ኦህዴድ አባላቱ ዉስጥ የተፈጠረዉን ስር የሰደደ ክፍፍል ለማብረድ ስብሰባ ጠራ
በዚህ ከ700 በላይ የሚሆኑ የኦህዴድ አባላት በተሳተፉበት ስብሰባ ዋነኛ የመወያያ ርዕስ ሆነው ከቀረቡት መካከል በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነትና የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በስብሰባዉ ላይ የኦሮሞ ህዝብ በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማንነቱን ያስከበረ መሆኑ፤ ኦነግ የሚያቀነቅነው የመገንጠል ሀሳብ በአንቀጽ 39 የተከበረ መሆኑና በአመራሩ መካከል የታዩ ክፍተቶች የተዘጉ መሆናቸዉ ተደጋግሞ ተስተጋብቷል። ከዚህ በተጨማሪ “የኦነግ አመለካከት ያላቸው ሰርጎ ገቦች” በቂ የስልጣን ቦታ አላገኘንም በማለት የሚያስወሩት ሀሰት መሆኑንና ኦህዴድ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን ማግኘቱን የስብሰባዉ መሪዎች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛዉ የስብሰባዉ ተሳታፊ “ ይህ በቂ አይደለም “ ምስራቅ ሀረርጌ በኦሮሚያ ክልል ስር መሆን ሲገባው በሀረሪ ክልል ሆኗል፣ ቋንቋችን ተግባራዊ ይሁን ከተባለ በኋላ እስካሁን ተግባራዊ አልሆንም።” ወያኔንና ለወያኔ የደሩትን የኦህዴድ መሪዎች ያስቆጣ ጥያቄ አቅርበዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar