አሜሪካ ሚስጥ
ራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ 21 ሀገራት ተገን ጠይቆ፤ ከበርካታ አዉሮጳ ሃገራት ይሁንታን ካጣ ወዲህ፤
ጀርመን ስለላን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር እንደምታካሂድ አጋልጦአል። ዴር ሽፒግል የተሰኘዉ የጀርመን ጋዜጣ ባወጣዉ እትሙ፤ ራሱ ጋዜጣዉ ፣ ከስኖውደን ጋር ባደረገዉ የኢሚል ልዉዉጥ፣ ጀርመን በስለላዉ ተግባር ከአሜሪካ ጋር አባሪ ናት ብሏል። ይህን ዘገባ በተመለከተ የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ሃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግረናል ።
ይልማ ሃይለ ሚካኤል
አዜብ ታደሰ ተክሌ የኋላ
AUDIOS: http://www.dw.de/
|
tirsdag 9. juli 2013
የአሜሪካ የስለላ ቅሌት ወደ ጀርመን መዛመቱ
Breaking News: የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ ከግርማ ብሩና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ተ ወያየ
(ዘ-ሐበሻ)የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩና ከሌሎች የኤምባሲው ሃላፊዎች ጋር ረጅም ሰዓት የፈጀ ውይይት ማድረጉን ከኤምባሲ አከባቢ የተገኘ መረጃ አጋለጠ።
የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንዳጋለጡት ዛሬ ጁላይ 8 ከቀኑ 4pm ጀምሮ ዳዊት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ውይይት ያደረገው ስለምን እንደነበረ ባይታወቅም በድምጻዊ ሰለሞን ተካልኝ ምትክ ወያኔ ለመክፈት ላቀደው ሬዲዮ እንዲያዘጋጅ ሊሆን እንደሚችል የኤምባሲው ምንጭ ያለውን ግምት ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ቪድዮችን በመልቀቅ ከትግራይ ኦንላይን እና ከአይጋ ፎረም የማይተናነስ ገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ሥራዎችን እየሰራ ነው በሚል የሚተቸው ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር ከመገናኘቱ አስቀድሞ በቅርብ ወደ አሜሪካ ለአባይ ግድብ ጉዳይ መጥተው ያልተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ካካሄዱት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎሮስ አድሃኖም ጋርም በስልክ መገናኘቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በዲያስፖራው የሚገኙ የነፃው ፕሬስ ሚዲያዎችን በማጥቃት እየተወነጀለ እንደሚገኝ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ከሚሰጡ አስተያየቶች መረዳት ተችሏል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/ amharic/?p=5097
አንዱአለምና ጋዜጠኛ እስክንድር የኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ
የአንድነት ፓርቲ የህዝባዊ ንቅናቄ ግብረሀይል፣ የሶሻል ሚዲያ ኮሚቴ አባላት የነፃነት ታጋዮቹን አንዱአለም አራጌንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጎበኙ፡፡ የሶሻል ሚዲያ አባላቱ ትላንት በቃሊቲ እስር ቤት ባደረጉት ቆይታ የአንዱአለም እና የእስክንድር መንፈሳዊ ጥንካሬ እንዳስደሰታቸው ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የነፃነት ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አበረታች መሆኑን አስምረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በንቅናቄው መሳተፍ እንዳለበት መክረዋል፡፡ ታጋዮቹ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለጎንደርና ለደሴ መልዕክት እተላልፈዋል፡፡
ወጣቱ የነፃነት ታጋይ አንዱአለም አራጌ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነፃነቱ በሰላማዊ መንገድ መታገል አለበት ካለ በኋላ “በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ በተጠሩት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የጎንደርና የደሴ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ማሰማት አለበት፡፡ ሰላማዊ መሆናችንን ለሁሉም ወገን ማስመስከር ዘለብን” ብሏል፡፡
ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ኢትዮጵያ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ብሔራዊ ውርደታችንን የሚያሳይ መሆኑን አስረድቶ “የጎንደርና የደሴ ነዋሪዎች በህዝባዊ ንቅናቄው ተሳተፉ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ በንቃት ተሳተፉ ድምፃችሁን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰሙ፡፡ ሳር እንኳን እንዳይበጠስ ጠጠር እንኳን እንይወረወር” ብሏል፡፡
ዋይታ በደቡብ ነግሷል የብሄር ጥያቄ ተመልሷል በተባለ ማግስት ጥያቄው አገረሸ
በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጋሞጎፋ ዞን የምትገኘው ቁጫ ወረዳ ሰላም በር ከተማና አካባቢዋ ላለፉት ሁለት ቀናት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ስትታመስ መቆየቷን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከስፋራው አጋልጠዋል፡፡
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ በቁጫ ወረዳ የሚገኙ ከ200.000የሚልቁ ነዋሪዎች ያለ ፍላጎታቸው በጋሞጎፋ እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል፡፡‹‹እኛ ጋሞ ወይም ወላይታ አይደለንም››በማለት የማንነት ጥያቄ ያነሱት ቁጫዎች የራሳችን ቋንቋና ከጋሞም ሆነ ከወላይታ የሚለየን ባህል ያለን በመሆኑ ልጆቻችን በራሳችን ቋንቋ እንዲማሩ ይደረግ በማለት የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ አመታት ተቆጥረዋል፡፡
የደቡብ ተወላጅ የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ከተረከቡ በኋላ በመለስ አስተዳደር ምላሽ ያላገኘው ጥያቄያቸው መልስ ሊያገኝ እንደሚችል ተስፋ በማድረግ ሽማግሌዎችን በመምረጥ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰድደዋል፡፡አዲስ አበባ የመጡት መልእክተኞች ጥያቄያቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካኝነት ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ ተገብቶላቸው ወደ መጡበት እንዲመለሱ ቢደረጉም መኖሪያ ቀዬአቸው ከደረሱ በኋላ ለእስር መዳረጋቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ አስቆጥቷል፡፡
mandag 8. juli 2013
ወያኔ እያለ ሙሰኝነትን ማጥፋትም መዋጋትም አይቻልም!
የእስክንድር ነጋ መልእክት እና ሌሎችም የሰሞኑ ወጎች
የEMF – (ዳዊት ከበደ እንደጻፈው) በቀጠሯችን መሰረት ወጋችንን ልቀጥል። ማክሰኞን አልፈን ረቡዕ ላይ ነው የተለያየነው። እሮብ ጠዋት እኔ ወደ ኢሳት ስቱዲዮ ለቃለ ምልልስ ሳመራ፤ የስራ ባልደረባዬ ክንፉ አሰፋ ደግሞ የኃይሌ ገሪማ “ሳንኮፋ” ቢሮ ሄደ። ተክላይ (የበርሃ ስሙ አማኑኤል) የአሲምባ ፍቅር ብሎ ባሳተመው የመጽሃፍ ምረቃ ላይ ለመገኘት ወደዚያ አምርቷል። እዚያ የቀድሞ የኢህአፓ ሰዎች “የናንተ ትውልድ ፌዴሬሽኑን ሳይቀር ለሁለት የከፈለ ነው!” ተብሏል። ዝርዝሩን ክንፉ እንደሚያስነብበን በማመን ወደራሴ ትረካ ልገባ ነው።
ከደረጀ ደስታ ጋር ወደ ኢሳት ስቱዲዮ ሄድኩ እና ቃለ ምልልሳችንን ከጨረስን በኋላ፤ በርከት ያሉ ሰዎች ወደ ስቱዲዮው ሲመጡ አየሁ። ከነዚያ ውስጥ አንዷ (ለጥንቃቄ ያህል ስሟን ልዝለለው) ናት። ሰሞኑን ነው ከአዲስ አበባ የተመለሰችው። ቃሊቲ ሄዳ እስረኞችን ጠይቃ ነው የመጣችው።
“ከእስክንድር ጋር የተላከ መልእክት አለኝ” አለችኝ፤ ገና እንዳገኘኋት (ሰላምታ መለዋወጣችንንም አላስታውስም)። ቀሪውን በፒ.ዲ.ኤፍ ያንብቡ 5
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም የሀገሪቱን ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 30ና የሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ 50ኛ ዓመት ቁጥር 4 በሚደነግገው መሰረትም ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካልና ለዞኑ አስተዳደር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ በመግባት ከ80 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በማሳተም ከ20 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በጎንደር ከተማ አሰራጭቷል፡፡ በመዋቅራችን አማካኝነትም የቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ እያደረግን ባለንበት ወቅት በክልሉ መንግስት የማደናቀፍና የማሰር ርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡
በክልሉ መንግስት አባሎቻችን ላይና አመራሮቻችን ላይ በሕገ ወጥ መንገድ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እየተገፈፈ፤ ሰብዓዊ ክብራቸውን በመጣስ ላይ ነው፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ የፓርቲውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ፣ አቶ አምደማሪያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ዝምቤ ከሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው፡፡ እንዲሁም በወገራ አቶ ጀጃው ቡላዴ ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ታስሮ ተለቋል፡፡ አቶ ጋሻው ዘውዱ ላይ ጥይት በመተኮስ የመግደል ሙከራ የተደረገ ሲሆን ሮጦ ለማምለጥ ችሏል፡፡ በአልፋ ጣቁሳ ወረዳ መምህር አዋጁ ስዩም ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ሲሆን ሁሉም የታሰሩት ለምን ቀሰቀሳችሁና ወረቀት አሰራጫችሁ በሚል ነው፡፡ ፓርቲያችንም የዞኑን መስተዳድር አፋኝነትና ህገወጥነትን እያወገዘ የታሰሩ አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በፅኑ እንጠይቃለን፡፡ የታሰሩ አባሎቻችንም ህገወጥ እስሩን በመቃወም ከትናንት ጀምሮ የርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
የዞኑ አስተዳደርና የከተማው ም/ከንቲባ በአንድ በኩል ሰላማዊ ሰልፋችንን ለማፈን ርምጃ እየወሰዱ በሌላ በኩል የህዝቡ ሰላማዊ ትግል ወዳድነት ስላስደነገጣቸው የእንነጋገር ጥሪ በ25/10/2005 ዓ.ም አቀረቡ፡፡ በተለይም የከተማው ም/ከንቲባ የሆኑት አቶ ጌትነት አማረ ከሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በ27/10/2005 ዓ.ም 2 ሰዓት የፈጀ ድርድር ካደረጉ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ዕለት በጎንደር የተማሪዎች ምረቃ ስላለና የመንገድ ምረቃ ስላለ እንዲሁም ፖሊስ ግምገማና ስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ የጥበቃ ኃይል አይኖረንም በሚል ቀኑን አዘዋውሩልን የሚል ጥያቄ በማቅረባቸውና ይህም ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ተዘዋውሮ እንዲደረግ ፓርቲያችን ወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት ህዝባዊ ንቅናቄያችን የቆመለትን ዓላማ በምንም ህገ-ወጥነት የማይቀለበስ መሆኑን እየገለፅን ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን፡፡ ሰላማዊ ትግል የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የቆምንለት ክቡር አላማ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንን በመረዳት አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ በቁርጠኝነት ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን፡፡ የጎንደርና አካባቢው ሕዝብም ይህንን አፋኝ ስርዓት በማውገዝ ከጎናችን በመቆም ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Abonner på:
Innlegg (Atom)