ፍኖተ ነፃነት
… በሰሜን ጐንደር ልዩ ቦታው ድጐማ በሚባል ስፍራ ባለ በለስ ምንጭ ላይ በመንግስት ባለስልጣናት እና በህዝቡ መካከል ከፍተኛ ግጭት ተፈጠረ፡፡ በተጠቀሰው በለስ ምንጭ ላይ ለመስኖ በሚል መንግስት 1.3 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ለነዋሪው እየሰራ እንዳለ ከዞኑና ከወረዳው ባለስልጣናት ቢነገርም አሁን ግን ምንጩን ውሃ አሽገው ለሚሸጡ የግል ባለሃብት መሸጡ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም የተነሳ በህዝቡና በፖሊስ መካከል ታህሣሥ 4 እና 5 ቀን 2005 ዓ.ም የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ታውቋል፡፡
ከነዋሪው ህዝብ መካከል ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዲገነፅ ያልእንደገለፁልን ከሆነ ቦታው ከ500 በላይ አባወራዎች የሚጠቀሙበት ምንጭና የሰይፍ አጥራ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እኛን ሳያማክሩን ሳይነግሩን ለባለሃብት ሸጠዋል፤ ሌላው ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ የችግኝ ጣቢያ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ነው ሲሉ የግጭቱን ምክንያት አስረድተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት 15 ያህል ሰዎች መታሰራቸውና ሌሎችንም ለማሰር እንደታሰበ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡
ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የወረዳው አስተዳደር አቶ ግዛት አንተነህ በበኩላቸው የበለስ ወንዝ ምንጭን ለባለሃብቱ ፈቃድ የክልሉ ማዕድንና ኤነርጂ ቢሮ ነው፣ የተሰጠውም የመንግስት መሬት ነው እንጂ እኛ ህዝብ የሚጠቀምበትን አልነካንም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዕለቱ ግጭት የቀሰቀሱትም ህገወጥ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች በመሆናቸው ታስረዋል፤ ገና ሌሎችም በቁጥጥር ስር የሚውሉ አሉ ሲሉ ነግረውናል፡፡
በተያያዘ ዜና በጐንደር ዙሪያ ወረዳ በምትገኘው ማክሰኚት ከተማ የኢህአዴ ግን “አዲስ ራዕይ” የተሰኘ መፅሔት የአቶ መለስ ታሪክ የያዘ ነው በሚል አንዱን በ100 ብር ዋጋ በአካባቢው ቢሰራጭም ገዥ እንዳልተገኘ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት ታህሣሥ 27 ቀን 2005 ዓ.ም የወረዳው ርዕሳነ መምህራን ተሰባስበው ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በአካባቢው ገዥ ያጡት የመለስ ታሪክ ያለበት “አዲስ ራዕይ” በት/ቤቶች በጀት እንዲገዛ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ ይህንንም ለማጣራት ወደ ወረዳው ትምህርት ቢሮ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡
http://www.zehabesha

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar