onsdag 25. februar 2015
tirsdag 17. februar 2015
Addisua Ethiopia : የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመ...
Addisua Ethiopia : የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመ...: February 14, 2015 | Filed under G7 Editorial , አማርኛ | Posted by admin አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝ...
የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ
አርበኞች
ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ
የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው።
እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣
የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም
መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ
ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል
ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።
ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
Addisua Ethiopia : የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
Addisua Ethiopia : የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ: ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም :-<<ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል>...
የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
ሌሎችን የ አንድነት አባላትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት፦ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አፈ ጉባዔ አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ናቸው፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል የቀድሞዎቹ የአንድነት አመራሮች። በዚህም መሰረት በርከት ያሉ የአንድነት አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲን የአባልነት ፎርም መሙላታቸው ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት፦ ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ከሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ-“በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው” ሲል አንድነት ፓርቲ አስታወቀ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ስርዓቱ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚመች የአስተሳሰብ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ ፣ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው ብሎአል። የምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለማፍረስ የወሰደውን እርምጃ አጥብቆ የኮነነው አንድነት፣ አሁን ባለው ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ተቀበረዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን አስታውቋል። አባሎቹ ይህን ህገወጥ እርምጃ በፅኑ እየተቃወሙ ለነፃነትና ለኢትዮጵያዊነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመከፍል ዝግጁ መሆን እንደሚኖርባቸው አሳስቧል፡፡ ምርጫን በተመለከተ ፓርቲው አቋሙን ሲገልጽ፣ በአምስት ዓመት የሚደረግ ክብረ በዓል አድርጎ ለማድመቅ እና የህዝብ ሀብት ለማባከን በሚደረግ ሂደት ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ፓርቲ መመስረትም ሆነ አሁን ካሉት ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ መታገል የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎአል፡፡ በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው የሚል ፅኑ እምነት መያዙን የሚገልጸው አንድነት፣ የፓርቲ ፖለቲካ አላበቃም ብለው የሚያምኑ የአንድነት አባላት ካሉ በራሳቸው ነፃ ውሳኔ ወደ ፈለጉት ፓርቲ ተቀላቅለው የመታግል መብታቸው መጠበቁንም አስታውሷል። ህዝቡ የትግሉ ባለቤት ሆኖ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የፓርቲው አባላት ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቁርጠኞች መሆናቸውንም መግለጫው ጠቅሷል። አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲፈርስ መደረጉ ብዙ ኢትዮጵያውያንን አበሳጭቷል።
5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላትና 2 ፓይለቶች ጠፉ
Feb 06, 2015
ጥር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት
ሳምንት በፊት 5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንዲሁም 2 ፓይለቶች ከድሬዳዋ አየር ሃይል
ጠፍተዋል። የጥበቃ አባላቱም ሆነ ፓይለቶቹ ያሉበትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ይህንን
ተከትሎ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከመቶ አለቃ ማእረግ በላይ ያላቸውን አየር ሃይል አባላት ሰብስበው ግምገማ አካሂደው
ነበር።
ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።
ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።
The 60th Birthday celebration of Andargachew Tesige in Oslo Norway
mandag 16. februar 2015
ሰበር ዜና – ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ፣ ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው ከትግራይ፣ እስከ ሞያሌ ጫፍ ዕጩ ማቅረቡ ለገዥው ፓርቲ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኖበታል ያሉት ኢ/ር ይልቃል በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረጉት ጫናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ሰይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ 23 ዕጩዎችን አቅርበናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ሳይቀር በሚዲያ ሲነገርላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት በቴሊቪዥን ቀርበው ‹ሰማያዊ በተደጋጋሚ ብንነግረው አልሰማም፣ በመሆኑም ሰኞ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል› ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰማያዊ በምርጫው እንዳይሳተፍ ችግር መፍጠር እንደሚፈልጉ ነው፡፡›› ሲሉ ፓርቲው ላይ እየተፈጠረበት ያለውን ጫና ገልጸዋል፡፡
የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በዛሬው ዕለት በኢቢሲ ቀርበው ሰማያዊ ይቅርታ ባለመጠየቁና ማስጠንቀቂያዎችን ባለመቀበሉ ነገ ሰኞ ጥር 9/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያስተላልፋል ብለዋል፡፡
ከሌሎች ፓርቲዎች ሰማያዊን በመቀላቀል በፓርቲው ምልክት ለመወዳደር የወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ መደረጉና በሌሎች ዕጩዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረሲት ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆነው አቶ ግርማ ቢተው በፈረሲት ወረዳ ፖሊሶች መያዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በገዥው ፓርቲ ደህንነቶችና ፖሊስ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጾአል፡፡
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው። በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don't support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል:: እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል። ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን! ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!! የወጣቶች ክፍል |
Abonner på:
Innlegg (Atom)