lørdag 2. mars 2013

የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ እና ትርጉሙ



ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፈለ ከተማዎች የወያኔ መንግስት ፓሊሶችና ደህንነቶች በሙስሊሙ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር ዝርፊያ የተቀላቀለበት አሸባሪ ብርበራና ፍተሻ ሲያካሄዱ ሰንብተዋል። ይህ ብርበራ በአይነቱ ፍጹም ከሆነ የወሮባላ ተግባር የተለየ እንዳልሆነ የደረሰባቸው፣ ያዩና የሰሙ ሁሉ የሚመሰክሩት ነው።
የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለይስሙላ እንኳን ያልያዙ ጭንብል ያጠለቁ ፓሊሶችና ደህነነቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በር እየበረገዱ በመግባት ቅዱሳን መጸሃፍትን፣ ሞባይልን፣ ቴሌፎኖን እና ወርቅ በግፍ መዘረፋቸውን ሰለባዎቹ አረጋግጠዋል። ይህ በእነዚህ ንጹሃን ሙስሊም ወገኖች ላይ ከተፈጸመው ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ ተጨማሪ መሆኑ ነው።
የእነዚህን አሳዛኝ ግፈኛ ተግባር የሰማው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዜናውን በየካቲት 14 ቀን 2005 አ.ም ምሽት ዘግቦ ነበር። በዚህ ዘገባ ላይ የቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ የሰለባዎቹን ምስክርነትና አስተያየት ብቻ ማቅረብ ተገቢ ያልመሰለው ፕሮፌሽናሉ ጋዜጠኛ፣ ሚዛናዊ ዘገባ  ለማቅረብ ድርጊቱ ተፈጸመባቸው ወደተባሉት ክፍለ ከተማዎች የፓሊስ አዛዦች መደወል ነበረበት። ይኼኔ ነበር ጋዜጠኛው ሳጅን ዘመድኩንን ያገኘው። ይህን የመንግስት ወንጀል እንዲያስተባብሉ እድል የተሰጣቸው ሳጅን ዘመድኩን የሰጡት መልስ ሰዋዊ ሳይሆን አውሬያአዊ   ነው ማለት ይቻላል።
የተሰራውን ግፍ መዘገቡ ያናደዳቸው የፖሊስ አዛዦች ጭራሹኑ ጋዜጠኛውን ራሱን አሁን መጥቼ አስርሃለሁ የሚል መልስ ነበር የሰጡት። እብሪተኛው ሳጅን ጋዜጠኛው እንኳን ዋሽንግተን መንግስተ ሰማያትም ገብቶ እንደማያመልጠው ካዛቱ በኋላ ቃለ ምልልሱ አለቀ።
ይህን ቃለ ምልልስና የሳጅን ዘመድኩን ዛቻ ስንሰማ ቅጽበታዊ ምላሻችን ሳቅና መገረም ሊሆን ይችላል። ከዚህ የደንቆሮ ሃሳብ ከሚመስል አስቂኝና አስገራሚ አነጋገር በስተጀርባ ግን በእጅጉ የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስና የሚያስቆጭ ትርጉም አለው። የሳጅን ዘመድኩን ጥያቄ አመላለስ የልዩ አጋጣሚ ጉዳይ (Isolated Event) አይደለም። እንደዚያ ከመሰለን ክፉኛ ተሳስተናል። በሳጅን አንደበት የሰማነው አውሬ ወይም የህወሃት ድምጽ ህዝባችን በእየለቱ ቁም ስቅሉን የሚያሳየውን የወያኔ የየእለቱን ዘረኛ ቋንቋ እና ተግባር ነው። ሳጅን ዘመድኩን የተናገረው የሰለጠነበትንና ወያኔ የወሰነውን ነው በእሱ ልሳን የሚናገረው።
ወያኔዎች የፈለገንን አድርገን አዋርደን እንገዛችኋለን፤ ምን አባታችሁ ትሆናላችሁ ነው የሚሉን በወያኔኛ ቋንቋ። ሳጅን ዘመድኩን እንደምንገምተው ደንቆሮ አይደለም። ወያኔ ውስጥ ያደገ ወያኔኛ የተማረና የሰለጠነ፣ ሁሉንም ጣቢያዎች ከሚያዙት ሰዎች አንዱ ነው። ትእዛዝ ፈጻሚ ወያኔ ነው። ህዝብ ደሞዝ የሚከፍለው የህዝብ ተቀጣሪ ነኝ ብሎ አያምንም። እንደሁሉም ወያኔዎች እየዘረፈ የሚኖር ሽፍታ ነው። ህግና ህገ-መንግስት ለጌጥ የተቀመጠ መሆኑን ወያኔዎች ሁሉ ያውቃሉ። ተናግረውታልም።
በሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊ አነጋገር ስቀን ከሆነ የሳቅነው በራሳችንና በህዝባችን ሰቆቃ ነው። በራሳችን ውርደት ለመሳለቅ አይተናነስም።ሀገራችን በእንደ እነ ሳጅን ዘመድኩን ያሉ ሰዎች ነው የምትመራው። ትልቅ ውርደት ላይ ነን። ሀገራችን ከውረደት፣ ህዝባችንን ከሰቆቃ የማዳን ግዜው አሁን ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ምርጫችን ሁለት ነው። ወይ “ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል እያልን የቁም ሞት ኑሮአችንን መኖር” አሊያም ወያኔን አስገድደንም ሆነ አስወግደን የሚገባንን የኩሩ ህዝብና ሀገር ስብእናችንን ማስመለስ እና ሀገርን ከማዳን ከሞራላዊ ግዴታ ተጠያቂነት ነጻ የመሆን።
እንዳንሳሳት! የሳጅን ዘመድኩን አራዊታዊና እብሪታዊ ቋንቋ ወያኔያው የእለት ተእለት ዘይቤ  ነው። ስለዚህ ጀንበር ቁልቁል ሳትጠልቅብን ወያኔን አስገድዶ ለመጣል ከሚንቀሳቀሰው ህዝባዊ ሃይል ጋር በመሆን የመታገያ ጊዜው አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

fredag 1. mars 2013

የገደሏት እና የሚገሏት የሚበሉባት ሃገር – በአያና ከበደ | Unity for Democracy and Justice Party ( Andinet)

የገደሏት እና የሚገሏት የሚበሉባት ሃገር – በአያና ከበደ | Unity for Democracy and Justice Party ( Andinet)

የውያኔ መንግስት ያሰበው ሆነለት



የ6ኛ ዙር የጳጳስ ምርጫ እንደተለመደው የማጭበርበር ልምዳቸውን በተግባር ለይ  ለማዋል አንዳሰቡት የስራልምዳቸውን  በተግባር ብላይ አዋሉ   ውያኔ እውነትን ገልብጦ ለማውራት  በዓለም ተውዳዳሪ የማይገኝልት የወራሪወች ስብስብ መሆኑን  ማንም የይክድ ነው  ፡፡
 በዘገባው መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የንቅዘቱ መፈልፈያ ማህጸን ነው፡፡  ገዢው ኣስተዳደር በጣሙን የገዘፈ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በቴሌ ላይ ኢንቬስት ቢያደርግም፤በአፍሪካ ሁለተኛው የቴሌፎን ስርጭት ዝቅተኛ የሆነበት ሃገር ከመሆን አላዳነውም፡፡ በጣም አናሳ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ከመሆንም አልፎ፤ከተጠያቂነት ነጻ የሆነ የዘረፋ ማእከል ነው፡፡በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ታዛቢዎች ድርጅቱ በሙስናና በንቅዘት የተገነባ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ በየትኛውም የአገልግሎት አሰጣጥ መመዘኛ ተጎታችና እርካታ ይሉት አገልግሎት የሌለው በየጊዜው በሚነደፈው የሙስና እቅድ ውስጥ ተውተፍትፎ አገልግሎቱ እርባና ቢስ ነው፡፡ የፍትህ ስርአቱም ቢሆን ሕብረተሰቡን በነጻ እንዳያገለግልና የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ተደርጎ በገዢው ኣስተዳደር ንጹሃንን በመወንጀል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በመግታት አገዛዙ ከመንበሩ ሳይለቅ የሚቀጥልበትን ሁኔታ የሚተገብር የፍትህን ስርአት የጣሰ ነው፡፡ ይህም በህጋዊ ኢፍትሃዊነት ብቻ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ለጉቦና ለንቅዘት ተጋልጦ ያለ አንድ የገዢው መንግስት የጦር መሳርያ ነው፡፡ ገዢው መንግስት በስልጣን መቆየቱን እንጂ ለሃገርና ለህዝብ እድገትና ልማት ጨርሶ ደንታ የሌለው በመሆኑ ከጉቦ ውጪ አንዳችም ጉዳይ በስርአት አይከናወንም: የዚህም ሂደት ዋናው አስፈጻሚ ሞተር ገዢው ፓርቲና ጀሌዎቹ ናቸው፡፡  

ዘ-ሐበሻ ኦክቶበር 11 አቡነ ማቲያስ መንግስት አቡነ ጳውሎስን ለመተካት ካስቀመጣቸው ጳጳሳት አንዱ ናቸው በማለት ዘግባ ነበር

ዘ-ሐበሻ ኦክቶበር 11 አቡነ ማቲያስ መንግስት አቡነ ጳውሎስን ለመተካት ካስቀመጣቸው ጳጳሳት አንዱ ናቸው በማለት ዘግባ ነበር

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይልና የኢሕአዴግ ጦር በጭርቆና በረሃ ውጊያ ገጠሙ ተባለ

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይልና የኢሕአዴግ ጦር በጭርቆና በረሃ ውጊያ ገጠሙ ተባለ

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይልና የኢሕአዴግ ጦር በጭርቆና በረሃ ውጊያ ገጠሙ ተባለ

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይልና የኢሕአዴግ ጦር በጭርቆና በረሃ ውጊያ ገጠሙ ተባለ

በአባይ ግድብ ዙሪያ (ግርማ ካሳ)

በአባይ ግድብ ዙሪያ (ግርማ ካሳ)