ማሰር እና ማንገላታት የዚሁ ታሪክን የማበላሸት እና እንደ አዲስ የመጻፍ ዘመቻ መገለጫ ኹነቶች ናቸው:: ዛሬ ላይ በዋልድባ ገዳማት ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ዝም ብሎ በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም ይልቁንስ ቀደም ብሎ ታቅዶበት በሂደት እየተተገበረ ያለው ታሪክን የማጥፋት እና የመደለዝ ዘመቻው አካል እንጂ::

ወያኔ ታሪክን ልክ እንደ አዲስ ከዜሮ ከሃዲው መለስ እና ሌሎች የወያኔ ጀሌዎችን ጀግና ነገር ግን ስለ እውነት እና ነጻነት ሲሉ የተዋደቁ እና የተሰዉ ሰማእት አባቶቻችንን ደግሞ ፈሪ እና ከሃዲ አድርጎ የመጻፍ ዘመቻውን ወያኔ ከሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን እና አሁን አሁን በብዛት እየተጻፉ ከሚወጡ እርባና ቢስ መጻህፍት መረዳት ይቻላል::ወያኔ በኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብት አምጥቼያለሁ ይለናል:: ውሸት! የሆነው እና እየሆነ ያለው አገሪቷን በዘር ከፋፍሎ ሲያበቃ እነኚሁ መብት አምጥቼላችኋለሁ የሚላቸው ብሄሮች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን እያካሄደባቸው ይገኛል::

ወያኔ ግዙፉን የደርግ ሰራዊት ደምስሼ ኢትዮጵያን ነጻ አውጥቻለሁ ይለናል:: ቅጥፈት!! የሆነው እና እውነታው ሌላ ነው:: ትክክለኛ የታሪክ ተንታኝ ከአንድ ብሄር በተውጣጣ እና በአብዛኛው ዜጎችን የማይወክል ይልቁንም ታሪካቸውን የሚሰድብ እና የሚያንቋሽሽ ፖለቲካ ይዞ በመጣ የመርዘኞች ቡድን የኢትዮጵያ ጦር ተሸነፈ ብሎ መቀበል ፍጹም ስህተት ይሆናል:: ለኢትዮጵያ ጦር መሸነፍ በወቅቱ የነበረው የከሰረ የኮሚኒስት ስርዓት መላሸቅ እና የፖለቲካ ስርዓቱ ከቀዝቃዛው ጦርነት መዳከም ጋር ተባብሮ የእዝ ሰንሰለቱ በመላላቱ ያስከተለው የመዋጋት መንፈስ መቀዝቀዝ አይነተኛ እና ወሳኙን ሚና ተጫውቷል:: አንዳንዶች በወቅቱ በወያኔ መሪዎች የተሰጠውን ቃል አምነው ለጊዜውም ቢሆን እስቲ እንያቸው በሚል ካሳደሩት ዛሬ ላይ እንደ ታላቅ ስህተት ሊቆጠር የሚችል የፖለቲካ ስሌት ስህተት በቀር ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ወያኔን መጣብን እንጂ መጣልን ብሎትም አያውቅ::

ሌላው የወያኔ አይን ያወጣ የታሪክ ሽምጠጣ አንድ አንዶች ህገ አራዊት ብለው የሚጠሩት እና ሟቹ እኩይ መለስ ዜናዊ እንደ ማወናበጃ የሚጠቀምበት ህገመንግስት ነው:: ወያኔ ሲዘብት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስደናቂ እና ነጻነቱን ያጎናጸፈ ህገመንግስት አመጣን ይለናል:: ሓሰት!! ህገ መንግስቱ በውስጥ ከያዛቸው አንቀጾች በመለስ አላማው ምን እንደሆነ እነሆ ከረቀቀበት የዘጠናዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ምን ማለት እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እየኖረበት አይቶታል እና ዝርዝር ማብራሪያ ውስጥ መግባት አያሻኝም::

ሲመጻደቅ ደግሞ ኢትዮጵያን ከመበታተን አዳናት ይለናል:: ክህደት!! ስብሓት ነጋ ሲያዳልጠው ኢትዮጵያን አፍርሰን እንደ አዲስ እየሰራናት ነው ይልና ማን አፍራሽ እና በታኝ እንደሆነ ሳያውቀው ይነግረናል:: ወያኔ እንዳሰበው ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ጽናት እና እምነት አገራችን እስካሁን በአንድነት ቆይታለች:: ይብላኝላቸው ለእነሱ እንጂ ከወያኔ ውድቀት እና ሞት በኋላም አንድነቷን ጠብቃ ትቀጥላለች::

ሲላቸው ደግሞ የአክሱም ታሪክ የጥቂት የትግራይ አካባቢዎች ታሪክ ነው ይሉናል:: ሙሉውን ትግራይ እንኳን አያጠቃልልም ሲሉም በድፍረት ይነግሩናል::ጉድ ነው!! ምን አይነት ማህጸን ይሆን እንደዚህ አይነት ከሃዲዎችን የወለደች?? በአንድ አገር ታሪክ ውስጥ አይነቱ ይለያይ እንጂ በታሪክ አጋጣሚ አሁን በማሊ እንደምናያቸው እና እንደአፍጋኒስታኑ ታሊባን አይነት ከተጠማዘዘ የሃይማኖት ፍልስፍና ተነስተው አገራዊ ጥፋት የሚያደርሱ ቡድኖች ስልጣን ሊይዙ ይችላሉ:: እንደ ወያኔ አይነት ግን ከአንድ አካባቢ ተቧድነው መጥተው በዚህ የመረጃ እና የእውቀት ዘመን ለክህደት እና ለጥፋት የሚተጉ ቡድን ግን አንብቤም ሆነ ሰምቼ አላውቅም:: የአክሱም ታሪክ የመላው ኢትዮጵያውያን ታሪክ ነው:: እንደዘመኑ እና ጊዜው የተፈጸሙ ታሪኮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሁሉንም የአካባቢውን ማህበረሰቦች መንካታቸው እስካልቀረ ድረስ ታሪኩ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሊኮሩበት ሊወያዩበት እና ሊማሩበት የሚገባ የጋራ ታሪክ ነው::

ህዝባዊ ወያነ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው ጥቃት እንደ ዮዲት ጉዲት እና አህመድ ግራኝ በአጭር ጊዜ ባይሆንም ላለፉት አርባ አመታት ገደማ ከበረሃ ጀምሮ በኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና እና ቅርስ ላይ ያደረገውን ጥቃት ስናይ ሁለቱ ካደረሱት መጠነ ሰፊ ጥቃት ጉዳቱ ይበልጥ እንጂ አያንስም::

የህወሃት ጥንሥሥ የጀመረው በ1964 በቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ በሻዕቢያ “ጥሩምቡሌነት” (“ጥሩምቡሌ” ማለት በቀድሞ አነጋገር በገንዘብ የተገዛ ቅጥረኛ ባንዳ እንደ ማለት ነው::) በተሰባሰቡ የትግራይ ዘረኞች ነበር:: ሻዕቢያ ለራሱ እኩይ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ጥቂት ዘረኞችን ሰብስቦ ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ ማህበረ ገስገስቲ ብሄረ ትግራይን ፈጠረ:: የድርጅቱን ከጥንስሡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት መነሳት የኔን ምስክርነት ማንበቡ ብቻ በቂ አይሆንም:: በአንድ አንድ ድረ ገጾች ላይ እና በኢንተርኔት በቀላሉ ሊገኝ የሚችለውን የድርጅቱን የ1968 ፕሮግራም ማየቱ ብቻ በቂ ነው::

ህወሃት በቀላሉ ሊደልዛቸው እና ሊያጠፋቸው የማይችላቸውን ከፍተኛ የአገር ክህደት እና የጅምላ ግድያ ወንጀሎችን የግል መዛግብቶቼን አመሳክሬ እዘረዝራለሁኝ:: አንባቢያን ዝርዝሩ ያለቅደም ተከተል መቀመጡን ልብ ይበሉ፤

  1. ገና ከመመስረቱ ብዙም እድሜ ሳያስቆጥር በ1968 ንጹሃን የትግራይ ልጆችን ሲለው ኢዲዩ ሲያሰኘው ደግሞ በኢህአፓ እና በደርግነት እየወነጀለ በጅምላ ፈጃቸው:: አባወራ እና እማወራዎችን በመግደል ብቻም አላበቃም:: የብዙሃንንም ንብረት በመውረስ ቀሪ ቤተሰባቸውንም ጭምር ነው አይቀጡ ቅጣት የቀጣው:: ብዙሃን ህጻናትንም ያለወላጅ ፤አረጋዊያንንም ያለጧሪ እና ቀባሪ አስቀራቸው:: ይህ በትግራይ በስፋት የሚታወቅ ሃቅ በመሆኑ በዘመኑ የወያነ ጉጅሌ ጦር ይንቀሳቀስ በነበረባቸው ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን በመጠየቅ ማንም ሊረዳው የሚችለው ሃቅ ነው::

  2.  

  3. በወርሃ ህዳር 1969 ዓ.ም. ከህወሃት አመራር ተወክለው መለስ ዜናዊ እና አባይ ጸሃየ ከሻዕቢያ ጋር አሁን አወዛጋቢ ተብለው የሚነገርላቸውን ከባድመ ጀምሮ እስከ የአፋር አካባቢዎች ድረስ ያሉ ቦታዎችን አሳልፈው የሰጡ መሆናቸው እና ከብዙ አመታት በኋላም ይህንኑ መዘዝ ተከትሎ በተነሳ ጦርነት ከመቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ያለቁበት ሁኔታ እና የጉዳዩም እስከአሁን ሳይቋጭ በእንጥልጥል መቆየት ማንም ሊዘነጋው የማይገባው ሃቅ ነው:: ህወሃት ይህንን አገር የመሸጥ ስራውን ይሰራ የነበረው ገና በደፈጣ ውጊያ ላይ በነበረበት ጊዜ እና በትግራይ ህዝብ ጭምር ምንም አይነት ተቀባይነትም ሆነ ውክልና ሳይኖረው መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል::

  4.  

  5. በ1968 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ህንፍሽፍሽ ተነሳ በማለት አመራሩ የተምቤን : እንደርታ : አዲግራት : ክልተ አውላሎ : ራያ : በትንሹም ቢሆን በአክሱም እና አድዋ ከነበሩ ታጋዮች ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ገድለዋል:: ለዚሁም ምስክር አሁን በህይወት ያሉ ታጋዮች እና ህዝቡ እማኝ ነው:: በየአካባቢውም ማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉ የጅምላ መቃብሮችን ጭምር ማሳየት ይቻላል::

  6.  

  7. በ1969 በወርሃ ህዳር በወልቃይት ጠገዴ : ዳንሻ : ጠለምት : ሁመራ : እንዲሁም ከወሎ አካባቢውን ከተወላጆች በማጽዳት የትግራይ መሬት ነው በማለት በካርታ ቀላቅሎ አስታወቀ::

  8.  

  9. በ1971 ዓ.ም. የህወሃት አንደኛ ጉባዔ አንስቶ የድርጅቱ አመራር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የአማራው ገዢ መሳሪያ ነች በማለት የጥቃት በትሩን መዘርጋቱን ተያያዘው:: ይህ እኩይ ትንተናው ከኮሚኒስታዊ የፖለቲካ ፍልስፍናው ጋር ተጣምሮ በፈጠረው የተወላገደ ስነልቦና እየተመራ በብዙ አብያት ክርስቲያናት ላይ እና ገዳማት ላይ የዘረፋ እና የጥቃት እጁን ሰነዘረ:: ለዘመናት የኖሩ የሃይማኖቱን ትውፊት እና ባህላዊ እሴቶችን ማህበረሰቡን በማስገደድ ከለከለ:: ክርስትና ማንሳት እና ሰርግ ማድረግን ጭምር:: ቀሳውስትን በግልጽ ማጥቃት እና ቤተ እምነቶችንም ማርከስ እና መዝረፍ የሰርክ ግብሩ አደረገው::

  10.  

  11. በ1972 ጥቅምት ወር ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ የወያነ ህወሃት የዘር ማጽዳት ስራ አማራ ጸረ ትግራይ ነው በሚል ይፋዊ መፈክር ታጅቦ ከህጻን እስከ ሽማግሌ ድረስ ተፈጸመባቸው:: ቤተሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በላያቸው ላይ እየተዘጋ እሳት ተለቀቀባቸው::

  12.  

  13. በ1970 ዓ.ም. ህወሃት በሚቆጣጠራቸው ነጻ መሬቶች ይኖሩ የነበሩ አማሮች ዘራቸው እየተቆጠሩ ተገደሉ:: ንብረታቸውም ተወረሰ:: አማራ በተገኘበት ቦታ ሁሉ እንዲገደል በይፋ አዋጅ ተላለፈ:: ብዙሃን አማራ ስለሆኑ ብቻ ተፈጁ::

  14.  

  15. በ1970 ዓ.ም. ኢህአፓ ከትግራይ ለቆ እንዲወጣ የህወሃት አመራር አዋጅ አስተላለፈ:: የኋላ፣ ኋላ ላይም ኢህአፓ በትግራይ ኢትዮጵያዊነት ላይና በኤርትራ ጥያቄ ላይ ያለውን አቋም እንዲለውጥ ለማስገደድ ቢሞክሩም አሻፈረኝ በማለቱ ሻዕቢያ እና ወያነ ግንባር ፈጥረው የኢህአፓን ጦር ደመሰሱ::

  16.  

  17. በ1970 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ በብስራት አማረ የሚመራ በቁጥር ወደ ሃምሳ ገደማ የሚሆኑ ታጋዮች ኤርትራ ውስጥ በሻዕቢያ አማካይነት የፈዳይነት ስልጠና ወስደው በተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ውስጥ ሰርገው በመግባት የህወሃትን እኩይ አላማ የማይደግፉ ንጹሃንን እና የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ ሌሎች ዜጎችን በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጁ::

  18.  

  19. በህዳር ወር 1968 ዓ.ም. የህወሃት አመራር ከነሰራዊታቸው የግንባር ገደሊ ሃርነት ትግራይ ታጋዮችን(ይህ ድርጅት በጊዜው በግብርም ሆነ በአላማ ከህወሃት እምብዛም የማይለያይ ድርጅት ሲሆን ብዙም በትግል ሳይቆይ በህወሃት የተደመሰሰ ድርጅት ነው::) በሙሉ በጸረ ዲሞክራሲያዊ ባህሪያቸው በአንዲት ለሊት ዘገልባ ጎጥ ውስጥ በጅምላ ፈጇቸው::

  20.  

  21. በ1977 በትግራይ የደረሰውን አስከፊ ድርቅ ተከትሎ በለጋሽ አገራት እና ህዝቦች ዘንድ ለነብስ አድንት ተብሎ የተላከውን እርጥባን የህወሃት አመራር በጥሬ ገንዘብ የመጣውን በቀጥታ ወደግል ካዝናቸው በአይነት የተለገሰውን ደግሞ በሱዳን ገበያ በመቸብቸብ ለትጥቅ መግዣ እና ለግል ሃብት አዋሉት:: እርዳታ ተላከለት የተባለው ምስኪን ህዝብም በየበረሃው ወድቆ ረገፈ::

  22.  

  23.  ለመለመኛ ለታሰበ ድራማ ወደሱዳን እንዲሰደድ በህወሃት የታዘዘው ረሃብተኛም በየመንዱ ቀረ:: የትግራይ ህዝብም ታሪክ ሊረሳው የማይገባው ታላቅ ክህደት ከአብራኩ ወጣሁ በሚሉ ከሃዲዎች ተፈጸመበት::

  24.  

  25. በ1981 ዓ.ም. ደርግ ትግራይን ለቆ እንደወጣ ህወሃት ካለምንም ችግር በሩ የተከፈተ ቤት በማግኘቱ ሰተት ብሎ መሃል ትግራይ ገባ:: ገብቶም አላረፈም:: በየከተማው ይኖሩ የነበሩ መምህራንን እንዲሁም የመንግስት ተቀጣሪ ዜጎችን ጠላት ብሎ በደርግ ደጋፊነት በመወንጀል ለቅሞ ፈጃቸው:: ከየአውራጃው ብዙ ሰዎች መገደላቸውን በቀላሉ ማጣራት ይቻላል::

  26.  

  27. ህወሃት በበረሃ በነበረበት ወቅት ከሻዕቢያ ጋር በነበረው ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን የማጥቃት የጋራ ውል የትግራይ ወጣት ሴት እና ወንዶችን ሻዕቢያን ለማጠናከር በተለያዩ ጊዜያት በባርነት አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ይህም የትግራይን ልጆች ወደማያውቁት ጦርነት አሳልፎ የመማገድ ዘመቻ ይፈጸም የነበረው በአስገዳጅነት እንደነበር እሙን ነው::

  28.  

  29.  ከ1969-1970 ዓ.ም. ብቻ በቁጥር ወደ 29,000 የሚገመቱ የትግራይ ወጣቶችን ለሻዕቢያ አላማ ማስፈጸሚያ አሳልፎ ሰጥቷል:: የቀይ ኮከብ ዘመቻ እንደተጀመረ የህወሃት አመራር ከዚህ በፊት ያደረገው ሳይበቃው ከ1971-1974 ዓ.ም. ተጨማሪ በቁጥር ወደ 70,000 የሚደርሱ የትግራይ ልጆችን በደርግ ጥቃት የውድቀት ገደል ላይ የደረሰውን ሻዕቢያን ለማዳን በቀጥታ በሻዕቢያ እዝ ስር አዘመተ::ይህም ሳይበቃው ቀይ ኮከብ ዘመቻ በተፋፋመበት ወቅት በ8 ብርጌድ የተደራጁ በቁጥር 13,500 የሚደርሱ ተጨማሪ የትግራይ ወጣቶችን ለሻዕቢያ ህልውና ማስጠበቂያነት ለጭዳነት ላከ:: እነዚህ ሁሉ በማያውቁት እና ይልቁንም አገራቸውን ለሚጎዳ ጦርነት በባንዳነት ህወሃት አሰልፎ የላካቸው የትግራይ ወጣቶች ደም በየበረሃው መና ሆኖ ቀረ::

  30.  

  31.   በጠቅላላው ህወሃት ለወሬ ነጋሪነት እንኳን ያልተመለሱ በቁጥር ከ112,500 በላይ የትግራይ ልጆችን ለሻዕቢያ ጦርነት ማጠናከሪያ እንደላከ ማስረጃ አለ:: አንዳንዶችም ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችል የሚናገሩ አሉ:: ይህ ነው እንግዲህ ትግራይን ነጻ አወጣለሁ የሚለን የነ ስብሓት እና መለስ ጉጅሌ የተሸከመው እና እንዲሰማ የማይፈልገው ጥቁር ታሪክ::

  32.  

  33. በ1981 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በየካቲት ወር በሱዳን ካርቱም መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂን አነጋግረው እንደምን ስልጣን እና አገሪቷን ከደርግ ውድቀት በኋላ እንደሚያስተዳድሩ አደላድለው ሲያበቁ ለወያነ ከሃዲዎች ኢትዮጵያን አመቻቸተው አሳልፈው ሰጧት::

  34.  

  35. ከደርግ መዳከም ጋር ተያይዞ የአገሪቷ አራቱም ማዕዘናት ክፍት በመሆናቸው ህወሃት ከመቀሌ ተነስቶ ካለምንም ችግር አዲስ አበባ ሊገባ ቻለ:: ከሽሬ ተነስቶ በጎንደር: በባህርዳር በኩል አድርጎ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ::

  36.  

  37.  ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሰራውን ወንጀል በዝርዝር ለማቅረብ ይሄ ጽሁፍ ብቻ በቂ አይደለም:: ስፍር ቁጥር የሌለው የአገር ክህደት እና የዘር ማጥፋት ስራዎች በተለያዩ ቦታዎች በሚኖሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሟል:: በተለያዩ ቦታዎች በአማራዎች ላይ ፣ በጋምቤላ በአኝዋኮች ላይ ፣ በአዋሳ በሲዳማዎች ፣ በኦጋዴን በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ላይ እንዲሁም በመላ አገሪቱ ባሉ እስር ቤቶችን ታጉረው በሚማቅቁ በ10,000 የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ላይ እስከ ዘር ማጥፋት(genocide) ደረጃ የሚደርስ ወንጀል ፈጽሟል:: አሁንም እየፈጸመ ነው::

  38.  

  39.  በተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደተገለጸው ህወሃት በበረሃ በነበረበት ወቅት በአሜሪካን መንግስት በሽብር ድርጊቱ እንደ አል ቃኢዳ አሸባሪ ድርጅት ተደርጎ ይታይ እንደነበር ወጣቱ ጋዜጠኛ አበበ ገላይ ከግሎባል ቴረሪዝም ዳታ ቤዝ(Global Terrorism Database) ላይ አሳይቶናል:: ይህንን መረጃ ማየት ለሚፈልግም ሰው ከኢንተርኔት ላይ ማግኘት ይችላል::

የህወሃት ጥቁር ታሪክ እንግዲህ ይህ ነው:: የእነ መለስ ዜናዊ ፖለቲካ እና አመራር በበረሃም ሆነ በከተማ ይህ ነበር:: ታሪክ ዳቦ ሆኖ አንበላውም ከሚል እጅግ አሳናፊ እና መሰሪ ትንተና ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ የማንቋሸሽ እና የማጨማለቅ ስራ የህወሃት ዋንኛ የፕሮፖጋንዳ ግብ እንደነበር እና አሁንም እንደሆነ ከአፋቸው የሚወጣውን ንግግር በመስማት መገንዘብ ይቻላል:: እነኚህ ናቸው እንግዲህ አማራን እና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እናጠፋለን ከሚል ጀምሮ ኢትዮጵያን አፍርሰን እንሰራለን እና ታሪኳንም እንደ አዲስ እንጽፋለን የሚሉን::

የስርዓቱ ዋና አንቀሳቃሽ መለስ ዜናዊ በሞት ተቀስፎ ከሄደ እነሆ ወራት ተቆጠሩ:: ሊታረቅ በማይችል የክህደት ቁልቁለት ውስጥ ያለው ህወሃትም ፍጹም ሊመልሳቸው በማይችላቸው ታሪካዊ ጥያቄዎች ተወጥሮ የውጪ ነብስ ፤ ግቢ ነብስ ግብግብ ላይ ይገኛል:: የድርጅቱ እኩይ አላማ እና ግቡ ዛሬ ፍንትው ብሎ በወጣበት ወቅት ላይ ኢትዮጵያውያን በመላ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ እስላም ፣ ክርስቲያን ሳይሉና አላስፈላጊ አተካራቸውን ወደጎን በማለት ይህንን የታሪክ አሽክላ የሆን ዘረኛ ቡድን ከስረ መሰረቱ ነቅለው መጣያ ጊዜው አሁን ነው:: በስቃይ ያሉ ወገኖቻችንን እና አገራችንን ከወያኔ መንጋጋ እናላቅ:: የሀገራችንን እና ህዝባችንን በጎ ታሪክ እና መጻኢ እድልም እናስመልስ::

ገብረመድህን አርአያ

የካቲት 2005


Filed in: Amharic Posts