በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል። |
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar