torsdag 28. februar 2013

ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች


Ethiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod
… በእኛ ዘመንም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ጎራ የተመደበችበት ዘመን ነው። ይህን ክፍፍል ወደ አንድነት ለማምጣት የመካነብርሃን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ድርሻ ተወጥታለች፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ስርዓትም መጠበቅ ቅድሚያ ትሰጥታለች። ስለዚህም ስላሴን እናመሰግናለን። በሻርለት ኖርዝ ካሎራይና የምትገኘው መካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13 ዓመታት በገለልተኛነት መኖሯዋ የታወሳል። በገለልተኝነት እንድትቆይ ያስገደዳትም ዋናው ምክንያት ለአለፉት ሃያ አመታት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ማዕከል በማድረግ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ በተዋህዶ ይመለሳል በማለት ነበር። በተለይ ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና ለአለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሲካሄድ የቆዬው የሰላም ድርድር ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ምኞታችን ፍጹም ነበር። ሆኖም ከዛሬ 21 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው አካል በቤተክርስቲያናችን ላይ ያስገባውን እጅ መሰብሰብ ባለመቻሉና ለፍላጎቱም መጠቀሚያ የሚሆኑ ለግል ጥቅምና ስልጣን እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ደንታ የሌላቸውን አንዳንድ አባቶች ከጎኑ በማሰለፍ ብዙ የተደከመበትና ተስፋ የተጣለበት የሰላም ድርድር ያለውጤት እንዲቋጭ አድርጓል። ስለዚህ የመካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያናችን በገለልተኛነት መቆየት የታሰበውን አንድነት የሚያመጣ ሳይሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሳተ አካሄድ በማጠናከር ዕምነታችንንና የቤተ ክርስቲያን ስርዓታችን የሚያፋልስ በመሆኑ ለማስተካከል ተገዳለች። ይቀጥላል…

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar