torsdag 28. februar 2013
አንድ አድርገን: “ምርጫ ውስጥ ስካተት አትርሱኝ” አቡነ ጎርጎርዮስ
አንድ አድርገን: “ምርጫ ውስጥ ስካተት አትርሱኝ” አቡነ ጎርጎርዮስ: (አንድ አድርገን ህዳር 11 ቀን 2005 ዓ.ም)፡- “ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ፤ ክብር ፤ ባህል ፤ እምነት ፤ሥርዓት ፤ መንግሥትና ቋንቋ ያቋቋመች ፤ የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ፤ ከሔኖክ ፤ ከመልከ ጼዲቅ ፤ ከ...
አንድ አድርገን: ለስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ 800 መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ
አንድ አድርገን: ለስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ 800 መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ: ምርጫው የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ይፈጸማል (Reporter :- ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም....
ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች
… በእኛ ዘመንም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ጎራ የተመደበችበት ዘመን ነው። ይህን ክፍፍል ወደ አንድነት ለማምጣት የመካነብርሃን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ድርሻ ተወጥታለች፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ስርዓትም መጠበቅ ቅድሚያ ትሰጥታለች። ስለዚህም ስላሴን እናመሰግናለን። በሻርለት ኖርዝ ካሎራይና የምትገኘው መካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13 ዓመታት በገለልተኛነት መኖሯዋ የታወሳል። በገለልተኝነት እንድትቆይ ያስገደዳትም ዋናው ምክንያት ለአለፉት ሃያ አመታት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ማዕከል በማድረግ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ በተዋህዶ ይመለሳል በማለት ነበር። በተለይ ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና ለአለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሲካሄድ የቆዬው የሰላም ድርድር ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ምኞታችን ፍጹም ነበር። ሆኖም ከዛሬ 21 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው አካል በቤተክርስቲያናችን ላይ ያስገባውን እጅ መሰብሰብ ባለመቻሉና ለፍላጎቱም መጠቀሚያ የሚሆኑ ለግል ጥቅምና ስልጣን እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ደንታ የሌላቸውን አንዳንድ አባቶች ከጎኑ በማሰለፍ ብዙ የተደከመበትና ተስፋ የተጣለበት የሰላም ድርድር ያለውጤት እንዲቋጭ አድርጓል። ስለዚህ የመካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያናችን በገለልተኛነት መቆየት የታሰበውን አንድነት የሚያመጣ ሳይሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሳተ አካሄድ በማጠናከር ዕምነታችንንና የቤተ ክርስቲያን ስርዓታችን የሚያፋልስ በመሆኑ ለማስተካከል ተገዳለች። ይቀጥላል…
|
የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
onsdag 27. februar 2013
የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ደህንነት መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ከአገር እንዳይወጡ ማዘዙ ተዘገበ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የትኬት እና 30 የኤርፖርት ሰራተኞችን ከስራ ካባረረ በሁዋላ ከአገር እንዳይወጡ ማገዱን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለኢቪዥን ኢሳት ዘገበ። እንደ ኢሳት ዘገባ ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሀብታሙ ጫኔ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ኢማን ያሲን፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛ ኤፍሬም፣ ይገርማል ታደሰ፣ ሰለሞን ይብራህ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፣ አየር መንገዱ ለደህንነት እና አሚግሬሽን መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ አሳግዷል።
ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ ሲታገዱ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆን፣ የድርጅቱን ሚስጢራዊ መረጃዎች የአገር ጠላት ለሆኑት የሽብርተኞች ሚዲያዎች ለኢሳት እና ለፍትህ ጋዜጣ መስጠታቸው፣ እንዲሁም የባለራእዩን መሪ የመለስ ዜናዊን ራእይ ለማሳካት በሚል የተነደፈውን የስድስት ቀን የነጻ የስራ አገልግሎት እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን የሚሉት ይገኙበታል ብሉአል ኢሳት። የሰራተኞቹ ፓስፓርት ቁጥር ለኢሚግሬሽንና ደህንነት ክፍል በመላኩም ሰራተኞች ከአገር ለመውጣትና ራሳቸውን ለማዳን እንዳልቻሉ ዘገባው አመልክቱአል።
ኢሳት እንደዘገበው አካሉ አሰፋ፣ አንተሰናይ አማረ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ ኤደን ካሳየ፣ ኢማን ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ሶሎሞን በቀለ፣ አይዳ ዘልኡል፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ አንዱአለም ግርማ፣ ብርሀኑ ሰሎሞን፣ ቸርነት አለሙ፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሂሩት መለሰ፣ ቅድስት አበራ፣ ቅድስት ከበደ፣ ማትያስ አድማሱ፣ መቅደስ አበራ፣ ሜላት አስራት፣ ትንግርት ደምሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሰሚራ አማን፣ ተዘራ ወርቁ፣ ወንዶሰን ሀብቴ፣ ዮሀንስ ፍሰሀ እና አልአዛር ተክለ ሚካኤል ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ከተላለፈባቸው መካከል ይገኛሉ ብሉአል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ዘርን መሰረት ባደረጉ ጥቂት ግለሰቦች እንደፈለገው እንደሚሽከረከርና ከአንድ ዘር ውጪ ያሉ ሰራተኞች ደግሞ ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው እንዲሁም ከስራቸው እየተባበሩ እንደሆነ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ዘርን መሰረት ባደረጉ ጥቂት ግለሰቦች እንደፈለገው እንደሚሽከረከርና ከአንድ ዘር ውጪ ያሉ ሰራተኞች ደግሞ ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው እንዲሁም ከስራቸው እየተባበሩ እንደሆነ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል።
ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ
ባለፈዉ ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓም ዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዉስጥ የሚኖሩ ትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በወንድሞቻቸዉና በእህቶቻቸዉ ላይ በማድረስ ላይ ያለዉን ግፍና መከራ በመቃወም ዋይትሀዉስ ፊትለፊት በሚገኘዉ ላፋየት ፓርክ ዉስጥ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉን ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚገኘዉ የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢ በላከልን ዜና ገለጸ። በዚህ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎች በብዛት በተሳተፉበትና ፕሬዚዳንት ባራክ አባማ በሚወጡበትና በሚገቡበት ዋነኛዉ የአሜሪካ ቤተመንግስት በራፍ ላይ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሐይማኖት አባቶች፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሲቪክ ድርጅቶቸ ተወካዮችና ብዛት ያለዉ የዲሲ፤ የቨርጂኒያና የሜሪላንድ ነዋሪ ህዝብ ተገኝቷል። ሰለማዊ ሰልፉ ከፍተኛ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የነገሰበትና የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዘመናት ተከባብሮ የኖረዉን የእስላሙንና የክርስትያኑን ህብረተሰብ ለማጣላት የሚያደርገዉን ሙከራ ያከሸፈ እንደነበር ዘጋቢያችን አክሎ የላከልን ዜና ያስረዳል። በዕለቱ ሰልፈኛዉ ይዞ ከወጣዉ መፈክሮች ዉስጥ “እስላሙና ክርስቲያኑ አንድ ነዉ” ፤ ‘’የእስላሙ መብት ሳይከበር የክርስቲያኑ መብት አይከበርም” ኡስታዝ አቡበከር እኛ ነን” የሚሉና ሌሎችም የወያኔን አላማ መክሸፍ የሚጠቁሙና ጠንካራ መልዕክት ያዘሉ መፈክሮች ይገኙበታል።
በአያና ከበደ ከኖርዌይ፡ አገርማለት
አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየትከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት የሚጥቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲጋኝባት በማድረጉ አገር እየጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆንች እናት ማለት ነው ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኒ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህንትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠያደራ ገንዘብ ነው ፡፡
ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!
በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)
ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ በፍቅር አብረን ኑረናል፤ የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
|
Why this ad?Ads –
0% full
Using 0.1 GB of your 10.1 GB
©2013 Google - Terms & Privacy
Last account activity: 1 day ago
Details |
People (2)
Show details
Ads – Why these ads?
Maria Arredondo
Ute med ny singel: Det jeg har gitt fra meg. Hør den nye singelen her!
|
Abonner på:
Innlegg (Atom)