
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ ሰዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይ የእስልምና እምነት ተወካይ፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን አባትና አንድ ከኢትዮጵያ ከመጣ ሳምንት ያልሞላዉ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታይ ያደረጉት ንግግር የብዙዎችን ስሜት የኮረኮረና ቀልብ የሳበ ነበር። ሁለቱ የሐይማኖት መሪዎች ባስተለላፉት መልዕክት ዉስጥ በኢትዮጵያዊነት የምንጋራቸዉ ብዙ እሴቶች አሉን ስለሆነም በሐይማኖት ተለያይተን የወያኔን ፍላጎት አናሟላም የሚል ጠንካራና የኢትዮጵያዉያንን ማንነት በግልጽ የሚያሳይ መልዕክት ይገኝበታል።
በየሳምንቱ ቃሊቲ ድረስ እየተጓዘ የትግል ጓደኞቹን ሲጠይቅ እንደነበረ የተናገረዉ ከኢትዮጵያ የመጣዉ ወጣት ደግሞ በእስር ላይ የሚገኙት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላት ትልቅ ጭንቀት መታሰራቸዉና በወያኔ ወታደሮች መሰቃየታቸዉ ሳይሆን የእነሱ ትልቅ ጭንቀትና ስጋት ይህ የተጀመረዉ ትግል እንዴት ከግቡ ይደርሳል የሚለዉ ጥያቄ መሆኑን ተናግሯል። ይሄዉ ወጣት ንግግሩን በመቀጠል በቅርቡ ወያኔ ክርሰቲያኑንና እስላሙን ህብረተሰብ ለማደናገርና የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱ እንዲጣላ ሆን ብሎ በሰራዉ “ጅሀዳዊ ሃረካት” በሚባል የማታለያ ወጥመድ ዉስጥ ኢትዮጵያዉያን ተሳስተዉ እንዳይገቡ የትግል ጓደኞቹ ከእስር ቤት ያሰተላለፉትን መልዕክት ለሰላማዊ ሠልፈኛዉ አስተላልፏል። በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፈኛዉ ለአሜሪካ ህዝብ፤ ለአሜሪካ ኮንግሬስ፤ ለዋይትሀዉስና ለአሜሪካ ህዝብ መልእክቱን ካስተላለፈ በኋላ ሳንለያይ እጅ ለእጅ ተያይዝን ይህንን የጀመርነዉን ትግል ከግቡ እናደርሳለን የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ወደየቤቱ ሄዷል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar