fredag 28. desember 2012

የወያኔ አገዛዝየስልክ ና የኢሜል መልእክቶችን እንዲሁም ዬሳተላይት ቴሌቪዥን ለማፈን የሚጠቅመውን ቴክኖሎጂ ከህንድና ከቻይና ኩባንያዎች መግዛቱ
by MinilikSalsawi
የወያኔ አገዛዝየስልክ ና የኢሜል መልእክቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም ዬሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለማፈን የሚጠቅመውን ቴክኖሎጂ ከህንድና ከቻይና ኩባንያዎች መግዛቱን አዲስ መረጃ አጋለጠ
በዋጣው አዲስ መረጃ በአለም ላይ ለዚሁ ተግባር የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚሸጡ የ150 ኩብንያዎችን ስም ይፋ አድርጓል።
የዊኪሊክሱ መስራች ባለቤት የሆነው ዊሊያም አሳንጄ ለ ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እንደተናገረው፤ አንድ የህንድ ኩባንያ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የስለላና የማፈኛ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት መሸጡን ከኩባንያው ፋይል አንብቤአለሁ” በማለት አጋልጠዋል።
ሀይማካል ፕራዴሽ የተባለው የህንድ ኩባንያ የሳተላይት መስመሮችን፣ ከኢንል ሳት፣ ኢዩቴል ሳት፣ አረብ ሳት፣ ቱርክሳት የሚተላለፉ የሲና የኬዩ የቴሌቬዥንና የራዲዮ የሳተላይት ስርጭቶችን እንደሚያፍን ዘ ሂንዱ የተባለው የህንድ ጋዜጣ ዘግቧል። በዊኪሊክስ መረጃ መሰረት የማፈኛና የስለላ ቴክኖሎጂዎችን ለአምባገነን መንግስትታ ከሚሸጡት የህንድ ኩባንያዎች መካከል ሾጊ ኮሚኒኬሽን፣ ክሊር ትሬል፣ ሺልድ ሴኩሪቲ የሚገኙበት ሲሆን፣ የቻይናዎቹ ዜድ ቲኢ፣ ሀዋይ ቴክኖሎጂና ቪክስቴልም ተጠቅሰዋል።
13 ሚሊዮን ዜጎቿ ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሚለገሰው የእርዳታ እህል ህይወቱን የሚገፋባት አገር ኢትዮጵያ ን እየገዛ ያለው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በብዙ ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ የህዝብን ስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም ሰተላይት ሬዲዮኖችንና ቴሌቪዥንኖችን ለማፈን ሙከራ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።
ዊሊያም አሳንጄ አምባገነን መንግስታት ስልጣናቸውን ለማቆዬት ሲሉ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ እነዚህን የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች እንደሚገዙ በድረገጹ ላይ አስፍሯል

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar