mandag 8. juli 2013

አቶ ቡልቻ ከአንድነት ፓርቲና አባላት አናት ላይ መቼ ይወርዱ ይሆን ?


ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋርኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ከአቶ ግርማ ሰይፉ ጋር
የተከበራችሁ አንባቢያን ባለፈው ሳምንት በተቃጠርነው መሠረት ዛሬም ስለወሎ ትንሽ ልበላችሁ። የደቡብ ወሎ ዋና ከተማ ደሴ ደርሰው ሐይቅን ፣መርሳን፣ ጉባ ላፍቶን፣ ኡርጌሳ፣ ሳንቃን፣ወልዲያን፣ጉብዬን፣ ሮቢትን ፤እያሉ ቆቦ ይገባሉ። ሁሉም የኦሮምኛ ትርጉም ያላቸው ስሞች ናቸው ቋንቋቸው ግን አማርኛ ኢትዮጵያውያንን በዘር መለየት አይቻልም። ተፈጥሮ ይገርምዎታል። ወሎዬዎች መልክና ቁምነገር ሲታደል ከፊት ተሰልፈው የወስዱ ይመስልዎታል። ህጻን አዋቂው ያምራል። የሰባ ዓመት ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በሚገርም ሁኔታ አሁን በዚህ ዕድሜያቸው ላይ ሆነው በልጅንታችው የነብራቸውን ውበት ያሳብቅባቸዋል።
ወጣቶቹን በሙሉ ዓይን ለማየት እንኳን ያሳሳሉ። ውበት ለመጨመር ምንም የሚቀባቡት ነገር የለም። ለነገሩ ተፈጥሮ ቀብታችው የለ? ለመዋቢያ ብለው ቢቀቡ ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ውበት ከማበላሽትና ወጪ ከማብዛት የዘለለ ጥቅም የለውም። የሚገርም ነው። ወሎዮቹ ቁመተ ለግላጋ ጸጉረ ረጂም፣ አፍንጫ ሰልካካ ፈጽሞ ክፋት የሚባል ነገር የሌለባቸው ገራገሮች ነቸው።

በገንዳሆ ከተማ በመከላከያ ሰራዊትና ጸረ-ሽምቅ በሚባሉት ልዩ ሀይሎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውጥጥ በርካታ ሰዎች ተገደሉ

ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ  ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል።
በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ጸረ-  ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ከ 150-200 የሚደርሱ የመንግስት ታጣቂዎች ለወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና በሚል በቀድሞ ስሟ ሽንዲ በአዲሱ ስሟ ገንዳሆ ከተማ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ትናንት ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው ሰፍሮ ከሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ሌሊቱን ሙሉ ጎራ ለይተው ሲታኮሱ አድረዋል።

በጭቆናና በበደል የተፈተነ የፍትህ እና እኩልነት አባት – ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር (ክፍል ፪)


በማናዬ በላይ
II.        በእሳት የተፈተነ ብረት - ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር
 ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር እ.ኤ.አ ሚያዚያ 1889 ዓ.ም ማሀራሽትራ ክልል በአሁኑ ማድያ ፕራዲሽ ዉስጥ በምትገኝ ራትናግሪ በምትባል ወረዳ የተወለደ የዚያኔዉ ህፃን ያንን ሁሉ ጭቆናና በደል ያስተናገደ በኋላ ለህንድም ይሁን ለሌላዉ አለም ለፍትህ እና እኩልነት ትግል አርአያ የሆነ ታላቅ ሰዉ ነበር፡፡ አምበድከር በመላዉ የሹድራ ወይም አይነኬ ማህበረሰብ አባላት ላይ ይፈፀም የነበረዉ ጭቆናና በደል ማሳያ ነዉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ የመጀመርያ ክፍል በቅድመ ታሪክ ላይ የተገለፁት ይህ ታላቅ ሰዉ በልጅነቱ የደረሰበትን ግፍ ከከተበበት የግል ማስታዎሻዉ ላይ ከታተመዉ “Waiting for Visa” ላይ የተወሰደ ነዉ፡፡ በህንድ በዉልደት የሹድራ አባል ከሆኑ ትምህርት፤ ገንዘብ፣ ክብር፤ ስልጣን ማግኘት የማይታሰብ ነዉ፡፡ እርስዎ ሲወለዱ ጀምሮ የተፈጠሩት ለአገልጋይነት ነዉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በአጋጣሚ የሚደርስብዎን ጭቆና ተቋቁመዉ ቢማሩ፤ ሀብት ቢያፈሩ፤ ስራ ወይም ስልጣን ቢይዙ ማህበራዊ ህይወትዎን ሊቀይረዉ አይችልም፡፡
 

ከድጡ ወደ ማጡ! የቀበሮ ባሕታዊ በሎንደን

ወንድሙ መኰንን፣ ሎንደን

መግቢያ
Debretsion Mariam London Ethiopian Orthodox Church
በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁ ወገኖቻችን በኛ ሎንደን በምንኖረው የኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ በሆንን ኢትዮጵያውያን ላይ በአንድ መነኵሴ ነኝ ባይ የቀበሮ ባሕታዊ ግለሰብ አማካኝነትና በወያኔ ቀጠረኞች የደረሰብንን ይቅር የማይባል በደል ዕለት በዕለት እንደምትከታተሉና መጨረሻችንን ለማየት በጉጉት እንደምትጠባበቁ እዚህ ያሉት ወንድሞችና እህቶች በሚገባ ያውቁታል። ያመሰግናሉም። ታዲያ ከዚያች ቀውጢ የሁዳዴ ጾም መያዢያ ማግስት፣ ጀምሮ የተዘጋብን ቤተክርስትያን ጉድይ እስካሁን እልባት ሳያገኝ፣ ቀርቶ ሕጻናቱም፣ አይቆርቡም፣ አዛውንቱም፣ ወይዛዝርቱም እግዚአብሔርን ማምለኪያ ቦታ አላገኙም። ይኸ በደል ባንድ ካኽን ንኝ ባይ ሲፈጸም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪአው መሆን አለበት። ብቻ በየሰንበቱ፣“አንድ ሐሙስ የቀራችሁ፣ የእንጨት ሽበት፣ ሽሜ ጉጉ” እያተባሉ በወያኔ ሶልዲ በተገዙ ስድ ወጣቶች እየተሰደቡ፣ሴቶችም ለጆሮ በሚቀፍ ስደብ እየተሸማቀቁ፣ ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ገቢ እየገቡ ሕንጻዋን እየተሳለሙ፣ ከሕዝብ ጋር ከሚንከራተቱ አንድ ቄስ፣ አንድ መሪ ጌታ፣ እና በመምሕር ታሪኩን ጨምሮ በዛ ካሉ ዲያቆናት መሪነት ሜዳ ላይ እየጸለዩ፣ አራት ወራት አሳለፈዋል። ምን ላይ ደረሰ እያላችሁ የምትጠይቁ በዝታችኋል። ሁለቱ አዋጊ ጳጳሳትም፣ አቡነ ገብርኤልና አቡነ ቀውስቶስ፣ የትም ቦታ መንቀሳቀስ በማይገባቸው የሱባኤ ሰሞን አገረ ስብከታቸውን ጥለው ሕንጻውን ሊቀሙን ቢመጡም፣ በተደረገው ርብርብ ሳይሳካላቸው ቀርቶ “አባ” ተባዩን የቀበሮ ባህታዊ፣ “በርታ” ብለው ወደመጡበት ተመልሰዋል። “በመነኵሴ ነኝ” ባዩ አመጸኛ ግለሰብ አዝማችነት፣ ተዝቆ፣ ተዝቆ በማያልቀው የወያኔ ገነዘብ ኪራይ ከፋይነት ተደለለው፣ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ረግጠው በማያውቁ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጋጠ-ወጦች (ጋንግስተሮች) እስከመገፋት መገፍተር፣ደርሷል። እና አባ ተባዩም ንብረት እስከመስረቅና ማጋዝ ጀምረው ነበር። እንዲያም ሁኖ፣ እስካሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተክስቲያኑን እየጠበቀና እየተከላከለ ይገኛል። ግፉ ግን በዝቷል። ሁለንተናው ዘቅጧል። ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ ተብሎ ቢደመደም ይበጃል። “አባባሱባት” ነበር ያልኳችሁ ባለፈው? እሱን እርሱት። ያሁኑ ይባስ።
የመዳን ንሰሐ ለጥቃት ሲያጋልጥ
ባለፈው ሳምንት የተፈጽመው አሳፋሪ ወንጀል፣ በታሪካችን ምንጊዜም “በምዕምን ላይ ደረሰ” ሲባል ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ ነው። ፈረንጆች “Abuse of Trust” ይሉታል።  ያመኑት ፈረስ በደንደስ እንደሚሉት ነው። በመጨረሻው ጽሑፌ ከአንባቢዎቼ የተልያየሁት “ብጹዐን አባቶች ለታስታርቁን ወይስ ልታዋጉን መጣችሁ?” በማለት በሞነጫጨርኩት መጣጥፍ ነበር። አባዛኛው መልዕክቱ ቢገባውም፣ ሌሎች ሰዎች ነገሩን እያባባስኩ እንጂ እየረዳሁ አለመሆኔን ስላሳሰቡኝ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ላለመጻፍ አቅጄ ቆየሁ። የኔ ዝምታ ግን “ትሻልን ፈትቼ ትብስና አገባሁ” ቢጤ ሆኖብንና አሸንፈው ጭጭ ያሰኙኝ መሰላቸው። የኔ መተው ነገሩን አልከተተውም። ጳጳሳቱ ወደመጡበት በመመለሳቸው፣ የወያኔን ይሁንታ ተጨምሮበት፣ የቀበሮ ባህታዊው ባሰባቸው። በነጋ በጠባ ሕዝቡን “በምን ላቁስለው?” እያሉ ሲያልሙ የሚያድሩ ይመስላሉ። ፓትርያርኩ በሞቱላቸው ጊዜ፣ ይኸን ሕዝብ በምን ቆሽቱን ላድብን ብለው፣ ለታጋይ ጳውሎስ ፍትሀት አደርጋለሁ ብለው ተነስተው እንደአንጫጩን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሌላ አገኙ። የቤተክርስቲያናችንን መሠረት የናደ፣ እንኳን ከአንድ የአሀይምኖት አባት ነኝ ብሎ ከሚመጻደቅ ይቅርና፣ ከመርካቶ ዱሩየም የማይጠበቅ፣ በጣም የወረደ ተግባር ፈጸሙ። “ቤተክርስቲያናችንን ይጎዳል፣ ዝም በሉ” ለምትሉን፣ ዝምታ ለበጓም አልበጃት፣ ዝም አንልም። ዝም እማ ካልን ዲያብሎስ ይነግሳል። በዓለም ዙሪያ ያሉት ክርስቲያን ወንድሞችና እየቶቻችን የደረሰብንን በደል አውቀው፣ በጸሎታቸው እንዲተባበሩን፣ በደሉ ይታወቅ። የሎንደንማ ሕዝብ በተፈጽመው አስነዋሪ ነገር ተደናግጦ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ገብቶት ቁጭ ብሏል። አንዳንዱ፣ “ተው ከእግዚአብሔር ያግኙት”ይሉናል። ኤዲያ! እግዚአብሔር በአምሳያው የፈጠረን የምንችለውን አድርገን የማንችለውን ልንተውለት ነው። የምንችለውንም፣ የማንችለውንም ለሱ መተውማ ስንፍና ነው። የተጎዱት ያቃስታሉ። እንዴት ዝም እንላለን? ከመሀላችን አንዳችን ተጎዳን ማለት፣ ሁላችንም ተጎድተናል ማለት ነው። ነውሩን እራሱ ይደብቅ እንጂ እኔ ጫካ አይደለሁም የምደብቅለት። አልደብቅለትም። ያበጠው ይፈንዳ! ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

torsdag 4. juli 2013

አባይም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሚጠቅም መልኩ ይገደባል።

የሰብአዊ መብት ረገጣንና ኢትዮጲያዊውያንን በገዛ ሀገራቸው የዜግነት መብት ያሳጣውን ዘረኛ ሥርዓት በጽኑ
እየታገልን አባይም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሚጠቅም መልኩ ይገደባል።
አገራችን በዓባይና በመጋቢ ወንዞች ላይ ግድብ ለመሥራት ሙከራ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1959 ዓ/ም (እ.ኤ.አ) በግብፅና በሱዳን 
መሃል በተናጠል የተደረገውን ስምምነት በመቃወም አስር ሚሊዮን ዶላር በመመደብና በአሜሪካ ሙያተኞች አማካኝነት አያሌ ግድቦችን ለመገንባትና የውሃ 
ሃብቷን ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም በ1964 ዓ/ም (እ.ኤ.አ) ጥናቶችን ማጠናቀቋን መጥቀስ ይቻላል። 
የዚህን ዓይነት ብሔራዊ ጉዳይ ለማስፈጸም ወያኔ ብቻውን አመራሩን ጨብጦ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያለነውን ዜጎች በማስገደድም ይሁን በማታለል 
ገንዘባችንን ለመሰብሰብ ሲነሳሳ እኛም እንደ ዜጋ ይህ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብቱ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠብቆና ተከብሮ በአገሩ ኮርቶ 
በፈቃደኝነትና በደስታ የሚሳተፍበት እንዲሆን እንፈልጋለን። በእውነት ወያኔ ይህንን ብሔራዊ አጀንዳ በዚህ ወቅት ያነሳው ለኢትዮጵያዊያን አስቦ ከሆነ 
በሃይማኖታዊ እምነትና በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ያሰራቸውን ወገኖቻችንን እንዲፈታና ከየቀያቸው ማሳደዱንም እንዲያቆም መጠየቅ ሰብአዊ
መብታችንና ግዴታችንም ነው። የእኛ ጥያቄ የመብት የአንድነትና የፍትህ ጥያቄ ሆኖ አባይንም የመጠቀም መብት የግብፅና የሱዳን ብቻ ሳይሆን
የኢትዮጵያም ጭምር መሆኑን በዚሁ ልናሰምርበት እንወዳለን። የእኛም ሚና ገንዘብ ከማዋጣት ያለፈ ነው ብለን ስለምናምን ለዛሬው ስለ ህዳሴው ግድብና
ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉንን ነጥቦች እንደሚከተለው እናቀርባለን።
የወያኔ የአባይ ፖለቲካዊ ሰሌትና “ የወያኔ የአባይ ፖለቲካዊ ሰሌትና “““የህዳሴው ግድብ የህዳሴው ግድብ የህዳሴው ግድብ” ” ” ” ለኢትዮጲያ ህዝብ ለኢትዮጲያ ህዝብ
እንዲሁም ለተፋሰሱ ግርጌ ሃገራት ያለው ፋይዳ፡-
ፕሮጀክቱ እንደ ተአምር በሚወራው የአምስት ዓመቱ “የልማትና
ትራንስፎርሜሽን” እቅድ ውስጥ ያልተካተተ ሲሆን እቅዱ የመጣው “ባለ
ራዕዩ መሪ” በሰሜን አፍሪካ የተቀጣጠለው የጸረ አምባጋነን ዓመጽ
እሳቸውንም እንዳይጠርጋቸው በመስጋትና የኢትዮጵያ ህዝብ በአባይ ላይ
ያለውን ጥልቅ ብሄራዊ የቁጭት ሰሜት በማጤን የህዝብን የትኩረት
አቅጣጫ እንዳስፈላጊነቱ ለመዘወር እንደሚቻል በህወሃቶች ስለታመነበትና
የህዝብን ትኩረት በማስቀየር ጥቂት እድሜ ለመግዛት ታስቦ ነው። ወያኔ
በዕብሪት መንፈስ ግድቡን የግል ጉዳዩ ብቻ አድርጎ በመምራት በሃገራችን
ሃብትና ሞራል ርካሽ የፖለቲካ ጥቅምም ለመግዛት አስቦ በድንገት ያመጣው
የፖለቲካ ቁማር ነው። ለዚህም ምስክሩ በየሀገሩ የአባይ ቦንድ ለመሸጥ
በግንባር ቀደምትነት የሚሯሯጡትና እራሳቸውን የግድቡ ባለቤት አድርገው
የሚቀርቡት ግለሰቦች የወያኔ ሰዎች መሆናቸው ነው።
የህዳሴ ግድብ ለግንባታ ከተመረጠበት ቦታ እስከ ታቀደለት አላማ ድረስ
ለኢትዮጵያ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ በተለይ ለሱዳን የሚሰጠው ጥቅም
እጅግ የላቀ ነው። ለማስረጃ ሁለት ነገሮችን መጥቀስ ይበቃል።
1) የሱዳን በመስኖ የመጠቀም ሀቅም እሁን ከአለው የሶስት ወር ጊዜ ግድቡ
ሲጠናቀቅ ወደ አስራ ሁለት ወር ከፍ ያደርገዋል። በአንጻሩ ግን ኢትዮጵያ
ሰማንያ ቢሊዮን ብር ውጭ ግድቡን ሰርታ አንድ ስኩየር ሜትር መሬት
እንኳን በመስኖ ማልማት አትችልም።
2) ይህ ግድብ በኢትዮጵያ በኩል ታቅዶ እየተገነባ ያለው ሙሉ በሙሉ
የኤሌክትሪክ ሃይል ብቻ በማምንጨት ለጎረበት ሀገራት በመሸጥ የውጭ
ምንዛሬ ለማግኘት ብቻ ነው። እስከአሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለዉን
የመብራትም ሆነ የሀይል እጥረት በተወሰነ መልኩ ለማቃለል እንኳን እቅድ
አልተያዘለትም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ በብሄራው ስሜትና
አንዳንዴም በፍራቻ እንዲሁም በግዴታ ከሌለው ኪሱ ሰማንያ ቢሊዮን
አዋጦ ከሰራው ግድብ መብራት እንኳን ሳያገኝ ጎረቤት ሃገራት በተለይ ሱዳን
በቅናሽ ከፍያ (በዶላር ስለሚከፍሉ ብቻ) ከህዳሴ ግድብ በሚመነጭ
የኤሌክትሪክ ሀይል ይንበሽበሻሉ። የግድቡ ውሃ ግን በኢትዮጵያ ለም መሬት
ላይ ያርፋል። ውሃው የሚያርፍበት መሬት ስፋቱ ሲንጋፖር የምትባልን ሀገር
ሁለት እጥፍ ይሆናል።
ሱዳን ግድቡ ድንበሯ አጠግብ በመሰራቱ ደስተዋን የገልጸችው በውጭ ጉዳይ
ሚኒስትሯ ነበር፤ ለዚህም ለዋቢነት የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የተናገሩትን መጥቀስ ያስፈልጋል። እንዲህ ይነበባል፡- “the dam will
bring many benefits and blessings for us,” Informa on Minister Ahmed Bilal Osman (Bloomberg June17, 2013)
በነገራችን ላይ ለሱዳን ሰፊ ለም መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርሶ መሰጠቱ የቅርብ
ጊዜ ትዝታ ነው። እና መሬቱ አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በሰማንያ ቢሊዮን
ብር ግድብ ሰርተን መስጠት አለብን ማለት ነው? ለየትኛው ውለታዋ
ይሆን?
ግብፅስ በእውነት ግድቡ እርሷን የሚጎዳ ከሆነ እስከ ወንዙ መጠለፍ ዜና
ድረስ ለምን ዝምታን መረጠች? የአሁኑስ ተቃውሞዋ ጠንካራ ያልሆነበት
ጥቅም ስላላት ነው ወይስ ስለማያዋጣት?
ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብፅ በበለጠ በህዳሴ ግድብ ተጠቃሚ ናትን?
መንግስት ስለህዳሴ ግድብ ሲያልም ይዞት የተነሳው ግድቡን
በኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ ማጠናቀቅ እንደሚቻል አድርጎ ነው።
እውነታው ግን ይህ እንደማይቻል ከመጀመሪያው መንግስት እንድሚያውቅ
ነው። ለዚህም ማስረጃ አምባሳደር ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የተባሉ (ውስጥ
አዋቂ ዲፕሎማት) ሪፖርተር ለተባለ የመንግስት ደጋፊ ጋዜጣ የሰጡት
ቃለመጠየቅ መጥቀሱ በቂ ይሆናል። እንደሚከተለው ይነበባል።
"ሪፖርተር፡- የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ብቻ
መሸፈን ወይም ዳር ማድረስ ይቻላል?
አምባሳደር ኃይሉ፡- አንችልም፡፡"
ታዲያ መንግስት ለምን ለህዝብ መዋሽት ፈለገ? ለምን በኢትዮጵያ ሕዝብ
መዋጮ ብቻ ይሰራል ይለናል?
ስለዚህም ነው ይህ ግድብ ፍፁም የሃገሪቷን ሃቅም ያላገናዘበ፤ ከወዲሁ
የተመደበ በጀት ስለሌልው በማንኛውም መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሁሉ
ወደዚሁ ግድብ ስራ ስለሚሄድ ግድቡ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ቀውስ
በመፍጠር ኢኮኖሚውን በበለጠ ያዳክማል የሚባለው። ይህንንም የአለም
ባንክ ያረጋገጠው ጉዳይ ነው። ስለዚህም ጉዳይ የአለም ባንክ ርፖርትን
ማየት ይቻላል።
ከኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር መካከል በምግብ እራስን አለመቻልና ሥራ
አጥነት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ መንግስትም ማተኮርና
ቅድሚያ መስጠት ያለበት የመስኖ እርሻን ማስፋፋትና የግብርና ምርትን
ማሳደግ ብሎም ለዜጎቹ የስራ እድል መፍጠር ነው። ይህ የህዳሴ ግድብ
ሰማንያ ቢሊዮን ብር የሚፈስበት ቢሆንም እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች
በመፍታት ረገድ እዚህ ግባ የሚባል አስትዋኦ አያደርግም። ለመስኖ እርሻ
አይውልም፤ ከሚፈስበት ገንዘብ አኳያ በጊዜዊነት በግድቡ ግንባታ ወቅት
ከሚሰማሩ ሰራተኞች በስተቅር ይህ ነው ይሚባል የስራ እድልም
አይከፍትም።
የህዳሴ ግድብ አቀንቃኞችና ሙሰና፡-
በየዓመቱ ጠቅላይ ኦዲተሩ በሚያቀርባቸው የኦዲት ሪፖርቶች
እንደሚታየው በርካታ ቢሊዮን ብር በመንግስት ባለስልጣናት ና በሰራዊቱ
አዛዦች በማን አለብኝነት ያለማቋረጥ እየተመዘበረ መሆኑን ያሳያል። የ 2011
ዓ.ም Global Financial Integrity ሪፖርት እንዳመለከተው ከ 2000 -
2009 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ባለው ጊዜ ውስጥ ከ 11.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ በህገ
ወጥ መንገድ ከሃገር ወጥቷል (ይህ ገንዘብ 3 የአባይ አይነት ግድቦች
መገንባት ያስችል ነበር)።  2
በቅርቡ Celebrity Net Worth የተባለ ድረ ገጽ እንደዘገበው ከመጽሀፍት
በቀር ቤሳ ቤስቲን የለኝም ሲሉ የነበሩት “ባለ ራዕዮ መሪ” እንዲሁም
ባለቤታቸው በ 4 ሺ ብር ነው የምንተዳደረው እያሉ የሚሳለቁብን ሰው
በሰማቸው 3 ቢሊዮን ዶላር እንዳለ አሳውቆናል (ለማነጻጸር ስቴፈን ሀርፐር 5 ፣
ኦባማ 12.2 ሚሊዮን ዶላር ነው የሃብታቸው መጠን ግምት)።
ለግድቡ እቃ ማቅረብን ጨምሮ የመንግስት ፕሮጀክቶች በሙሉ ማለት ይቻላል
በአብዛኛው ያለ ግልጽ ጨረታ ለህወሃት ድርጅቶችና በዘመድ አዝማድ በዘረፋ
ለተቋቋሙ ድርጀቶች የሚሰጥ ሲሆን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ምንም
ያልነበራቸው የህወሃት አባላትና ዘመዶቻቸው ጥሩ የተባሉ የመኖሪያ ሰፈሮችን
በመውረር ነባሮቹን በተለያየ ዘዴ በማፈናቀል ውድ በሆኑ የመኖሪያ ቤቶች
የተድላ ህይወት እየኖሩ ነው።
የሌላ ብሄር አባላት የሆኑ የግል ባለሃብቶችን በፈጠራ የታክስ ማጭበርበርና
ሌሎች ወንጀሎች በመክሰስ እንዲሁም የመንግስት መዋቅሮችን በመጠቀም
በተቀነባበረ የንግድ አሻጥር ከውድድር በማስወጣት ህወሃቶችና ጥቂት
አጋፋሪዎቻቸው መንሰራፋታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።
እውን ወያኔ አባይን ለሃገር ጥቅም የመገደብ ሃሳብ ካለው በ”ባለራዕዮ መሪ” ስም
ያለው ገንዘብ ብቻ የፕሮጀክቱን 71% ወጪ መሸፍን ይችላል። ከዚህ አንጻር
ቀሪውን አንድ ከሳቸው አነስ ያለ ወያኔ ሊሽፍነው ይችላል ማለት ነው።
የህዳሴ ግድብና ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ፡-
እራሱ ወያኔ/ኢህአዴግ ያጸደቀውን ህገመንግስት በመጣስ ዜጎችን አሸማቆና
አዋርዶ እያሸበረ ለመግዛት በማሰብ የራሱ የሰለላ ሀይሎች በተላያዮ የሃገሪቱ
ክፍሎች ፈንጂዎችን በማፈንዳትና የበርካት ንጹሃን ዜጎችን ህይውት በመቅጠፍ
የተውኑበትን የግፍ ድራማ መነሻ በማድረግ “የጸረ ሽበርተኛ ህግ”
አጽድቆ፤የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ ሀይማኖትን በነጻነት የመከተልና
የመሳሰሉ መሰረታዊ መብቶችን በሃይል በመጣስ እንደ ርዕዮት አለሙ፣ አንዷለም
አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከር አህመድን ጨምሮ በበርካታ ሺዎች
የሚቆጠሩ ወገኖቻቸንን ከጠላት እንኳን በማይጠበቅ የጭካኔ ሰቆቃ
እይፈጸመባቸው ረዥም የእስር ዘመን በመግፋት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሳያንስ እንደ
አጋዚና ፌደራል ፖሊስ ያሉት የአፈናና የጭፍጨፋ መሳሪያዎቹ ባለ ሀይላቸው
ያለምንም ማመንታት የጭካኔ በትራቸውን በህዝብ ላይ እንዲሳርፉ መብት
ለመስጠት በማሰ እነዚህ ሀይሎች የጭፍጨፋ ተግባራቸውን በሚያካሂዱበት
ወቅት በሚውስዷቸው ማናቸውም እርምጃዎች በህግ እንዳይጠየቁ የሚደነግግ
የህግ ረቂቅ “ጥርስ ለሌለው” ፓርላማ አቅርቧል።
በሌላ በኩል የፍትህ ስርዓቱ ችሎታ ሳይኖራችው ነገር ግን ለአገዛዙ ባላቸው
ፍጹም ታማኘነት ብቻ ተመልምለው የሃገሪቱን የከፍተኛ ትምህርት የጥራት ደረጃ
በማያሟላውና በተለምዶ “ድንጋይ ማምረቻ” ተብሎ ከሚጠራው ሲቪል
ሰርቪስ ኮሌጅ በኮታ “እየተመረቁ” በሚወጡ ምንደኛ ካድሬዎች የተሞላ መሆኑ
ለሥርአቱ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ከመሆን አላለፉም።
እስካሁን ፍትህ ያላገኙ በመንግስት ባለሰልጣናት ትዕዛዝ በጸጥታ ሀይሎችና
በሰራዊቱ በህዝብ ላይ የተፈጸሙ እና እይተፈጸሙ ካሉ ወንጀሎች በጥቂቱ
ለማስታወስ ያህል፦
• በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በደቡብና በአፋር ክልል እንዲሁም በሌሎች የተለያዩ
የሃገሪቱክፍሎች በወያኔ ወኪሎች ሆን ተብለው በተቀስቀሱ የዘር ግጭቶች
የጠፋው ህይወትና የወደመው ንብረት፣
• በጋምቤላ በአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ፣
• በሱማሌ ክልል ለረዥም ጊዜ በመካሄ ላይ ያለው ጭፍጨፋና በተፈጥሮ አደጋ
የተጎዳውን ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዳያገኝ በመከልከል ሆን ብሎ በረሃብና
በበሸታ የማሰቃየት ተግባር፣
• በኦነግ አባልነት ስም በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ያልተቋረጠ ግድያ፣
እስር ና ሰቆቃ፣
• በምርጫ 97 ድምጻችን ይከበር ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ
የተካሄደው ጭፍጨፋ፣
• በጅማ፣ በደሴ እንዲሁም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የክርስትናና የእስልምና
ሀይማኖት ተከታዮችን ሆነ ተብሎ ለማጋጨት የተደረጉ ጭፍጨፋዎችና
የተከበሩ የዕምነት ቦታዎችን የማቃጠል ወንጀሎች፣
• በጉራፈርዳ ና በቤኒሻንጉል አካባቢ በሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ
ተወላጆች ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር ማፅዳት ወንጀል፣
• ለሀገራችን ምንም ፋይዳ ባልነበረውና ከፍተኛ የህዝብ ሃብት በባከነበት የኢትዮ
-ኤሪትሪያ ጦርነት በወያኔ አዛዦች ወታደራዊ ዕውቀት ማነሰና ለሌላው
ኢትዮጲያዊ ዜጋ ባላቸው ከፍተኛ ንቀት በአብዛኛው ከተቀረው የኢትዮጲያ
ክፍል የመጡ ወደ 70 ሺ የሚገመቱ ወጣቶችን ያስፈጁበት ሁኔታ።
እንግዲህ ይህ ሁሉ ግፍ ፍትህ ባላገኘበት ሁኔታ ነው ሌላ ነገር አትጠይቁ ዝም
ብላችሁ አፋችሁን ዘግታችሁ ለግድቡ ገንዘብ አዋጡ የምንባለው!
የህዳሴው ግድብና የህዝብ የሰልጣን ባለቤትነት፡-
“ዲሞክራሲያዊ ምርጫ” በሃገራችን ወያኔ ከራሱ ጋር ተወዳድሮ ከ 99.6 ወደ
99.9% በማሸነፍ እድገት ያሳየበት በከፍተኛ የሃገር ሃብት የሚከወን አሰነዋሪ
ድራማ ሆኗል። በሌላ በኩል ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የፓርቲ ልሳኖቻቸውን
ለማሳተም፣ ሌሎች የቀን ተቀን ተግባራቶቻቸውን ለማከናወንና አባላቶቻቸውን
ለመሰብሰብ አዳራሾችን ለመከራየት ቀርቶ አመራሮች ተሰባስበው ሆቴል ቤት
እራት መብላት የማይቸሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
በብሄራዊ ሰም በተደራጀው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ካሉት 60 ጀነራሎች 58
ቱ ወያኔዎች ሲሆኑ ከጀነራል ማዕረግ በታች በየደረጃው ያለው የሰራዊቱ
የስልጣን ዕርከን ጭምር በአብዛኛው በነሱ የተያዘ ነው። በእያንዳንዱን
የሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶች በግልጽ ወይም በስውር ሰራዎችን የሚዘውሩትም
የህወሃት ሰዎች ናችው።
ያለ እውቀት ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የወያኔን የሰልጣን ዘመን ለማራዘም ባላቸው
ፋይዳ ላይ ተመርኩዘው በሚወጡ ሰንካላ ፖሊሲዎች ምክንያት ህዝቡ በኑሮ
ውድነት፣ በድህነት፣ በበሽታና ሰራአጥነት ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ እይተሰቃየ
ይገኛል። በዚሀም የተነሳ ዜጎች በገዛ አገራቸ የመኖር ተስፋቸው ተሟጦ
በአስቸጋሪው ጉዞ ላይ በአስተላላፊዎች እንዲሁም በባዕድ አገር ቀጣሪዎች
የሚደርሰውን ዘግናኝ ግፍና ሰቃይ እያይዩና እያሰሙ ስደትን በመምረጥ በሺዎች
የሚቆጠሩ ዜጎች ለዱር አራዊትና ለባህር አሳ ቀለብ እንዲሁም በቁማቸው
እየተበልቱ ጉበት፣ ኩላሊትና ልባቸው እየተቸበቸበ ይገኛል።
አብዛኛው የኢትዮጲያ ገበሬ ለምነቱ በተሟጠጠ ኩርማን መሬት የአመት ቀለቡን
ልማግኘት ሲታትር እጀግ ለምና ውሃ ገብ የሆነውን የሀገሪቱን መሬት ዜጎችን
ያልምንም ካሳና ምትክ መሬት ከይዞታቸው በማፈናቀል ለባዕዳን ደሃው ገበሬ
ለደካማው መሬቱ ከሚከፍለው ግብር ባነሰ ዋጋ ያለምንም ዋስትና ለመቶ አመት
እይተቸበቸበ ይገኛል።
ሕዝቡ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በገዛ ሀገሩ ባይተዋር ሆኖ የባለቤትነት ስሜት
እንዳያድርበት ተደርጎ፤ ለአባይ ግድብ ገንዘብ አዋጡ ግን ሌላ ሰባዊም ሆነ
ፖለቲካው ጥያቄ አታንሱ ማለት ሌላ ንቅት ነው።
በአጠቃላይ አባይን ገድቦ ለኢትዮጵያ ጥቅም ማዋልን የሚቃወም ማንም
ኢትዮጵያዊ የለም። ነገር ግን የግድቡ እቅደና የሰራው አካሄድ በበቂ ጥናት ላይ
ያልተመሰረተ፤ ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደለዉ፤ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ይልቅ
በጊዜዊ ፖለቲካ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው። በተጨማሪም አጥቃላይ ሁኔታው
ሲታይ፤ ሱዳን ድንበር ላይ መሆኑ፣ ለመስኖ እርሻ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለሱዳን
አመቺ እንዲሆን ስለተደርገ ይህ ግድብ በኢትዮጵያ ገንዝብ ሳይሆን መሰራት
ያለበት በበለጠ ተጠቃሚዋ በሱዳን ወጭ መሆን አለበት። ይህንም በተመለከተ
እራሱ መለስ ዜናዊ እንዲህ ሲል በአንድ ወቅት ጠቅሶታል። "የዚህ ግድብ ወጭ
መሸፈን የነበረበት ሰላሳ ፐርሰንት በሱዳን ሃያው ፐርሰንት ደግሞ በግብጽ ነበር።"
ይህም የሚያሳየው ሁለቱ ሃገሮች ምን የህል በዚህ ግድብ ተጥቃሚ እንደሚሆኑ
ነው። ይህ እንግድህ በአደባባይ የተነገረው ነዉ። እዉነቱ ደግሞ ቢወጣ ከላይ
ለመግልጽ እንደተሞከረው እዉነተኛዋ ተጠቃሚ ከኢትዮጵያም በላይ ሱዳን
ናት። ታዲያ ኢትዮጵያ በምን አቅሟ ነው የሰማንያ ቢሊዮን ብር ግድብ ሰርታ
ለሱዳን የምትለግሰው? ለዚህም ነው በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ፤ ግዴለሽና
ሃላፊነት የጎደለዉ፤ የፖለቲካ ቁማር ነው የምንለው።
ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደሞከርነው የወያኔ የፖለቲካ መስመር፣ የዛሬና
ትናንት ተግባራቸው፣ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፣ ስለዜጎች መብት መከበርና
ስለጋራ እድገት፣ ስለ ብሔራዊ ክብርና ኩራት ያላቸዉ ንቀት ሳይታረም፣
የሕዝብን የመብት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳሉ ና ከላይ እስከታች በሙሰና
እንደተዘፈቁ ነው አባይን የምንገድብበት ገንዘብ አምጡ የሚሉን።
የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ተገርሥሶ የኢትዮጲያ ህዝብ የሥልጣን
ባለቤትነት ይረጋገጣል አባይም ይገደባል!

onsdag 3. juli 2013

THE WOYANE and ITS ‘’law of increasing poverity’’ IN Ethiopia


Posted: 01 Jul 2013 03:17 PM PDT

by Nathnael Abate( nathy de saint)

   Mass poverty is a catastrophe which is decreasing living standard of the mass that is created artificially by greedy grabbing of all available local public resources by individuals or groups. Human beings are not naturally created to be poor or to live under the roof of poverty.  Since all mankind is equal in birth regardless of his/her race, sex or status backgrounds. Economical poverty comes from mismanagement,uneven distribution of available resources,corruption through which few individuals get rich and the public suffers ,stealing  the public resources  and political unstability. In our country Ethiopia the intense poverty caused by ruling regime which is afflicting and suffering souls of millions. Poverty ever since its created it affected the lower society class but not the groups or individuals in power. During the famous Ethiopian famine those who were died were peasants, pastoralists and people who were at lower economical level.

ሞርሲ እንደማይወርዱ አስታወቁ፤ በግጭት ሕይወት ጠፋ



ከአንድ ዓመት በፊት  ከአፍሪካ ሀገሮች  የትስሃለ የመንግስት   በፋደንኝነት  ከስልጣን  መውረድ የታየማት  ሀገር  አሁን  ለአፍሪካ  ሰላም  አያስፍልጋም የተባለ ይመስል  የፈረስቺው ሊቢያመልሳ ሳትገነባ   ግብጽም  አሻፈርኝ ብላ መነሳቷ ጣም ያሳዝናል    ፡፡  

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ በቴሌቪዥን ንግግር ባደረጉበት ወቅት፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም - ካይሮ
 
 
ፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ - ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
የግብፅን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል - ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
 
 
የግብፅን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል - ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
በሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
 
 
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
ወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና  የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡
VOA