søndag 30. desember 2012

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5288

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/5288
ከአገር አቀፍ ንግግር ወደ አገር አቀፍ ተግባር
በሀብተጊዮርጊስ ለገሰ – ኖርዌይ ኦስሎ
“ሁሉም የሚችለዉን ያህል ጠጠር ይወርዉር” ይህ መልዕክት የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ምስረታን በተመለከተ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከእሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስGinbot 7 Popular Force - GPF formed ወቅት ያስተላለፉት ነዉ፣ ፣ በእርግጥ የእሳት ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ ሲሳይ ዓላማ ህዝባዊ ሀይሉን በተመለከተ በተለያዩ ግለሰቦች ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ነበር፣ ፣
የህዝባዊ ሀይሉ መሪ ማነዉ? ህዝባዊ ሀይሉ የየትኛዉ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ ነዉ? የዉጊያዉን እንቅስቃሴ የሚያደርገዉ የት አካባቢ ነዉ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሱ ቢሆንም የወታደራዊ ስትራቴጂ ጥያቄዎች በመሆናቸዉ ወቅታዊ ጥያቄዎች አይደሉም፣ ከዶ/ር ብርሀኑም አገላለጽ የምንረዳዉ ወቅታዊ ጥያቄ መሆን ያለበት የህዝባዊ ሀይሉ ዓላማ ምንድነዉ? ትግሉን ያነጣጠረዉ በማን ላይ ነዉ? የሚሉት ናቸዉ፣ ፣ከመልስም አንጻር መረጋገጥ ያለበት ወያኔ ላይ ያተኮረ ትግል በማድረግ ዘረኛዉን መንግስት በማስወገድ ሉአላዊነቷ የተከበረ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ነዉ፣ ፣
በመንደርደሪያነት የተጠቀምኩት የዶ/ር ብርሃኑ መልዕክት አንድ ዓረፍተ ነገር ቢመስልም በዉስጡ ያዘላቸዉ ሀሳቦች ግን ብዙ ናቸዉ፣ ፣ይህ መልዕክት ዓላማን መሰረት ያደረገ ትግል እንድናደርግ የሚያሳስበን ነዉ፣ ፣ትግላችን ከአንድ ብሄር በተዉጣጣ ቡድን የተጫነብንን የዉስጥ የቅኝ አገዛዝ ለማስወገድ የሚደረግ የነጻነት ትግል በመሆኑ ያለንን መለስተኛ የሀሳብ ልዩነታችንን ነጻ ከወጣን በሗላ በእኩልነት የምንዳኝበትን ስርዐት ፈጥረን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ያለብን መሆኑን የሚጠቁም መልክት ነዉ፣ ፣
ቅኝ አገዛዝ(colonialism) በ19ኛዉና በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን የዉጭ ሀይሎች በተለይ አዉሮፓዉያን የሌላን ሀገር ህዝብ በማግለልና የፖለቲካ የበላይነትን በመቆጣጠር ለእናት ሀገራቸዉ የሌላን ሀገር ሀብት መመዝበር ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ያራመዱበትን የሚገልጽ ቃል ነዉ፣ ፣በቅርጹ ከቅኝ አገዛዝና ከእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ( Colonialism and Neo-colomialism) የተለየዉና በይዘት አንድ የሆነዉ የዘመኑ የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ( Internal colonialism) በጥልቀት መታየት እንዳለበት በተለያዩ ምሁራን እየተገለጸ ይገኛል፣ ፣
ባሬራ (Barera) የተባሉት ምሁር የዉስጥ ቅኝ አገዛዝን ሲገልጹ ”Internal colonialism is a structured relationship of domination and subordination which are defined along ethnic or racial lines where the relation is established or maintained the interests of all or part of the dominant group in which the dominant and the subordinate populations intermingle.” ይላሉ ፣ ፣
በተጠናከረ መዋቅርና በረቀቀ ስልት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሀብት ከአንድ ዘር የተዉጣጣዉን ቡድን ኪስ እያሳበጠና እያደለበ ስናይ፣ የመከላከያና የደህንነት ሀይሉ ከአንድ ዘር በተዉጣጣ ቡድን ፈላጭና ቆራጭነትን ሲገለጽ፣ የፖለቲካ ሀይሉ በአንድ ዘር የበላይነት ሲመራ፣ ቢሮክራሲዉ በአንድ ዘር ተተብትቦ ሰራተኛዉን መግቢያና መዉጪያ ሲያሳጣዉ ስናይ የባሬራ (Barera) የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ(Internal colonialism) አገላለጽ የሀገራችን የዘረኛዉ መንግስት መገለጫ መሆኑን ሳንጠራጠር እንድንቀበል ያስገድደናል;;
ቅኝ አገዛዝና ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የማይለያዩ ሀሳቦች ናቸዉ;; የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ አንድ ሀይል ሌላዉን ትልቅ ሀይል በትንንሽ ክፍሎች በታትኖ እነዚህን ትንንሽ ሀይሎች አንድ በአንድ የመቆጣጠር ስልት ነዉ;; በእርግጥ ትልቁን ሀይል ትንንሽ ቦታዎች መከፋፈል ከባድ በመሆኑ አሸናፊዉ ክፍል ፖለቲካዉን፣ ሚሊታሪና ደህንነቱን፣ እንዲሁም ኢኮኖሚ ዘርፉን መጨበጥና የህዝብ አንድነት እንዳይፈጠር መከላከል የህልዉናዉ መሰረት ነዉ;; በመሆኑም የከፋፍለህ ግዛ መሪዎች በጎሳዎች፣ በብሔሮችና በአጠቃላይ በሕዝቡ መካከል የእርስ በርስ ጥላቻ መርዝ መርጨትና ማራገብ (encouraging blood feuds) የየዕለት ተግባራቸዉ ነዉ;; ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የእያንዳንዱን ጎሳና ብሔረሰብ ስስ ብልትና ደካማ ጎን አጥንቶ ማጋጨትና ማጣላትን ይጠይቃል;;በአገራችንም በትልልቆቹ ብሔረሰቦች በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በተለያዩ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረዉ የመረረ ጥላቻና በጠላትነት እንዲተያዩ የማድርግ ሴራ በወያኔ ተግባራዊ የተደረገ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዉጤት ነዉ;;
ይህ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በዓለማችን በሰፊዉ ስራ ላይ ዉሏል ;; ሮማዎችና እነግሊዞች ግዛታቸዉን ለማስፋትና ለመቆጣጠር ጎሳዎችን እርስ በርስ በማጋጨት ፖሊሲዉን ለሀብት ምዝበራ ተጠቅመዉበታል;;እንግሊዞች ህንድን፣ አንግሎ ኖርማን አየርላነድን ለመቆጣጠር የተጠቀሙበት ዘዴ ነዉ;; በአገራችንም ኢጣሊያን በአምስት ዓመት ቆይታዉ አገሪቷን በቋንቋ ከፋፍሎ ለመግዛት ያደረገዉ ሙከራ የሚረሳ አይደለም;;
በመሆኑም ለ21 ዓመታት የተዘራዉ የጎሰኝነት ወይም የዘረኝነት መርዝ ለነጻነት የሚደረገዉን ትግል ዉስበስብና ከባድ ያደርገዋል;;እዚህ ላይ ተጨምሮ የመቃወም ትርጉምና የተቃዋሚዎች ስራ እርስ በርስ በመብላላት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ትግሉን ከማዳከምና የስርአቱን ዕድሜ ከማራዘም ዉጭ የሚፈየደዉ እንደሌሌ በቃለምልልሱ ላይ በጉልህ መገለጹ አግባብ ነዉ;; ሁሉም የአቅሙን ያህል፣ የችሎታዉን ያህል ለትግሉ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ሲቀርብ ከልባችን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ እንዲመጣ እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ የሚለይበት በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች በጉልህ ተለይተዉ የሚታወቁበት ወቅት ላይ የደረስን መሆኑን ከመልዕክታቸዉ መረዳት ይቻላል;;
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት አስከፊ የሆነ ጭቆና ስር ወድቋል;;የአንድ አገር ምሶሶዎች ተደርገዉ የሚታዩት ኢኮኖሚ፣ ቢሮክራሲ፣መከላከያ፣ ደህንነትና ፖሊስ ከአንድ ብሔር በተዉጣጣ ቡድን እጅ የተያዘ በመሆኑ አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የበይ ተመልካች የሆነበት ወቅት ላይ ደርሰናል;;በእሳት ቴሌቪዥን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቡድን አሳይመንት መስራት ጥያቄ እንደሚያስከትል መግለጻቸዉ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቁም ነዉ፡፡ የልቅ-ግብረስጋ ግንኙነት(pornography) ድህረገጾች እየተለቀቁ ስለ አገራችን ችግሮች መረጃ ልናገኝባቸዉ የምንችልባቸዉን ድህረገጾች ይዘጉበናል በማለት ተማሪዎቹ አሰደምመዉናል;;ይህን ሰምቶ ምን አገባኝ ብሎ መቀመጥ ከህሊና ወቀሳ አያድነንም;;
መረጃን ማራቅ፣ ያለመተማመን ስሜት በእያንዳንዱ ግለሰብ ዉስጥ እንዲፈጠር ማድረግ፣ የርስ በርሰ ጠላትነት ስሜት መፍጠር፣ ሁሉም በአይነቁራኛ እንዲተያይ ማድረግ የዘረኛዉ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማጠናከሪያ ዘዴዎች ናቸዉ;;
ስለዚህ ይህን ፀረ ሕዝብ የሆነ ከፋፋይ ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገዉ ትግል ለመሳትፍ አምርረዉ የተነሱት;;አገራዊ አጀንዳ ያላቸዉ እንደ ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይልና የመሳሰሉ ድርጅቶች ሙሉ ድጋፍ ሊሰጣቸዉ ይገባል;; በተለይ ህዝባዊ ሀይሉ ሀገራዊ አጀንዳ ካላቸዉ ከሌሎች በጎሳ/በብሔር ከተደራጁት ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሳዉን ስጋት ከማስወገዱም በላይ ድሉን የሚያፋጥነዉ በመሆኑ የሚደገፍ አቋም ነዉ;;
በአጠቃላይ ከጠባቂነት ተላቀን የእያንዳንዳችን ሀላፊነት መሆኑን በመረዳት ሁላችንም ለትግሉ የችሎታችንን ያህል ጠጠር በመወረዉር ከአገር አቀፍ ንግግር ወደ አገር አቀፍ ተግባር መሸጋገር እንዳለብን የሚጠቁም መለልዕክት የተላለፈ ስለሆነ በአዎንታ መቀበል ይኖርብናል;;
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች !!!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar