tirsdag 22. januar 2013

ሰበር ዜና: በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ተካሄደ



ኢ.ኤም.ኤፍ. – የኤርትራ መከላከያ ሰራዊተ በዛሬው እለት (ሰኞ 21 ጃንዋሪ) በፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ መፈንቅለ-መንግስት ማድረጉን ኢ.ኤም. ኤፍ. ከአስመራ በስልክ አረጋግጧል:: ሰራዊቱ በአሁን ሰዓት ማስታወቂያ ሚኒስትሩን የተቆጣጠረ ሲሆን እስካሁን ምንም አይነት ደም መፋሰስ እንደሌለ ዘጋቢያችን ገልጿል::

ኢሳያስ አፈወርቂ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም::

ምንጮች እንደሚሉት ኢሳያስ አፈወርቂ ለስራ ጉብኝት ምጽዋ ሲሆኑ ከአስመራ-ምጽዋ የሚወስደው መንገድም በወታደሮች ዝግ ሆኗል::

ወታደሮቹ በተለይ የኤርትራ ጋዜጠኞች ምንም እንቅስቃሴ እንዳያድርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ጋዜጠኛዋ የኢሳያስ አፈወርቂ ልጅም እንደታገተች ተገልጿል::

እንደ ሪፖርተራችን ዘገባ ህዝቡ እንዲረጋጋነ እቤቱ እንዲቀመጥ ሰራዊቱ እየተናገረ ሲሆን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሙሉ ተቋርጠዋል::

ምንም ደም መፋሰስ ሳይኖር ማስታወቂያ ሚ/ርን እስከመቆጣጠር መድረስ ያልተለመደ መፈንቅለ-መንግስት ነው::

የአፍሪካ ጥናት አኤክስፐርት የሆነው ማርቲን ፕላውት ዲፕሎማቲክ ምንጮችን በመጥቀስ መፈንቅለ መንግስት እየተካሄደ መሆኑን በድረ-ገጹ ጽፏል:: ከፈረንሳዩ ኤ.ኤፍ.ፒ. በስተቀር አለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዜናውን አልዘገቡትም::

ዝርዝር ዘገባውን እየተከታተልን እናቀርባለን::

http://ethioforum.org/

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar