onsdag 25. februar 2015
tirsdag 17. februar 2015
Addisua Ethiopia : የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመ...
Addisua Ethiopia : የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመ...: February 14, 2015 | Filed under G7 Editorial , አማርኛ | Posted by admin አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝ...
የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ
ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
Addisua Ethiopia : የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
Addisua Ethiopia : የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ: ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም :-<<ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል>...
የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
ሌሎችን የ አንድነት አባላትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት፦ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አፈ ጉባዔ አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ናቸው፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል የቀድሞዎቹ የአንድነት አመራሮች። በዚህም መሰረት በርከት ያሉ የአንድነት አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲን የአባልነት ፎርም መሙላታቸው ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት፦ ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ከሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ-“በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው” ሲል አንድነት ፓርቲ አስታወቀ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ስርዓቱ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚመች የአስተሳሰብ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ ፣ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው ብሎአል። የምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለማፍረስ የወሰደውን እርምጃ አጥብቆ የኮነነው አንድነት፣ አሁን ባለው ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ተቀበረዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን አስታውቋል። አባሎቹ ይህን ህገወጥ እርምጃ በፅኑ እየተቃወሙ ለነፃነትና ለኢትዮጵያዊነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመከፍል ዝግጁ መሆን እንደሚኖርባቸው አሳስቧል፡፡ ምርጫን በተመለከተ ፓርቲው አቋሙን ሲገልጽ፣ በአምስት ዓመት የሚደረግ ክብረ በዓል አድርጎ ለማድመቅ እና የህዝብ ሀብት ለማባከን በሚደረግ ሂደት ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ፓርቲ መመስረትም ሆነ አሁን ካሉት ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ መታገል የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎአል፡፡ በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው የሚል ፅኑ እምነት መያዙን የሚገልጸው አንድነት፣ የፓርቲ ፖለቲካ አላበቃም ብለው የሚያምኑ የአንድነት አባላት ካሉ በራሳቸው ነፃ ውሳኔ ወደ ፈለጉት ፓርቲ ተቀላቅለው የመታግል መብታቸው መጠበቁንም አስታውሷል። ህዝቡ የትግሉ ባለቤት ሆኖ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የፓርቲው አባላት ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኞች መሆናቸውንም መግለጫው ጠቅሷል። አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲፈርስ መደረጉ ብዙ ኢትዮጵያውያንን አበሳጭቷል።
5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላትና 2 ፓይለቶች ጠፉ
Feb 06, 2015
ጥር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት
ሳምንት በፊት 5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንዲሁም 2 ፓይለቶች ከድሬዳዋ አየር ሃይል
ጠፍተዋል። የጥበቃ አባላቱም ሆነ ፓይለቶቹ ያሉበትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ይህንን
ተከትሎ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከመቶ አለቃ ማእረግ በላይ ያላቸውን አየር ሃይል አባላት ሰብስበው ግምገማ አካሂደው
ነበር።
ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።
ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።
The 60th Birthday celebration of Andargachew Tesige in Oslo Norway
Abonner på:
Innlegg (Atom)




