fredag 18. januar 2013
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅፅ 1 ፣ ቁጥር 10
ችግር በፈጠረው አስተሳሰብ፣ ችግሩን መፍታት አይቻልም!
ያለፉትን 50 እና 60 ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ታሪክ በአንክሮ የተከታተለ ሰው በውል እንደሚረዳው፣ 'የኢትዮጵያ
አውራ ችግር መደባዊና ብሔራዊ ጭቆናዎች ናቸው፣' የሚለውና ድምፅ ያልተቆጠረበት ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ቀለም-ቀመስ ትውልድ የገዛ
አስተሳሰብ እንደነበር ይረዳል። ገዥው መደብና ጨቋኙ ብሔርም 'ዐማራ' እንደሆነ ያላንዳች ማመንታት እንደ ደረቅ ሃቅ የተወሰደ መሆኑን
ያጤናል። ይህን አባባል ከመቀበል አልፈው ፣ ዐማራውን ለማደን በመጀመሪያው ረድፍ ተሰልፈው ፣ መሣሪያ መልጠው ፣ ጎራዴ መዝዘው
፣ 'ዱርቤቴ' ፣ ያሉት እኒሁ አባቶቻቸው 'በገዥነትና በጨቋኝ ብሔርነት' የተፈረጁት የዐማራው ልጆች እንደነበሩም ይገነዘባል። ዐማራን
ለማጥፋት በታቀደው ዘመቻ ግንባር ቀደም ሆኖ 'ዐማራን የማጥላላት' ዘመቻውን 'ሀ' ብሎ ያስጀመረው 'ዋለልኝ መኮንን' የተባለው ወጣት
የያኔው የቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበር። ዋለልኝ መኮንን ከዐማራው ልጆች መካከል ‘እንደ ጠማማ የመጥረቢያ እጀታ ሆኖ
በማገልገል’ ሆኖ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የገዛ ወገኖቹ በዘረኞች እንዲጨፈጨፉ ጥርጊያ መንገዱን ከፍቷል። በመሆኑም የዐማራው
የመጀመሪያ ጠላቱ ራሱ ዐማራው መሆኑንም ከድርጊቱ ይረዳል። ይህ 'ማንነትን የመሸሽ እና የሌሎች ጀሌ የመሆን አባዜ' ዛሬም የዐማራው
ቀለም-ቀመስ ትውልድ ‘ባለህበት ሂድ’ ከመሆን ያልወጣ የዝንጉነት ደዌ እንደሆነም ልብ ይላል። በአንፃሩ ደግሞ አክራሪ ብሔርተኞች
'ዐማራው ጨቋኝ ብሔር ነው፤ የኢትዮጵያ አንድነት የተመሠረተው በዐማራው የበላይነት በኃይል ነው፤ ዐማራው የሌሎች ነገዶችንና
ጎሣዎችን ባህል ፣ ቋንቋ ፣ ታሪክ ፣ እምነትና ማንነት አጥፍቷል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እየተባለ የሚነገረው ውሸት ነው፤ ሕዝቡ
የታሪክ ፣ የባህል ፣ የቋንቋና የሥነ-ልቦና አንድነት የለውም፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር "የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት፤" ኢትዮጵያዊነት
ዐማራው በሌሎች ላይ የጫነው ዕዳ ነው፤' በማለት የራሳቸውን ማንነት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ልዩነት ላይ መሥርተውና ተደራጅተው፤
‘የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ነው’ ባሉት የዐማራ ነገድ ላይ በትጥቅ የታገዘ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሣ የዘር ማጥፋት ጦርነት
ከከፈቱበት በትንሹ ከአርባ ዓመታት በላይ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል።
ከእኒህ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት በዘር ከተደራጁት ድርጅቶች መካከል ሻዕቢያ ፣ ሕወሓት ፣ ኦነግና በኦሮሞ ስም
የተቋቋሙት ከስምንት የማያንሱ ድርጅቶች ፤ እንዲሁም በሶማሌ ፣ በአፋር ፣ በጉራጌ ፣ በሐዲያ ፣ በከንባታ ፣ በሲዳማ እና በሌሎችም
ነገዶችና ጎሣዎች 'ነፃ አውጪነት' ስም የተደራጁት ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ ደርጅቶች ፣ ሁሉም ማለት ይቻላል 'ጠላታችን ዐማራው ነው '
ብለው የተነሱ መሆኑ የታወቀና በተግባርም እየታዬ ያለ ሕያው እንቅስቃሴ እንደሆነ ማንም ያጣዋል አይባልም። የፖለቲካ
ፕሮግራማቸውና ተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው ሳይዛነፍ የሚናገረው ይኸንኑ ዕውነታ ነው። ስለዚህ የሌሎች ነገዶች ልሂቃን ዐማራን
ለማጥፋት ሲያሤሩ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት የማያንስ ጊዜ አስቆጥረዋል ቢባል ከሃቁ አይርቅም። የብሔርተኛ ድርጅቶች መሪዎች ዐማራውን
'በጨቋኝ ብሔርተኝነት' ፈርጀው ብቻውን አቁመው ለመቅጣት የዐቅም ውሱንነት እንዳለባቸው ሲረዱ ሌላ አጋዥ ኃይል ማግኘት
እንዳለባቸው ተገነዘቡ። ስለሆነም አጋዥ ኃይሉን ለማግኘት የሚያበረክቱት ገጸ-በረከትና ሊያሣምኑበት የሚችሉበት ምክንያት ማቅረብ
እንዳለባቸው አመኑ። በዚህም መሠረት የሚሰጡት ገጸ-በረከት የኢትዮጵያን ቅምጥ የተፈጥሮ ኃብትና የሰው ጉልበት እንዳሻው ለመበዝበና
ለመጠቀም ፍላጎት ያለው የውጭ ኃይል መሆን አለበት። ይህንን ካደረጉ የአገሪቱን የግዛት አንድነት ባፈተቱት መልኩ መሸንሸን
እንደሚችሉ ተማመኑ። ነገር ግን ከውጭ ኃይሎች ጋር ለመሞዳሞድ ይህንን በገጸ-በረከትነት መልክ የሚያቀርቡትን የኢትዮጵያን የተፈጥሮ
ኃብትና የዜጎቿን ጉልበት በቁጭትና በእልክ እምቢ ብሎ የሚሟገታቸው ማን እንደሆነ ሲያጠኑ፦
1. የኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነት ዋናው ኃይል ዐማራው ነው ፣ ስለዚህ መመታትና ዘሩ ከምድረ-ገፅ መጥፋት ይኖርበታል፤
2. ዐማራው የነጮችን የበላይነት አይቀበልም፣ ምክንያቱም በራሱ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ይመካል፤
3. በየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ዐድዋ ላይ የአውሮፓን ቅኝ ገዥ ኃይል ቅስም ሰብሮ የመለሰ ዐማራው ነው፤
ስለዚህ በሚከተሉት የሐሰት መርሆዎች ላይ ተመርኩዘው የዐማራውን ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት ለማኮላሸት የዋሃንን የማነሁለያ
ሥልቶችን ነደፉ ፦
1. "ኢትዮጵያዊነት ዐማራው በሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ላይ የጫነው ዕዳ እንጂ የቀሩት ጎሣዎችና ነገዶች የሚጋሩት የወል
ዕሴት አይደለም፤
2. በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት ነገዶችና ጎሣዎች (በእነርሱ አገላለፅ ብሔር/ብሔረሰቦች) የዐማራው ነገድ እስረኞች ፣
አገሪቱም የብሔረሰቦቹ እስር ቤት ናት ፤ በአገሪቱ ሕዝብም መካከል የታሪክ ፣ የባህል ፣ የሥነ-ልቦና ፣ የደምና የጋብቻ
መተሣሠር የላቸውም፤
3. ኢትዮጵያ የምትባለዋ አገር በመጀመሪያ ሙሉ በሙሉ ፈርሣ ከዚያ በእኒህ ነገዶችና ጎሣዎች መልካም ፈቃድ እንደገና
መሠራት አለባት፤" የሚሉ ናቸው።
MORESH WEGENIE AMARA ORGANIZATION
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910
Tel: (202) 230 - 9423 Fax:
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar