mandag 29. april 2013

በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ለ ሁለተኛ ጊዜ በ ኦስሎ ውርደት ተከና…

በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ለ ሁለተኛ ጊዜ በ ኦስሎ ውርደት ተከና…


 
ውሸት የማይገደው የወያነ ጉጅሌ ዛሬስ ምን ዪሉ ይሆን      ቦለመሸጥ   የሚያስችል አቅም አልንውበራቸውም ለህይወታቸእውም   መትረፍ    ኖሮዊይ ያለትን የፕሊስ ሰራዊት  በመጠቀም ነው   ህይ ውታቸው የተርፈው . ደግመው በአውሮፓ ውስጥ  የቦንድ ሽያጭ . ማደረግ ቢያስቡ እንኳን   ማድረግ እንደማይችሉ  ፡  በቅረቡ የተቋቋመው  ለወገን ደርራሽ ግብረሁይል   በመባል የሚጠራው   የውያኔን ስራውች ግበንዳይመቱእና ከተፈለገም  እገርቤትድ  ደርስ በተልያዩ ስልቶቹ  ውያኔ በቁጥጥር፡ ስር ማደረግ የሚችል   ገብግረሀይል  ኖሮዊይ  ውስጥ፡ መኖሩን  በአጋጣም  ለመግለጥ እወዳለሁ ፡፡
ይህ ገብረሀል  በተቁቋመ አንድ፡ወር  ባልሞላ ውስጥ ሁለት ድሎችን  በዓለም አቀፍ ዜና አስመ ዝግባል    ለውደፍትም የሚሰራቸው  ስራወትች  በጣም፡አኩሪ አንደሚሆኑ አያጠራጥርም .፡፡
ስለዚህ ግብረኅይል  ያየሁትንም   ከሞላጎደል  መገለጽ እፈልጋለሁ ..ቀኙ፡28 042013  እ.አ .ኤ  አለቱ አሁደ  ከአንደቀን በፊት  መሆኑነው  ክጧቱ 10.30 የኦስሎ  ከተማ  በተለይም  ኦስሎ ጋላሪ በመባል የሚጠራው፡ቦታ  በቡድን  በቡድን በጋንታ መሪ የሚመሩ  በመሰለ   አሰላነፍ  በመልክ አይቻቸው የማለቅቀና አንዳንዶች  የኦስሎ  ከተማ  ኗሪወች  ከተማዋ  ተጥለቅልቃለች ፡እኔም  ነገሩ ሰለገረመኝ፡  ከአንደቦታላይ  ቆም ብየ ለማየት   በመወሰን   ወዳንድ  ካፍተሪያ  ጉራ አልጉና  ነገሩ ምንደነው በማለት እራሴን በመጠየቅ .የያዝኩትን ሻይ  ጠጥቸ ሳልጨርስ አንደ  በከተማው የታውቁ በህዥቦጭም ዘንድ ተውዳጅነት ያላቸው ሰውየ ከአንድ ወጣጥ፡ጋር  ኮምፒተር  ላይ ስራ እየሰሩ ሻይ ይጠጣሉ›  እስኺ፡ነገሩ፡ምን እንደሆነ ልጠይቃቸው ቢየሳመንታ  ባካባቢው  ያየሁት  ሰው  በቅጥበት  ከቦታው  ወጥጧል   ስዓቴን ስመለከት 11፡.17 ፡18    ነበር  ለማጋነን ባይሆንብኝ እኔ ያየሁት   የድሮ የአንበሳክፍለጦር፡ ሰራዊትን በኖሮዊ ነው  በጣም ፈጣንና  የተቀናጀ  የጦር መሳሪያ ያላዘ ቆራጥ ስራዊት  እኔም እንዳቅሚ   ወደዚያው ተጓዝኩ   ከቦታው አንደደርስኩ  የወያኔ ደጋፊውች አና ሆድና ጀርባ ሆነው ለብዙ ዓንታት የቆዩት  ተቃዋሚወች  አብረው  ቁጭብለዋል እኔም ነግሩ ገርሞኝ   ይህ ያየሁት  በጣም  የሚያስፈራ  ሰራዊት   የአስታራቂ   ኮሚቴ ነወንዴ በማለት   እራሴን በመጠየቅ   ወደማውቃቸቅ አንድ የትቃዋሚ  መሪ ጠጋብየ  ሰላታ  በመስጠ ለይ እያለሁ  አንደ ፊቱ  የተኮፋተረ ሰው መታና ለቫክት  እንህን ሰውች አሰውጡልኝ፡ ሰል ሰማሁት  ምንለማለት ነው ብየ ሰውየውን ስጠይቅ  አንደ የወያኔ ደጋፊ መጣና ይሒኝ፡ሰውየ አስወጡጥ፡ የሚል መልክት  ልፖሊስ   ይሰጣል፡ ፖሊስም  መጣና  ባአገርኛው ቋንቋ አልሳምን ጎ ኦት  አለ  ህዝቡም አንውጣም   በማለት  ጉርምርምታ አሰማ  የፖሊስም ሀይል እየጨመረሄድ  ህዝቦችም  ተገርደ ወደውጭ፡ ውጡ፡ያያሰፈራ የነበረው ሰራዊት  ቦታውን  ተገዶጥሎ ሲወጣ፡እኔና ሁለት ውንደኦች  ከተወሰኑ ሴቶች ጋር  ቦታውን ብቆጥጥር ስር አደረግነው   እኔም ያያንበሳ  ክፍለጦር፡ሊሰራው ያሰበውን ስራ ለሰራለት  የቴድን ቀን ይስጠኝ፡ ከነሱ አልነይም  በተላዩ  መንገድ  ተጠቅሜ፡ ድል እንደምመታ  እርግጠኛ፡ነበርኩ  ሰራውም ተሰራ፡ውረውም ተውራ  ከሰራው ይልቅ ክውስጥ መሆኔ የስጠኝ ትልቅ ትምህርት  ቢኖር  ለአሰር አመታት የክል በደስታም  በመከራም  የማንለያይ ጓድኛ  ሌላሰው ኦኖ  በማገኘቴ  እኔም ሆንኩ ሌሎች ወንድሞቼ   በደንብ ከማታውቁት ሰው ጋር ያላችሁ ..ገንኙነት   የላላ ይሆን ጓድኛየ  በሌሎች አጋጣሚ ቢሆን አንደሚሞትልኝ  እርግጠኛነኝ  አይቸውም አለሁ  ይህግን በዘርላየ የተመሰረተ ሰለሁነ   ሌላሰው ሆኖ ነው ያገነሁት  ለመግባትለም  ምክናየት የሆነው የሱ ከዚያ  መገኘት ነው   እኔን ደፈሩ ማለት እሱን ፍሩ ማለት ሰለሁነ ለሱክብር ሲሉ ነው  ምንም መከራከር ያልፈለጉት  እኔን  እነኤ አዝናለሁ   እናንተግን ልትደሰቱ ይገባችኋል  ለምን ቢባል  ሁሉም  ነገሮች  በሱ በኩል ነበር  የሚላኩልን ..፡፡

የዕለቱ ዜናዎች » በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ


በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡
እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ  ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘ
ጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር  ስህተት በመኖሩን  በተማሪዎችና  በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡
በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡
ከረብሻው ጋር በተያያዘ ሚያዚያ 11 ቀን 2005ዓ.ም. በትምህርት ቤቱ አካባቢ ተኩስ መከፈቱና  በተፈጠረ ግጭትም 3 ተማሪዎች ቆስለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህን ዜና እስከዘገብንበት ድረስም ትምህርት ቤቱ በፌደራል ፖሊስ መከበቡ ተጠቁሟል፡፡
ይህንንም በሚመለከት የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አብዱ ካሣ ስለጉዳዩ ስናነሳላቸው አሁን ስለማልችል ከ30 ደቂቃ በኋላ መልሳችሁ ደውሉ ካሉ በኋዋላ ስልካቸውን በመዝጋታቸው  ምላሻቸውን  ማካተት አልቻልንም፡፡
ምክትላቸው አቶ አበራ ጉልማንም ለማናገር ጥረት ብናደርግም ስልካቸውን ጆሯችን ላይ ዘግተዋል፡፡

ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪ በዘመነ ሰላቶ


….ምንይልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ግዜ አበሻ…….
 ……….በግዜው ይህንና ይህንን የመሳሰሉ ልዩ መልዕክት ያላቸው የግጥም ቋጠሮዎች የተደረደሩት ወራሪው  የኢጣልያ ሰራዊት ከነበረው የቅኝ ግዛት ፍላጎት መስፋፋት በመነሳት በኢትዮጵያ ላይ አካሂዶት በነበረው ወረራ  የደረሰበትን ሽንፈት ለመግለፅ፤ በዘመኑ የነበሩ ነገስታትና ሰራዊታቸው ያሳዩትን ጀግንነት ለማወደስ፤ በአጠቃላይ  ባርነትን ፍፁም ሊቀበሉ ያልቻሉ ጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ዛሬ ላይ ሆነን የነፃነትን አየር ለመተንፈስ  መብቃታችንን ለመመስከር ነው። በእርግጥ ከዚያ ቀደም ይሁን ከዛ በሗላ የነበሩ አባቶቻችንም ቢሆኑ በየወቅቱ ግዜ  እየጠበቀ በተለያየ አቅጣጫ የመጣብንን ባእዳን ወራሪ በተደጋጋሚ አሳፍረው መመለሳቸው ባይካድም፤ በአድዋ ጦርነት  ግዜ የተገኘው ውጤት ግን፤ ለኛ ኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጥቁር ህዝቦች እንደ ነፃነት ተምሳሌት ሆኖ  ይጠቀሳል። በዚህም ድል መላው የጥቁር ህዝቦች እጅግ ከፍ ያለ ኩራት ሲሰማቸው ይኖራል። ከዚህ በተፃራሪው በዚያ  ቀውጢ ዘመን ራሳቸውን በጥቅማጥቅም ለማኖር ሲሉ ባርነትን አሜን ብለው በመቀበል ሀገርን ለጠላት አሳልፈው  የሰጡና በራሳቸው ወገን ላይ ፊታቸውን አዙረው የዘመቱ ጥቂጥ ባንዳዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። ዛሬም እነዚያ የሞሰለኒ  አሽከሮች ካደረሱብን በደል በላይ በከፋ መልኩ ሀገርና ታሪክን እያጠፉ ያሉት፤ የኢጣልያ ባንዳ ከነበሩት ከአቶ አስረስ  ተሰማ የልጅ ልጅ ሟቹ መለስ ዜናዊ ጀምሮ በርካታዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት የባንዳ ልጆች (ሰላቶዎች) መሆናቸውን  መገንዘብ ይኖርብናል።
(በ ይታያል እውነቱ) ሆላንድ

የትግሬ-ናዚዎች አዋጅ፦ “ዐማራን ከምድረ-ገፅ እናጠፋለን!” – ሞረሽ



. ናዚዝም በጀርመን ፣ ፋሽዝም በጣሊያን ቢቀበሩም በኢትዮጵያ ትንሣኤ አግኝተዋል (PDF)


ናዚዝም እና ፋሽዝም በአውሮፓ እንዲያቆጠቁጡ ምክንያት የሆናቸው አንድ ዓይነት መንስዔ ብቻ ነበር ብሎ ለመደምደም ያስቸግራል። ሆኖም ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት በተባባረው የእንግሊዝ እና ፈረንሣይ ኃይል ተደቁሳ፣ ወርራ ከያዘቻቸው የቅኝ ግዛቶቿ በተጨማሪ ከራሷም ግዛት እንድታጣ በመደረጉ፣ እንዲሁም ጦርነት መቀስቀሷ ምክንያት ተደርጎ ለአሸናፊዎቹ ለእንግሊዝ እና ለፈረንሣይ እንድትከፍል የተገደደችው የጦርነት ካሣ ቁልል ኢኮኖሚዋን መቀመቅ ከትቶት ሰለነበረ በጀርመኖች ዘንድ «ተጠቃን ፣ ተዋረድን ፣ የእኛ የነበረውን አሣጡን» የሚል ቁጭት እንዲፈጠር አድርጎ ነበር። ስለዚህ አዶልፍ ሒትለር እና የፖለቲካ አጋሮቹ ያንን የጀርመን ሕዝብ ቁጭት፣ የተከሠተውን ኢኮኖሚያዊ ችግር፣ እርሱንም ተከትሎ በጀርመን ሕዝብ ላይ የደረሠውን የተመሠቃቀለ የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ በፈጣን እና «በአስተማማኝ የጀርመን ብሔረተኝነት» መፍትሔ ለመስጠት እንደሚችሉ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ማዝነብ ጀመሩ። በቤኔቶ ሙሶሊኒ ይመራ ለነበረው ለጣሊያን ፋሽስቶች አነሣሥም አመቺ ሁኔታ የፈጠረላቸው ከሮም አገዛዝ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አዲስ ከተዋቀረችው የኢጣሊያ ሪፓብሊክ አመሠራረት ጀምሮ የዘለቀው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሲሆን ያም «ፈጣን ለውጥ እናመጣለን» ለሚሉ አጭበርባሪ ፋሽስቶች የተመቻቸ የፖለቲካ ድባብ መፍጠሩ አልቀረም።

ናዚዝም እና ፋሽዝም በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተፈጥረው በሁለት የተለያዩ ሥያሜዎች ቢጠሩም መገለጫ ባህርይዎቻቸው ተመሣሣዮች ነው። ናዚዝምም ሆነ ፋሽዝም የፓርላማ ዲሞክራሲን አይቀበሉም። ለእነርሱ ብሔረተኝነት የሚገለፀው በዘር (በጎሣ ወይም በነገድ) ላይ በተመሠረተ መሥፈርት ላይ ስለሆነ የርዕዮታቸው መሠረት ሁሉ ዘረኝነት ነው። ለናዚዎች እና ለፋሽስቶች የቡድን ማለትም «የጎሣ ወይም የነገድ» መብት ከሁሉም መብቶች በላይ ስለሆነ የግለሰብ መብት ሥፍራ የለውም። በተለይ ደግሞ ናዚዎች «ምርጥ የሆነው የአርያን ዘር ነን» ብለው ስለሚያምኑ ዘራቸውን ከሌላው ዘር ሣያቀላቅሉ ማራባት መርሆዋቸው ነበር፣ ነውም። ናዚዎች ለፖለቲካ ግባቸው መቀስቀሻ ፀረ-አይሁዳዊነት ዋና መፈክራቸው ስለነበረ ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዶችን በአሠቃቂ ሁኔታ በግፍ ጨፍጭፈዋል። ለፋሽስት ጣሊያኖች ዋና ጠላታቸው «ኢትዮጵያዊ» በተለይም ደግሞ «ዐማራ» የሚባለው ዘር ስለነበረ ኢትዮጵያን በወረራ በያዙበት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ፤ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በእሣት በማጋዬት እና በሌሎችም አሠቃቂ መንገዶች ጨፍጭፈዋል። በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በፋሽስት ጣሊያኖች በብዛት የተጨፈጨፉት ዐማራዎች ነበሩ። ናዚዎች እና ፋሽዝቶች በነፃ ገበያ መርሆ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት አይቀበሉም። ስለዚህ የመሠረቱት የኢኮኖሚ ሥርዓት በዘር ትሥሥር እና በሥውር ሤራ ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ካፒታሊዝምን የጀርባ አጥንት አድርጎ የሚንቀሣቀስ የማፍያ ካፒታሊዝም ነበር። በፖለቲካ አመለካከታቸውም ዜጎቻቸውን ለፍፁም አምባገነናዊ አመራር ታዛዥ የሚያደርግ ሥርዓትን ያራምዳሉ። ስለሆነም የሊበራል ዲሞክራሲንም ሆነ በተፃራሪ የቆመው የግራ ርዕዮተ-ዓለም «ኮሚኒዝምን» አምርረው የሚጠሉ እና የሚታገሉ ነበሩ፣ ናቸውም። ሁለቱም እኒህን የርዕዮተ-ዓለማቸውን ምሦሦዎች ያቆሙት «ውሽት ሲደጋገም ወደ እውነቱ ይጠጋል» በሚሉት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ላይ ነበር። ከላይ የተዘረዘሩትን ለሚመለከት የትግሬ-ወያኔዎች ቀዳሚውን የርዕዮተ-ዓለም መሠረታቸውን ያገኙት ከጀርመን ናዚዎች እና ከጣሊያን ፋሽስቶች መሆኑን ለመገንዘብ ይችላል። ለትግሬ-ወያኔዎች ሁለተኛው የርዕዮተ-ዓለማቸው መሠረት ደግሞ የኮሚኒዝም አመለካከት ነው። አንድ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው «እንዴት ተደርጎ እኒህን ሁለት ፍፁም ተፃራሪ የሚመስሉ ርዕዮቶች አንድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት በተጣመረ ሁኔታ መርሆ አድርጎ መቀበል ይቻላል?» ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ ተገቢ ጥያቄም ይሆናል። መልሱ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔዎች በሚሄዱበት አቅጣጫ ከተሄደ ይቻላል፤» ነው። ለዚህ እንዲረዳ የትግሬ-ወያኔዎችን የመጀመሪያውን የ1968 ዓ.ም. ማኒፌስቶ በከፊል መመልከቱ ይጠቅማል።

የቀድሞው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የአሁኑ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) ወይም በተለምዶ አጠራሩ
«ወያኔ» በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ በግልፅ እንዳሠፈረው፦

«ትግራይ ኣክሱም እስከወደቀችበት ጊዜ ድረስ የኣክሱም መንግሥት እየተባለች ትጠራ ነበር። ኣክሱም ከወደቀች በኋላም እራሷን በማስተዳደር ለብዙ ጊዜ ብትኖርም ቅሉ ኣልፎ ኣልፎ ባካባቢዋ ለነበሩት ነገሥታት ግብር መክፈሏ አልቀረም። በኣፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ኃይሏ በርትቶ ባካባቢዋ የነበሩትን ነገሥታት በቁጥጥሯ ሥር አውላ ነበር። ይሁን እንጂ አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ ኣማካኝነት ትግራይ በሸዋው ማእከላዊ ግዛት ሥር ወደቀች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው የኣማራው የመሳፍንት ቡድንና ተከታዮቹ የትግራይን ነፃነት ገፈው የሕዝቧን አንድነት ያናጉት። ግልጽና ስውር በሆኑ ዘዴዎችም [ሸዋዊ ዘይቤዎች] የትግራይ ሕዝብ በድንቁርና ፣ በበሽታ ፣ በረሃብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት። በተለይም ትግሬነቱን በፍጥነት እንዲክድና ያለውድ በግድ “አማራ ለማድረግ” ያልሞከሩት ዘዴ ባይኖርም መሬቱ ተቆራርሶ ስለተወሰደበትና የተደራረበ ጭቆና ስለደረሰበት አገሩን ጥሎ ተሰደደ። ባጠቃላይ ባሁኑ ጊዜ ትግራይ ነፃነቷ የተገፈፈች ፣ መሬቷ ተቆራርሶ የተወሰደባትና የተወሳሰበ ችግር የደቆሰው ሕዝብ የሚኖርባት ጭቁን ብሔር ናት። (ገፆች v-vi)
ሀ – ራስ ን መጣል (ዲ -ሁማ ናይ ዜሽ ን )፦

ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሚሄደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ በሰፊው የትግራይ ህዝብ ላይ ድሕነት ፣ ረኃብና ውርደት እየተደጋገመ እንዲደርስ አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ ለረጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈጸምበት ቆይቷል። ይህም በደል ጨቋኝዋ የአማራ ብሔር ሆነ ብላ እንደመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን ፋሽስታዊ ደርግም በባሰና በመረረ መንገድ ቀጥሎበታል። ከዚህም የተነሳ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ኑሮው እንዲቆረቁዝ ተደርጓል። በዚህ ምክንያት የሥራ ማጣት ችግር ፣ ሽርሙጥናና ስደትን ከማስከተሉም በላይ ራስን መጣልና መንከራተት የትግራይ ሕዝብ ዕለታዊ ተግባሩ ሆኖ ይገኛል። ስለሆነም ሕዝቡ ተጠርጣሪና የተጠላ እንዲሆን በመደረጉ በህብረት መኖር የማይቻል ሆኖ ይገኛል። (ገፅ 15)

ለ – የህብረተሰ ቡ ወደኋ ላ መቅ ረትና ዕረፍት ማ ጣት

ሰፊው የትግራይ ህዝብ ሥራ አጥቶ በሽርሙጥናና በስደት ወ.ዘ.ተ. ብቻ

ሳይሆን በረኃብ ፣ በድንቁርናና በበሽታ እየተሰቃየ ይኖራል። እነዚህም ችግሮች ወንጀል እንዲፈጽም ይገፋፉታል። ለችግሩ መሠረታዊ ምክንያት ኢምፐርያሊዝምና ባላባታዊ ሥርዓት ይሁኑ እንጂ ጨቋኝዋ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚ ብዝበዛና የፖለቲካ ጭቆና ታክሎበት ነው። ከዚህም በላይ የሚያኮራው የህዝባችን ታሪክ ፣ ባህልና ቋንቋ እንደዳከምና ተዳክሞ እንዲጠፋ ወይም የአማራ ብሔር የገዢ መደብ ጥቅም እንዲጠብቅ የ3ሺ ዓመታት ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ይገኛል። ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሔር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ታሪክ እንደሌለው ሕዝብ እንዲያስቆጥረው የተደረገ የመንግሥት መመሪያ ነው። ቢሆንም የትግራይ ህዝብ ቂሙንና ተቃውሞውን በቁጣና በጥላቻ በብዙ መንገድ ደጋግሞ ገልጸዋል። ይሁንና ይህንን የመሳሰሉ አድሃሪ ድርጊቶች አሁን ያለው ፋሽስታዊ መንግሥትም ስለቀጠለበት ሰብዓዊ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ትግሉን አያቋርጥም። ጨቋኝዋ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋ እስካላቆመች ድረስ ህብረተሰብዓዊ እረፍት አታገኝም። (ገፆች 15-16)

ሀ – ዓላማ ውና ሥራው ፦

የትግራይ ህዝብ ብሔራዊ ትግል ፀረ-የአማራ ብሔራዊ ጭቆና ፣ ፀረ-ኢምፐርያሊዝም እንዲሁም ፀረ- ንኡስ ከበርቴያዊ ጠጋኝ ለውጥ ነው። ስለዚህ የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ሥርዓትና ከኢምፐርያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ማቋቋም ይሆናል።» (ገፅ 18)

ሰለሆነም ወያኔ የተመሠረተበት ዓላማ እና ተልዕኮ ከላይ በድርጅቱ ማኒፌስቶ በግልፅ የሠፈረው አቋሙ ነው። ወያኔዎች ተዋጊዎቻቸውን ከሚቀሰቅሱባቸው መፈክሮች «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ» የሚል ይገኝበታል፤ ትርጉሙም «የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቀበሪያ ይሆናሉ» ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬም ዐማሮችን በነገዳቸው ለይቶ መፍጀት ከዚህ የትግሬ-ወያኔዎች የትግል መግለጫ የመነጨ፣ ግቡም የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት እንደሆነ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባም።

2. የዐማራ ሕዝብን ሠቆቃ እና ህልውና ለመካድ «የዐማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ብሎ ማደናገር

ሠሞኑን ከጎልማሣዎቹ የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ ድርጅቶች ጀምሮ እስከ ጨቅላዎቹ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ድረስ እየተቀባበሉ በሚያቀርቧቸው መግለጫዎች ላይ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቀሉ» የሚል አዝማች ቃል አላቸው። ለመሆኑ «ዐማራ» የሚባል ነገድ እና ሕዝብ የለም ወይ? የትግሬ-ወያኔዎች እና ተባባሪዎቻቸውስ በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅሙት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ተግባር የለም? ችግሩንስ በዚህ መልክ አድበስብሶ ማቅረቡ እና ማደናገሩ «ለማን ደስ ይበለው» ተብሎ ነው? የተፈናቀሉት «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ከሆኑ እኮ አፈናቃዮቹ እና ጨፍጫፊዎቹም ሟቹ የወያኔዎቹ ጣዖት መለስ ዜናዊ ፣ የደቡቡ የወያኔ ሎሌ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ በመተከል እና በአሶሳ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው አህመድ ናስር ጭምር አማርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው የሚናገሩ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» ናቸው። ሰለዚህ «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች» የሆኑት ሹሞች «የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን አፈናቀሉ» ለማለት ተፈልጎ ይሆን? በተቃራኒው ግን እኒህ የፖለቲካ ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ወያኔዎች በሌሎች ነገዶች ላይ ለሚፈፅሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል በስም «ይኼ ነገድ ወይም ጎሣ በወያኔዎች ተጨፈጨፈ» ብለው መግለጫ ያወጣሉ። ስለሆነም እኒህ «በሕብረ-ብሔር ፖለቲካ እናምናለን» የሚሉት ድርጅቶች በሚያወጡት መግለጫ ግልፅ በሆነ ቋንቋ «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከሚሉ ድረስ መጠበቅ የለባቸውም። ምክንያቱም አሁን ለተጋፈጥነው ችግር መባባስ አንዱ ሠበብ «የዐማራ ነገድ የኢትዮጵያ ችግር ምንጭ እንጂ የችግሩ ሠለባ ሆኖ አያውቅም» የሚለው እና ላለፉት 40 ዓመታት የኢትዮጵያ የግራ-ዘመም እንዲሁም ራሣቸውን «የሕብረ-ብሔር ፖለቲከኞች ነን» ብለው የሚጠሩት በቀዳሚነት ሲያቀነቅኑት የቆዩት የፖለቲካ አመለካከት ያለማንም ሞጋች እንደወረደ በይሉኝታ ተቀባይነት አግኝቶ በመቀጠሉ ነው።

3. የትግሬ-ወያኔዎች እስከዛሬ በዐማራው ላይ ምን አደረጉ?

የትግሬ-ወያኔዎች ገና ክጥንስሣቸው ጀምሮ ለዐማራ ሕዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ያንንም የመረረ ጥላቻቸውን እስከ ዘር ማጥፋት በሚደርስ እርምጃ ከመግለፅ የቦዘኑበት ወቅት የለም። ይህ ያልተገለፀለት ሰው ቢኖር ከገሃዱ ዓለም ወጥቶ በተምኔታዊ የቅዠት ኅዋ ውስጥ ራሱን

የደበቀ ብቻ ነው። የትግሬ-ወያኔዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ ከፈፀሟቸው አያሌ ከሆኑት ናዚያዊ ተግባሮቻቸው መካከል ዋና ዋናዎቹን አለፍ አለፍ እያሉ መጥቀስ ለማስታወስም ያህል ይረዳል።

ገና ሲሽፍቱ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀሱበት የመጀመሪያዎቹ ሦሥት ዓመታት እነርሱ ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረጓቸው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። እንዲያውም ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለትግሬ-ወያኔዎች ግን እኒያ ሰዎች ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ እየለቀሙ ጨፈጨፏቸው።
ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ ወደ ጎንደር የመስፋፋት ጦርነት አድማሱን ሲያሠፋ የመጀመሪያ እርምጃው በወልቃይት እና ጠገዴ የሚኖሩ የጎንደር ዐማሮችን በጅምላ መፍጀት ነበር። እስከዛሬ ምን ያህል የወልቃይት እና የጠገዴ ዐማሮችን እንደጨፈጨፉ በአሃዝ ለይቶ ለማስቀመጥ ቢከብድም በ20 ሺህዎች የሚቆጠሩትን ከምድረ ገፅ እንዳጠፉ፣ ከ70 ሺህ የማያንሱትን ደግሞ ከጥንት አባቶቻቸው ርስት አፈናቅለው ስደተኛ እንዳደረጓቸው ይታወቃል። ወያኔዎች የጎንደር ግዛት የሆነውን የወልቃይት ፣ የጠገዴ እና የፀለምት አካባቢዎችን «የትግራይ ክልል» ብለው ነጥቀዋል። በአካባቢውም ከተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ያመጧቸውን የራሣቸውን ዘር አሥፍረውበታል።
ሥልጣን ከያዙበት ከግንቦት 1983 ዓም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ ዐማሮችን፦ «ነፍጠኞች፣ ትምክህተኞች፣ አድሃሪዎች፣ ጨቋኞች፣ የትግራይ ሕዝብ ደም መጣጮች፣ ወዘተርፈ» እያሉ ከአገራቸው አፈናቅለዋል፣ ጨፍጭፈዋል። በተለይም ከግብር አጋሮቻቸው ከሻቢያ ፣ ከኦነግ እና ከኦብነግ ጋር በመሆን በሐረርጌ (በበደኖ፣ በሐብሩ፣ እና ሌሎች ሥፍራዎች)፣ በአርሲ (በአርባ ጉጉ እና ጢቾ)፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በባሌ፣ በሲዳማ፣ በጌድኦ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በጉራፈርዳ፣ በመተከል፣ በአሶሳ እና በሌሎችም አካባቢዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በአሠቃቂ ሁኔታ ፈጅተዋል።
ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ «ብረት ማስፈታት» በሚሉት ዘመቻ ዐማራው ሙሉ በሙሉ ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጓል። በተለይም «የዐማራ ክልል» ብለው በሠየሙትና አብዛኞቹ የዐማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ይህንን ዘመቻ በበላይነት የመራው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ነው። ዛሬ ዛሬ የዐማራ ተወላጅ እንኳን የጦር መሣሪያ ይቅርና የብረት ጅንፎ ያለው ዱላ መያዝ ጦር መሣሪያ እንደመታጠቅ ተቆጥሮበት ራሱን ከትንሽ አውሬ የሚከላከልበት ዱላ እንኳን መያዝ አይችልም።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. ባካሄዱት «ሽፍታ ምንጠራ» ብለው በሠየሙት ዘመቻ ከዐማራው መካከል ንቃተ-ኅሊናቸው ከፍ ያሉትን እና «ለትግሬ-ናዚያዊ አገዛዝ አይንበረከኩም» ብለው የሚያስቧቸውን ዐማራዎች እየለቀሙ አሥረዋል፣ ደብዛቸውን አጥፍተዋል፣ ገድለዋል።
ከ1986 እስከ 1987 ዓ.ም. ዐማራውን በሦሥት መደቦች ከፋፍለው፦ የወያኔ ኮር አባል፣ ተራ ዜጋ እንዲሁም ቢሮክራት እና ፊውዳል ብለው መድበው መሬት አከፋፍለዋል። የመሬት ድልድል ሲያደርጉ በገጠሩ የዐማራ ማኅበረሰብ መካከል የመደብ ልዩነት በመፍጠር ዐማራው እርስ በእርሱ እንዲፋጅ ሲያደርጉ፣ በተለይም ደግሞ አብዛኛውን ዐማራ የኢኮኖሚ ዐቅሙ የተዳከመ እና ፍፁም በድነህት የሚማቅቅ ምስኪን አድርገውታል።
ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች «የጦር መሣሪያ ታጥቃችኋል፣ የኦሮሚያን መሬት ለግላችሁ አድርጋችኋል፣ የኦሮሚያ የቦታ ሥሞችን የዐማራ ስም አውጥታችሁላቸዋል፣ የከብት ዝርፊያ ትፈፅማላችሁ፣ ደን ትመነጥራላችሁ» እና የመሣሠሉትን ሠበቦች በመደርደር ከ12 ሺህ የማያንሱትን አፈናቅለዋቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ደግሞ የአካባቢው የወያኔ ሎሌ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ታጣቂዎች ፆታ እና ዕድሜ ሣይለዩ በአሠቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈዋቸዋል። የተፈናቀሉት ዐማሮች ከነበሩበት ሥፍራ ተባርረው ጎጃም ክፍለሀገር አገው ምድር አውራጃ ውስጥ ጃዊ የሚባል እጅግ ሞቃታማ እና በወባ ወረርሽኝ በሚጠቃ ወረዳ እንዲሠፍሩ ተደርገው አብዛኞቹ በወባ ወረርሽኝ እንዲያልቁ ተደርገዋል።
ከሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ወዲህ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች “የግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎች ናችሁ” ተብለው ከታሠሩት ከ37 በላይ የሲቪል ፣ የደህንነት ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የወታደር እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ዐማሮች ናቸው። በእኒህ እሥረኞች ላይ የወያኔ መርማሪ ፖሊሶች ካደረሱባቸው ዘግናኝ ግርፋት ዓይነቶች መካከል፦ የወንድ የዘር ብልት ማኮላሸት፣ በኤሌክትሪክ መጥበስ፣ ጥፍር መንቀል፣ ከባድ ድብደባ፣ በአስጨናቂ ሁኔታ በካቴና ጠፍሮ ማሠር እና ከጣሪያ ላይ ማንጠልጠል፤ እንቅልፍ መከልከል፣ በርሃብ እና በውኃ ጥም ማሠቃዬት፣ ጫካ ውስጥ ወስዶ ግድያ እንደሚፈፀምበትና ሬሣው ለአውሬ እንደሚጣል ማስፈራራት ይገኙባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በአካል የተሠቃዩት ሣያንስ እጅግ ቅስም-ሠባሪ ዘለፋ ለመስማትም ተገድደዋል፦ ከወያኔዎቹ አረመኔ ገራፊዎች ከሚወጡት ቃላት ውስጥ፦ “ትምክህተኛ ዐማራ፣ ግም ዐማራ ፣ ብስብስ ዐማራ፣ ሽንታም ዐማራ፣ ፈሪ ዐማራ፣ በኤድስ ቫይረስ የተበከለ ደም እንወጋሃለን፣ ከሃምሣ ጋይንት አንድ አጋንንት ይሻላል አንተ ሆዳም ጋይንቴ፣ ዘር-ማንዘርህን ቀሚስ አልብሰን የወጥ-ቤት ሠራተኛ አድርገን እንገዛዋለን፣ አንተ ደም መጣጭ ጎጃሜ እናቃጥልሃለን፣ ዘረ-ቆሻሻ ዐማራ፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ይገኝባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በወያኔው የጨረባ ፍርድቤት እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
እነዚህ ሁሉ የትግሬ-ወያኔዎች የዐማራ ጭፍጨፋ ድርጊቶች ከራሣቸው አንደበት እና ዘገባ ማረጋገጥ የተቻሉ ናቸው። በተለይም በ1999 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔዎች ባካሄዱት የሕዝብ ቆጠራ «አረጋግጠናል» ብለው ለሕዝብ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት ከ1989 እስከ በ1999 ዓ.ም. በነበሩት 10 ዓመታት ብቻ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ዐማሮች የደረሱበት አልታወቀም ብለዋል። በእርግጥ ይህ የአሃዝ አገላለፅ ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በራሣቸው በወያኔዎች የታመነውን ጉዳይ ከማስተባበል ይልቅ ከጨፈጨፏቸው የዐማራ ነገድ ተወላጆች መካከል ከዚህ ቁጥር ውስጥ ያልተካተቱት ምን ያህል እንደሆኑ ማጣራቱ ይበልጥ ትርጉም ይኖረዋል።

4.የእነርሱን የጥፋት እርምጃ ለመግታት እስከዛሬ ምን ተደረገ? ውጤት ተገኘበት ወይ?

የትግሬ-ወያኔዎችን ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ ለመመከት እና ዐማራውን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን በድርጅት በታቀፈ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉልህ እንቅስቃሴውን የመሩት ሟቹ መሪ ፕሮፌሠር አሥራት ወልደየስ ነበሩ። ፕሮፌሠር አሥራት የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን (መዐሕድ) በ1984 ዓ.ም. ከትግል ጓዶቻቸው ጋር ሲመሠርቱ የዐማራው ሕዝብ በትግሬ-ወያኔዎች የተጋረጠበትን ከምድረ-ገፅ የመደምሰስ አደጋ በውል ተገንዝበው ነበር። ሆኖም ፕሮፌሠር አሥራት የሚመሩት መዐሕድ ከውጭ በግልፅ በወያኔ እና በሻቢያ ፣ ከውስጥ ደግሞ ሥውር የሆነ መንገድ በወያኔ-ተላላኪ ሠርጎ ገቦች የደረሠበትን ቡርቦራ መቋቋም አልቻለም። መዐሕድ በተመሠረተ ሁለት ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወያኔ ፕሮፌሠር አሥራትን «የጦርነት ቅስቅሣ አድርገሃል» ብሎ ለእሥር ዳረጋቸው። ከዚያም በእሥር እያሠቃየ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን በማከም፣ አልፎ ተርፎም የሕክምና ባለሙያዎችን በማሠልጠን ሰብዓዊ ሕይወትን ለ40 ዓመታት ሲታደጉ የኖሩትን ታላቅ የሕክምና ሊቅ ሕክምና ነፍጎ፣ በግንቦት 1990 ዓ.ም. ለሞት አበቃቸው። ከፕሮፌሠር አሥራት መታሠር በኋላ ለዐማራው ሕዝብ ቋሚ ጠበቃ ሆኖ ጠንክሮ የሚታገል ድርጅት ለማፍራት አለመቻሉ ብቻ ሣይሆን የዐማራውን ጉዳይ «ጉዳዬ ነው» ብሎ በኃላፊነት የሚመራ ስብስብ እንኳን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች ፍሬ አልባ ሆነው ቆይተዋል። ለዚህ ሠበብ ሆነው የሚቀርቡ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም አንዱ የብዥታ ምንጭ የዐማራው ልሂቃን ከራሣቸው ነገድ ህልውና ይልቅ «በይስሙላ የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ» ጥልፍልፍ ውስጥ ተዘፍቀው የራሣቸውን ወገን ችግር ችላ በማለታቸው ነው። የሚያሣዝነው የዐማራው ልሂቃን ራሣቸውን ከገሃዱ ዓለም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ አግልለው፣ በሌሉ ተምኔታዊ የማኅበራዊ ሣይንስ ፍልስፍናዎች ውስጥ ተጠምደው፣ በትግሬ- ወያኔዎች የሠቆቃ አገዛዝ ሥር ለሚማቅቀው ለዐማራው ወገናቸው ጠቃሚ አስተዋፅዖ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

ለዐማራ ሕዝብ መከራ መራዘም እና ለኢትዮጵያውያንም የወደፊት ተስፋ ማጣት ሌላው ምክንያት የፖለቲካ ልሂቃኑ የሚከተሉት ውል- የለሽ እና ውጤት-አልባ የትግል ሥልት እንደሆነ ግልፅ ነው። በውጭ በሥደት የሚኖሩት ዐማሮች ግማሾቹ በሰላማዊ ሠልፎች ጋጋታ እና በኢንተርኔት መድረኮች እርግማን ብዛት ብቻ የትግሬ-ወያኔዎችን አገዛዝ መጣል ይቻል ይመስል ትኩረታቸውን በዚያ ላይ ወስነዋል። ግማሾቹ ደግሞ «ወያኔን በትጥቅ ትግል እናስወግዳለን» ብለው አጉል ተስፋ ያስጨብጡና «በመሣሪያ ትግል የምንጀምረው በሻቢያ ድጋፍ ከኤርትራ መሬት በመወርወር ነው» ይሉናል። በመካከሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋው «ጉም መጨበጥ» ሆኖበት ይበልጥ ግራ ተጋብቶ እንዲቀመጥ ተገድዷል። በአገርቤት የሚገኙት የሕብረ-ብሔር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ከወያኔ መሞዳሞዱ እንዳይቀርባቸው ስለትግል ሥልታቸው የቃላት ጨዋታ ይዘዋል፦ ሲጀምሩ ሰላማዊ ትግል የሚል ቃል ይጠቀሙ ነበር። ወያኔ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ ከፊት «ሕጋዊ» የሚል ቃል ጨምረው «ሕጋዊና ሰላማዊ ትግል እናካሂዳለን» ይላሉ። ነገር ግን የትግሬ-ወያኔዎች በሚገዟት ኢትዮጵያ ሕጋዊነትም ሆነ ሰላማዊ ሁኔታ የለም፣ አይኖርምም። ስለሆነም የትግሬ-ወያኔዎችን አገዛዝ ለማንበርከክ በመጀመሪያ በትግል ሥልት ላይ ግልፅ እና ለውጤት የሚያበቃ አቋም መያዝ ያስፈልጋል።

5.ምን መደረግ አለበት?

የትግሬ-ወያኔዎችን ናዚያዊ አገዛዝ ከሥሩ መንግሎ ለመጣል በአገርቤት ያለው ዋናው የሕዝብ ክፍል እና በውጪ በሥደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ እንደሚኖሩበት አካባቢ ተጨባጭ ሁኔታ መወጣት የሚገቧቸውን ሚናዎች ለይተው ሊያውቁ ይገባል። ለምሣሌ አገርቤት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በአገዛዙ የሚደርስበትን ጭፍጨፋ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በአካል ቀርቦ ለማስረዳት አይችልም፣ ክስ ለመመሥረትም አዳጋች ይሆንበታል። ምክንያቱም ግልፅ እና የማያሻማ ነው፦ ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ እንዴት ተደርጎ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተኖረ በወያኔ ላይ ክስ ማቅረብ የሚቻለው? በውጪ በአንፃራዊ ነፃነት ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያውያን ግን እንዲህ ዓይነቱን ኃላፊነት ለመወጣት ጊዜውም፣ ገንዘቡም፣ ዕውቀቱም፣ አማራጩም አላቸው። በሌላ ወገን ደግሞ አገርቤት ያሉቱ ሕዝቡን በቃላት ጨዋታ ከሚያደነዝዙት እና ራሣቸውንም ከፖለቲካ ትግሉ ጡረታ ባያወጡ ይበጃቸዋል። በግልፅ ቋንቋ እርባና ያለው የፖለቲካ ሥራ መሥራት ካልቻሉ እና በተቃዋሚነት ከሚቀጥሉ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ቢቀመጡ ቢያንስ የጥፋቱ ተባባሪ ከመሆን ይድናሉ። «ለዐማራው ሕዝብ ብሶት ቆመናል» የሚሉት ደግሞ ከትግሬ-ወያኔዎች ወገን የሚደርስባቸው ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ፣ ፈተናቸውም ከባድ ነውና ያላቸውን ግልፅ አደረጃጀት እንደገና ሊያጤኑት ይገባል። የዐማራን ነገድ ተወላጆች የሠቆቃ ዘመን ለማሣጠር እና የኢትዮጵያንም ዳግም ትንሣኤ ዕውን ለማድረግ እያንዳንዱ የዐማራ ተወላጅ በቦታ፣ በጊዜ፣ በገንዘብ፣ በቁሣቁስ፣ በድርጅት፣ በአጠቃላይ በሁሉም በሚችለው መንገድ አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅበታል። ያለበለዚያ ግን የመከራው ዘመን መራዘሙ ብቻ ሣይሆን ዐማራው ከምድረ-ገፅ እንደሚጠፋ በትግሬ-ወያኔዎች እና በተባባሪዎቻቸው ከተያዘው የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ መገንዘብ ያስፈልጋል።http://welkait.com/?p=634

 <http://www.zehabesha.com/

ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?

New post on Fitih le Ethiopia


“በአፍሪካ ብዙ ስራ አለን” ጆን ኬሪ
africa-china-us
በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ።
ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ “ጉባኤ አድማቂ” አሰኝቷታል።
“በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን” ሲሉ የተናገሩት ኬሪ “በድግሱ” ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። እየተጣጣመ የመጣው የአፍሪካና የቻይና ፍቅር እንዲሁም ቻይና በአፍሪካ ያላት ሰፋ ያለ ኢንቨስትመንት ለአሜሪካ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ቻይና የምትከተለው የንግድ ስልት በአጠቃላዩ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ኬሪ አልሸሸጉም፡፡ ዝርዝር ከመስጠት ቢቆጠቡም ጉቦ፣ ሙስና፣ አምባገነኖችን መርዳት በማለት የተወሰኑትን በግልጽ ከመጥቀስ አላለፉም፡፡
ኦባማም ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀኑበት ጉዳይ አሜሪካ በአፍሪካ ለምትከተለው አዲስ እቅድ ማጠናከሪያ ካስማ ለመቸንከር እንደሆነ አብዛኞች ይስማሙበታል። “ቻይናን በቅርብ ሆኖ መቆጣጠር” በሚለው መርህ  የአፍሪካን አምባገነኖች ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት ልቡናቸውን የመስለብ እቅድ ይዛ እየሰራች ያለችው አሜሪካ፣ የቻይናና የአፍሪካ ግንኙነት “የፓለቲካ እባጭ” የሆነባት ቻይና ድፍን የአፍሪካ መሪዎችን ቤጂንግ ጋብዛ ወዳጅነቷን አደባባይ በማውጣት ጸሐይ ካስመታቸው በኋላ ነበር። በርካታ መረጃዎችም በዚሁ ዙሪያ ቀርበዋል።
በቤጂንጉ ጉባኤ ቻይና ዶላር ለሚናፍቁት የአፍሪካ መሪዎች ብድር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂ፣ የመንገድ ግንባታ፣ የተለያዩ ርዳታዎች ለማድረግ፣ ከዚህም በላይ አምባገነኖች የስለላ መዋቅራቸውን እንዲያደራጁ የሚያስችላቸው በገሃድ እንዳይሰራጩ የተከለከሉ የአፈና መሳሪያዎችን ጭምር ለመስጠት ቃል ገብታ አፍሪካን የገበያዋ ሳሎን ስታደርግ አሜሪካና አውሮፓውያኖቹ ደነገጡ፤ ታመሙ።
በተመሳሳይ ቻይና ዘይትና የተለያዩ ማዕድኖችን ከአፍሪካ በመዛቅ የገበያ ድሯን ዘርግታ አፍሪካን ተጣባቻት። ዜጎቿንና የንግድ ተቋሞቿን አፍሪካ ምድር በትና ከላይም ከታችም ተቆጣጠረቻት። ከዚህ በኋላ ነበር መቀደሟ ያሳሰባት አሜሪካ ቻይናን በቅርብ መከታተል በሚል አዲስ ስልት የነደፈችው።
ባለሙያዎችና የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት አሜሪካ በኢኮኖሚና በገንዘብ ድጋፍ የአፍሪካን ሆዳም መሪዎች በማባበል ቻይናን ለመፎካከር በዛሬው ጊዜ አይቻላትም፤ በገሃድ እከተለዋለሁ የምትለውን ግብዝ ፖለቲካ ያበላሽባታል። እንደውም አታስበውም። ለዚህ ይመስላል የአፍሪካ አገሮችን ወታደራዊ ሃይል በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማስታጠቅ፣ የየአገራቱን ወታደራዊ እዝ ከበላይ ሆኖ በመምራት የቻይናን እንቅስቃሴ ለመበርበር የተንቀሳቀሰቸው። (ከዚህ በፊት“የኦባማ አስተዳደር መጪው የአፍሪካ ዕቅድ” በሚል የጻፍነውን እዚህ ላይ ይመልከቱ)
አምባገነኖች የመከላከያ ኃይላቸውን እንደ ብረት ለማጥበቅ ካላቸው የጸና ፍላጎት አንጻር አሜሪካ የነደፈችው ስልት የተዋጣለት እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች “አሁን አሜሪካ ወታደራዊ ሃይልን ለማጠናከር በሚል ወደ አፍሪካ የገባችበት ስልት፤ ከአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እውቅና ውጪ የሚፈጸም ተግባር ስለሌለ መረጃ የማግኘት አቅሟ የቻይናን መስኮት በርግዳ ሳሎኗን የማየት ያህል ነው” ይላሉ፡፡
አሜሪካ አሁን ባለችበት ደረጃ አፍሪካ 50ኛ ዓመት በዓል ስታከብር በይፋ ባይረጋገጥም ኦባማ የመገኘታቸው ሚስጥር ከፖሊሲያቸውና ቻይናን በቅርብ ሆኖ ከመቆጣጠር አዲሱ ስልታቸው በመነሳት እንደሆነ የማያሻማ ነው። በጉባኤው ላይ አራት ከፍተኛ የአገር መሪዎች እንደሚገኙ የኢህአዴግ አንደበት ፋና ጠቁሟል ግን ዝርዝር አላቀረበም። ጆን ኬሪ “ከአፍሪካ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ከአህጉሪቷ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሻሻል እንሰራለን” ማለታቸውን ፋና ምንጭ ሳይጠቅስ አስፍሯል።
ፋናም ሆነ ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ ባያደርጉትም የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባለስልጣናትና የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የስብሰባው ታላቅ እንግዳ እንደሚሆኑ ፖለቲከኞች ቅድመ ግምታቸውን አኑረዋል። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የክልል አንድ ልዩ ዞን ተወካይ እስኪመስል ልዑክ በመላክና የቻይንኛ ቀረርቶ በማሰማት ተሳትፎ ያላት ቻይና ለአፍሪካ ህብረት ታላቅ ስጦታ ማቅረቧ የሚታወስ ነው።
የአፍሪካ ኅብረትን ዘመናዊ ህንጻ በራስዋ ወጪ ያስገነባቸው ቻይና በቤቷ፤ ኦባማም ከተገኙ በእንግድነት የኅብረቱን የምስረታ ዘመን አስመልክቶ ቻይና በነጻ ገንብታ ባስረከበችው ህንጻ ውስጥ ሆነው ህንጻውን እያደነቁ ይደሰኩራሉ።

Comment   See all comments
Unsubscribe or change your email settings at Manage Subscriptions.
Trouble clicking? Copy and paste this URL into your browser:
http://freedomofspeech4.wordpress.com/2013/04/27/910/

Ethnic Cleansing in Ethiopia .





የኦነግ ግልብጥ የሌንጮ ለታ ፀረ_ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሸፍጥና የለበጣ አቋም


ሌንጮ ለታ፥ የተባለው አንጋፋ የኦነግ ግልብጥ ዩሃንስ ለታ ተብሎ የሚታወቅ የወለጋ ወይም የዳሞት ክፍለ ሃገር ሰው ነው። (ወለጋ የጥንት ስሙ ዳሞት ነበር የሚባለው)። ይህ ሰው የፖለቲካ ክላውት ወይም ወታደራዊ ጉልበት ፈጽሞ የሌለው እንደ ስብሃት ነጋ እንደፈለገው የሚቀደድና የሚናቆር ችግር ፈጣሪ ልግመኛ ደማጐግ ነው።

አባይ ወልዱ እና በደል በትግራይ

ኣባይ ወልዱ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በህዝብ ላይ ጨካኝ እና ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ የልማት ሰራዊት በማደራጀት የ 5 ኣመት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ግቡ እንዲመታ እናደርጋለን፤ የሚሊኒየም ግብ ካስቀመጥነው ጊዜ ገደብ ኣስቀድመን እንፈፅማለን ብለውናል:: ኣባይ ወልዱ ኣለቃ ፀጋይ በርሀን አስወገደው ስልጣኑን ከተቆጣጠሩ በኋላ በክልሉ እጅግ ብዙ ፀረ ዲሞክራሲ የሆኑ ድርጊቶችን ፈፅመዋል። እንደ ኣብነት ለመጥቀስ በሚያዚያ26/27/2005 ዓ/ም በትግራይ ደቡባዊ ዞን ወረዳ ሞኮኒ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ 7000 ኣባዎራዎች ከ ኣፂ ሃይለስላሴ እስከ ዘመነ ኣገዛዝ ኢህአደግ ሲኖርበት የነበሩ ከ 3 ትውልድ በላይ ጊዜ የኖሩበት ተተኪ

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር



 
Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekeleበህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል። በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ

ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?
‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።
አሁን ሰውየው ‘አርፈዋል’። ለተከታዮቻቸው የተውት መርህ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቅጣጫ የለም። የኢህኣዴግ ካድሬዎች ታድያ አሁን የሚግባቡበት ቋንቋ የላቸውም። የኣምስት አመቱ ‘የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን አቅድ’ ይዘት ወይ መሰረታዊ ፅንሰ ሓሳብ ምን እንደሆነ የሚያውቀው የለም። በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ያለ ዉጤት ተበትነዋል። (ዕቅዱ ግን ድሮውም ቢሆን ምንም የሚጨበጥ ሓሳብ አልነበረውም ….. የሚሰማን አጣን እንጂ)። ዕቅዱ ‘Ambitious’ ብለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር (‘ሊተገበር የሚችል ዕቅድ አሳዩን’ ብለን ተማፅነን ነበር)። አሁን ግን ካድሬዎቹ ራሳቸው (በተለያዩ ስብሰባዎች) ‘የተለጠጠው (ዝተለጠጠ)’ ዕቅድ ማለት ጀምረዋል።
በኢህኣዴግ ደረጃ ያለው ችግር የስልጣን ሽኩቻ ነው (የባለስልጣናቱ ዓላማ ስልጣን ነው)። ህወሓቶች በኢህኣዴግ የነበራቸው ሚና ማጣት አይፈልጉም። ግን ይህንን ሚና ሊጫወት የሚችል ደህና ሰው የላቸውም። (ዓቅም የነበራቸው የፓርቲው ሰዎች በተለያየ ምክንያት እንዲጠፉ ተደርገዋል ) ። ራሳቸው በራሳቸው ችግር ፈጥረው (በሁለት ተከፍለው፣ ጓደኞቻቸው ኣባረው) ተዳክመዋል (አሁን ትግራይ እንኳ መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ኣይገኙም)።
በኣሁኑ ግዜ በኢህኣዴግ ዉስጥ የተሻለ የስልጣን ተፎካካሪ ብአዴን ነው። ግን ብአዴን ከሌሎች ሦስቴ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ድጋፍም በሰፊው የለውም። የሚጠበቀው ያህል (ኢህኣዴግ ለመቆጣጠር የሚያስችል) ጠንካራ አባላትም የሉትም። ግን በኢህኣዴግ ስርወ መንግስት የህወሓት አልጋ ወራሽ ብአዴን ይመስላል። በህወሓትና ብኣዴን ከፍተኛ ውዝግብ አለ።
ኦህዴድ በኢህኣዴግ ዉስጥ በጣም ያኮረፈ ቡድን ነው። የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ስልጣን ለኦህዴድ መሰጠት እንዳለበት ይወተውታል። ግን ኦህዴድ ሁለት ችግሮች ተደቅነውታል። (አንድ) በኦህዴድ ውስጥ መግባባት ብሎ ነገር የለም። (ሁለት) በሌሎቹ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች እምነት ባለፈው የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ሓላፊነት የወጡ ሰዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው። በነሱ እምነት ኦነግ የኦህዴድ መዋቅር ተቆጣጥሮታል። ስለዚ ለኦህዴድ ስልጣን መስጠት እጅግ ያስፈራቸዋል።
ሌላው ደኢህዴን ነው። ደኢህዴን ጠንካራ ኣይደለም። በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ትርምስ ላይ ነው። ከቡድኖቹ አንዱ ከህወሓት ጎን መሰለፍ ይፈልጋል። ብቻውን (ህወሓት ከዚህ በፊት እንዳደረገው) የኢህኣዴግ ስልጣን መቆጣጠር የሚችልበት ዕድል የለውም። ህወሓትም ቢሆን ደካማ ሁነዋል። ዶር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኢህኣዴግ ጉባኤ ሲናገር “በቃ ወድቀናል” ብሎ ነበር። ይሄ ከህወሓት ጋር መጠጋት ለሚፈልግ ቡድን ራስ ምታት ነው።
ህወሓቶች ጉዳዩ ኣስጨንቋቸዋል። የነ አባይ ወልዱ ቡድን የነ አርከበ ዕቁባይ ቡድን ካባረሩ ወዲህ የባሰ ንትርክ ዉስጥ ገብተዋል። እርስበርሳቸው አይግባቡም፣ ይናናቃሉ። የኣሁኑ መሪዎች ማንም አያከብራቸውም። በህወሓት ጉባኤ የተሳተፉ አባላት በነ ኣባይ ወልዱ የተመለመሉ ቢሆኑም በጉባኤው ወቅት በነኣርከበ የተወሰደው እርምጃ ግራ አጋብታቸዋል። ጉባኤተኞቹ ‘እነ ኣርከበ ከውጡ ህወሓት ከማን ጋ ትቀራለች?’ የሚል ጥያቄ ነበራቸው።
የፓርቲው ሊቀመንበር የሚመረጠው (በፓርቲው ደንብ መሰረት) በጠቅላላ ጉባኤ ነው (በቀጥታ ግን አይደለም)። እንዲህ ነው። ጉባኤተኞቹ አርባ አምስት የፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመርጣሉ። በውጤቱ (ባገኙት ድምፅ) መሰረት በቅደም ተከተል (የተመረጡት ሰዎች) ስማቸው ይገለፃል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ስራ ኣስፈፃሚ (ፖሊት ቢሮ) ይመርጣል። ፖሊት ቢሮ አባላት ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበርና ምክትል ይመርጣሉ።
በምርጫው ከፍተኛ ስልጣን ያለው (በመርህ ደረጃ) ጉባኤተኛው ስለሆነ ከፍተኛ ድምፅ ያለው (By Default) የፓርቲው ሊቀመንበር ይሆናል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይሄንን አውቀው ባገኙት ድምፅ መሰረት ዘጠኙ (TopNine) ለፖሊት ቢሮ ይመርጣሉ። ፖሊት ቢሮ አባላትም በተሰጠው ድምፅ መሰረት ከፍተኛውን ያገኘ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጣሉ።
በጉባኤው የተሳተፉ አባላት ሊቀመንበር (ከተሰጣቸው አማራጭ) አድርገው የመረጡት ዶር ደብረፅዮን ነበር። ዶር ደብረትፅዮን የኣንደኛነት ድምፅ ሲያገኝ አባይ ወልዱ ሁለተኛ ነበር። (ደብረፅዮን ለኣባይ በ23 ድምፅ ይበልጠዋል)። ውጤቱ ግን ጉባኤተኞቹ እንደጠበቁት ኣልሆነም። የፖሊት ቢሮ አባላት ሁነው የተመረጡት (top nine) ዘጠኙ ኣልነበሩም። በውጤቱ መሰረት የህወሓት ሊቀመንበር መሆን የነበረት ዶር ደብረፅዮን ሲሆን ዉጤቱ ተገልብጦ አቶ ኣባይ ተመረጠ። ይሄ የሆነው የኣቶ አባይ ቡድን አብዛኛው የማእከላዊ ኮሚቴ ወንበር መያዝ በመቻሉ ነበር። (ጉባኤተኞቹ የነኣባይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ አባይ ፓርቲው ይመረዋል ብለው ግን አያምኑም። ስለዚህ ጉባኤተኞቹ ደብረፅዮን ሊቀመንበር አድረገው መርጠው እንደሄዱ ነው የሚያውቁ)።
ይሄን ዉሳኔያቸው ታድያ በጉባኤተኞቹ ጥሩ ስሜት አልፈጠረም። የኣሁኑ መሪዎች የህዝብ አመኔታም የላቸውም። ይሄን ችግር ለመፍታት ሲሉ ከነገ እሮብ (ሚያዝያ 16, 2005 ዓም) ጀምሮ ጉባኤው በተመለከተ በመላው ትግራይ (በየደረጃው ከከፍተኛ የክልል ቢሮዎች ጀምሮ እስከ ቀበሌ አስተዳደር ድረስ) ስብሰባ እንደሚደረግ ታውቋል። ለስብሰባው ማስኬጃ ብዙ ሚልዮን ብር ተመድበዋል (ከመንግስት ካዝና መሆኑ ነው)።
ኣየ ህወሓት! በቃ ስብሰባ ነው። እኔ ደግሞ ስብሰባ ስጠላ! (እንኳን የህወሓት አባል አልሆንኩ)።
 

tirsdag 23. april 2013

ያኔ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋትና ከመኖሪያ ስፍራቸው ማፈናቀልን በመቃወም የተደረገ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌ ኦስሎ ተካሄደ TPLF bosses should face justice


Posted: 23 Apr 2013 12:04 PM PDT
 18 .04.2013 
  by : Abi

በአሁኑ ወቅት በአማራ ህዝብ ላይ መንግስት እያደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ከሚኖሩበት ስፍራ ያለአግባብ ማፈናቀሉን እንዲቆም የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ አፕሪል 18.04. 2013 በኖርዌ ኦስሎ በደማቅና በተሳካ ሁኔታ ተካሂዶ ውሏል። ፕሮግራሙም በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14፡00 የተጀመረ ሲሆን ከተለያየ የኖርዌይ ከተማ የተሰባሰቡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች በሰአቱ በመድረስ ሰላማዊ ሰልፉን የተሳካ እንዲሆን አድርገውታል። 


 በአሁን ሰአት ህዝባችን በሚፈናቀልበት እና መከራውን በሚያይበት ስፍራ ይኖሩ የነበሩና ስለቦታው ጠንቅቀው የሚያውቁት አቶ ማህተቤ መለስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ም/ሊቀመንበር ዝግጅቱን በንግግር ሲከፍቱ በንግግራቸውም ላይ ስለሆነው አስከፊ ሁኔታ እና መንግስት ስለሚደረገው የዘር ማጽዳት እና መሰሪ ድርጊቱን ከስር መሰረቱ በማብራራት ለታዳሚዎቻቸውአጋልጠዋል።


በዝግጅቱም ላይ ስለሁኔታው የሚገልጹ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ሰላማዊ ሰልፍ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ይሰሙበት ነበር።

እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች መንግስት በአማራ ወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሰዎችን ከመኖርያ ስፍራቸው በማፈናቀል ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተቃውመው ለድርጊቱም ፈላጭ ቆራጭ የሆነውን የወያኔን መንግስት በአለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ የሚያስችል ድርጊት በመሆኑ ለፍርድ እንደሚያቀርቡት ገልጸዋል ።
 

እንዲሁም ከሀይማኖት ተቋማት የሙስሊም ድምፃችን ይሰማ ኮሚቴ በኖርዌይ ተወካይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም መንግስት በክርስቲያን የሃይማኖት ተከታዮች እና በሙስሊም የሃይማኖት ተከታዮች መካከልጣልቃ በመግባት ለማጋጨት ቢሞክርም እኛ አንለያይም ሁል ጊዜም አንድ ነን በሚል ጠንከር ባለ ንግግር የመንግስትን ሴራ አውግዘዋል።

 
እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በማሰብ ምንግዜም ከጎናችሁ ነን በሚል አጋርነታቸውን ተግቢር ተግቢር በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ዘርፍና የወጣት ክፍሉ አጫጭር ቀስቃሽ የሆነ መልዕክት ካቀረቡ በሓላ የተለያዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችም ንግግር አድርገዋል ። 
 

የተቃውሞ ሰልፈኛውም በአንድነት በመሆን በታላቅ ድምጽ የወያኔ መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭቆናና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኮንነው ይህንን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ገርስሶ ለመጣል ሁላችንም አንድ ሆነን በመነሳትና የበኩላችንን አስተዋጽዎ በማድረግ ሐገሪቷ ከወደቀችበት አዝቅጥ ውስጥ ለማውጣት ጠንክረን መታገል አለብን በሚል በመላው አለም ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ጥሪያቸውን በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በኖርዌይ ሰአት አቆጣጠር 16፡00 ሰአት የፕሮግራሙ መሪ የማጠቃለያ ንግግር ካደረጉ በኋላ አጠናቀዋል ።
 

ይህንን ፕሮግራም በመተባበር ያዘጋጁት ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ እና ኢህአፓ በኖርዌይ ሲሆኑ ከድርጅቶቻቸው አባላት እና ከሲቪክ ማህበረስብ የተውጣጡ ቡድኖችን task force በመፍጠር ታክስ ፎርሱም በመሰባሰብ የተለያየ እቅዶችን ለማዘጋዘት ወስኖ ሰላማዊ ሰልፉንም የመጀመሪያ እቅዶ በመሆኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተረባርበው በሰሳካ ሁኔታ ሊያዘጋጁት ችለዋል ። 

Posted: 23 Apr 2013 11:02 AM PDT

 

Wednesday, April 17, 2013
       
By Zelalem Abate 

One may ask why rulers commit genocide, crimes against humanity, and ethnic cleansing on the very people they rule. Although nothing would justify, heinous rulers always provide bizarre and incomprehensible justifications. The tyrants in Ethiopia, for example, say Amharas were evicted because they cut trees. For them cutting trees is enough reason to commit ethnic cleansing and crimes against humanity. As the world knows, these kinds of despicable crimes have been committed in Rwanda, Liberia, Sudan, Ethiopia and other countries. The star actors of genocide and crimes against humanity in Rwanda, Liberia and Sudan are already facing justice. The tribal and racist-primitive rulers who have been committing ethnic cleansing and crimes against Amharic speaking people (the Amharas) for the last 22 years in Ethiopia are still leaving lavish lives at the expense of the resources of their victims-the Amharas

.
Would you please listen to these verses, Emama Ethiopia?

My country, Ethiopia
You are fool, deceivable
You feed your murders
While you starve your martyrs!”

No single spot exists in the mountains, plains, low lands, deserts, jungles, rivers and lakes, where Amharas did not spill their blood to protect the national integrity and sovereignty of Ethiopia. A lot has been said about the battle of Maqdala, Adwa, Mychew, and The Five-Year War with Facist where Amharas gave their chest for bullets and their whole body for mustard gas in order to transfer a proud and free country to us. Let’s just gaze at the very near past. It was the Amhara peasants who broke the back bone of invader Siad Barre. It was the Amhara militia who protected our natural sea ports until mama Ethiopia’s neck and breasts were butchered by her traitor children. What is the gladiator Amhara getting in return now? Systematic discrimination, frequent eviction, endless displacement, repeated ethnic cleansing, chronic crime against humanity, and genocide?

One of the leading Ethiopian online news papers on Ethiopian affairs, Ethiomedia, covered on its March 17, 2013 front page, that 59 uprooted Amharas were killed by car accident in Benishngul Gumuz, western Ethiopia while they were forcefully evicted after their property was confiscated. [1] Similarly the Ethiopian Satellite Television, an independent news outlet, reported that more than 3, 000 people were evicted from Benishangul area. [2] These crimes were also discussed in the Voice of America Amharic program. [3] The evicted people and the deaths include children and pregnant women. Mind you, the victims only crime was being born Amhara. Dr. Yakob Hailemariam, one of the Lawyers who investigated the Rwandan Genocide, call this act of the TPLF lead government ethnic cleansing. [4]

In this 21st century human traits such as age, gender, and ethnicity are protected human characters. In civilized societies (at least in theories), discriminating based on these protected traits is illegal and immoral. However, concepts such as legality and morality are not found in the dictionaries of the barbaric tribal rulers of Ethiopia. Unfortunately, the ruling party’s fundamental policy in Ethiopia dictates cadres to organize people based on ethnicity and the language they speak. Furthermore, this backward policy (The Wild-animals’ law as the distinguished scholar professor Mesfin woldemariam calls it)promotes the different ethnic groups to discriminate each other based on human nature such as race, language, religion and so on. The Amharas, who are mainly against this uncivilized jungle law, have been the prime victims of this brutal and retarded policy since the racist Tigrai People Libration Front (TPLF) took power through a Trojan horse- the Ethiopian Democratic Libration Front (EPRDF).

The Amharas are the second largest ethnic group in the country. Some, in fact, argue that Amhara could be the largest group in the nation if counted in unbiased manner. Ancient and modern history teaches that this population group existed with other ethnic groups in Ethiopia and the surrounding East African countries since humans started to live as society on this earth. However, the Amharas have never claimed certain regions of Ethiopia as their own sole state. Unfortunately, TPLF created a segregated area called Amhara killil (Killil -a local term for segregation) for these groups of people.
Many including former members of TPLF have stated that TPLF leaders have been labeling the Amharic speaking people as their enemies since they organized themselves as communist Guerilla fighters in the early 70’s. [5] The crimes committed against Amharic speaking people since this rebel group (formerly labeled as terrorist group by USA) took power are the practical applications of this former communist Guerilla fighters’ racist-jungle manifesto.


As mentioned above, systematic discrimination of Amhara has been on the making for more than two decades. As soon as the TPLF took power in 1991, it cleansed more than 42 intellectuals (almost all of them Amharas) from the teaching positions at Addis Ababa University. [6] It established a unique and effective contraception programs in the Amhara communities to reduce the number of births. No sane Amharic Speaking individual with viable conscience is allowed to take key positions in the government. Those individuals who claim to represent the Amharas in the government are either non-Amharas or Amharas who sell out their soul and conscience to money and other ephemeral advantages.

About two years after the TPLF took power, thousands of Amharic speaking people including women and children were massacred in the eastern part of the country called Bedeno. [7] It needs an outstanding historical film maker to document how these unfortunate people were thrown away from the top of the cliff as high as 100 meters. It takes Schindler’s List film director to document the suffering of the children of these victims.

  It takes the skill of a horror film maker to produce how women were repeatedly raped in front of their husbands during this crime against humanity. Similar crimes have been committed against Amharic speaking people in Central, Southern, Western and Northern Ethiopia. Such kinds of atrocities were relatively abated by the formation of the All Amhara People Organization. Unfortunately, this organization’s leader, Professor Asrat (the first surgeon in the country), was incarcerated and died because he was denied access to medical care by TPLF lead government.

As a continuation of “cleanse the Amharas motto”, thousands of Amharic speaking people were forced to leave from Gura Ferda (southern Ethiopia) in 2012. [8] These unfortunate people were forced to leave their houses and other property behind and no one really knows who exactly has robbed their possessions. Many have suffered and died during this disgraceful ethnic cleansing. Only God and the victims know about what happen to the cleansed victims who are not dead at this point. The officials who systematically conducted theses dreadful crimes still hold higher positions in the States and Federal Government. Such is the case in the current Ethiopia-you commit wicked crime, you get promotion.

Besides being forcefully evicted from their homes at the different regions of the country, Amharas also roam to different parts of the world even to the failed state Somalia to escape the systematic discrimination and ethnic cleansing. During this mass migration, Amharas die every day in hundreds from various causes such as flood, wild animals, hunger, diseases, etc. Still among those who are able to escape and live in the foreign land, many die of slavery and suicide.
In summary, Amharas were not born Amharas by choice. Their ethnicity or language is their protected identity.

 Above all, the evicted Amharas fathers’ and forefathers’ have spilled their blood in every corner of Ethiopia to defend the sovereignty and pride of our nation. The land currently cultivated by Indian, Chines and Arab traders is enriched with Amhara’s blood and flesh. Despite this glorious history of their ancestors, Amharas have been discriminated and cleansed by TPLF lead government which is composed of disloyal and treacherous individuals who sold out our sea access and fertile land.

 This act of the narrow-minded TPLF government is not just totally immoral but absolute crime that should not happen in 6000 BC let alone in 21st century. If the TPLF lead rulers continue the ethnic cleansing of Amharic speaking people with this rate, Amharas will be endangered species in the near future. Therefore, those people who have direct or indirect participation in systematic discrimination, evicting, and ethnic cleansing of the Amharas or any other ethnic group should face justice as soon as possible. Lawyers and Judges (especially of Ethiopian origin) have professional, moral, ethical, historical and national responsibility to force these horrendous criminals face justice.

የማረሚያ ቤቱ ድራማ በርዕዮት እምቢተኝነት ከሸፈ


ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡
ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡
የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም  ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች  ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡
ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ  ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡
ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡
ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡
የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም  ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች  ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡
ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ  ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

አንድነት ፓርቲን ግለሰቦች በሚያናፍሱት የተዛባ መረጃ ከረጅሙ ጉዞው ሊገታ አይችልም!!

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ በሀገራችን መሰረት ያለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው የሚል ከፍተኛ እምነት አለን። ፓርቲያችን በሀገራችን ፖለቲካ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቁርጠኛ የሆኑ አባላቱ፣ አመራሩና ደጋፊዎቻችን የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደረጉ ያሉት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህ ሂደትም አንድነት ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት ከፍሏል። ወደፊትም ይህንን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። ይቀጥላል…
Posted: 22 Apr 2013 08:11 AM PDT
ነጻነት እኛ ሰዎች በልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ። ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲለየን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ። ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበት፤ እንዳንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግለን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ። ዛሬ 21 የወያኔ አመታት በኋላ እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ  ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ።  መፈናቀላችን፤ ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ ህዝባዊ ትግሉን መቀላቀል ብቻ ነዉ።
ነጻነታችንን የቀሙን የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን እንደቀሙን ለረጂም አመታት ለመግዛት እንዲመቻቸዉ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልልና በሐይማኖት ከፋፍለዉን ከሃያ አንድ በፊት በኢትዮጵያ ሀዝብ ላይ ጀመሩትን እስራት፤ ስደት፤ ግድያና ዝርፍያ አሁንም እንደቀጠሉ ነዉ።  የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን ቀምተዉ እየገዙን ቢሆንምገዛናቸዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም። ዜጎች ነጻነታቸዉንና መብታቸዉን እንዳይጠይቁ አፋቸዉን ያዘጋሉ፤ አንዱ ለሌላዉ አንዳይቆም አገር፤ ባንዲራና ኢትዮጵያዊነት የሚባሉ ትላልቁቹን የጋራ እሴቶቻችንን በየቀኑ ያፈርሳሉ። ይህ የሚያሳየን ዜጎች ትልቅተስፋይዘዉ፤ ቤተሰብ መስርተዉ ለራሳቸዉና ለአገራቸዉ የሚኖሩበት ግዜ እየጠፋ ተስፋ መቁረጥ፤ ስደትና የመከራ ኑሮ ዘመን እየከበበን መምጣቱን ነዉ።  ይህ ከሆነ የነገዋንየነጻነት፣ የፍትህ፣ የዴሞክራሲባለጸጋ ኢትዮጵያንለማየትእያንዳንዱዜጋበቻለው አቅሙሁሉጠንክሮበመታገል እና ከራሱባለፈሌላውዜጋ  የነጻነት ትግሉንጎራእንዲቀላቀል ብሎም የዚህትግልባለቤት እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡የሀገራችን ህዝብ የነጻነት ችቦ አቀጣጣይ የትግሉአካልበመሆንመስራት እንጅ፣ ከቶ ሌላ አካል፣ ሌላ ሃይል መጦ ነጻ ያወጣኛል በሚል በባርነት እየተገዛ መጠበቅ የለበትም። ነጻነትናዴሞክራሲ በችሮታ አሊያም ከሰማይ እንደሚወርድ መና የሚጠበቅ ስጦታ አይደለም። ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል። አለበለዚያ “ላምአለኝበሰማይወተትዋንምአላይ እንዳይሆን ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት፣ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ስደት፣ እንግልት በራሱ በህዝቡ ላይ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው። ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የወያኔ የጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?
ወገንሁሉለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊግዴታውንእንዲፈጽምጥሪ እናደርጋለን፡፡ለአገሩ፣ ለማንነነቱ መሰዋእትነት ለመሆንእንደሚኮራሁሉአገሩም በሱ ትኮራለች ፡፡
በርግጥ ነው በህወሃት/ኢህአዴግ የአሰቃቂ ዘመናት ስለአገራችንየፖለቲካጉዳይማሰብና መናገር ወንጀልና ሽብርተኛ አስደርጎበጠራራፀሐይ የሚታሰሩበትናበግፍየሚገደሉበትጊዜነው።ይህንንአድርገሃልተብሎሳይሆንይህንንሳታስብአትቀርምተብሎያለምንምህጋዊናበቂምክንያትወጣቶች፣ አረጋውያንያለጊዜያቸው፣ያለዕድሜያቸውበከንቱአልቀዋል።በቅርቡም ደግሞ በአማራው ተናጋሪ የተጀመረው ዘርን የማጥፋት ዘመቻ አንዱ ነው። ስለዚህ እስከ መቼ ነው ለራሳችን ነጻነት ሌላ አካል ነጻ እስኪያወጣን የምንጠብቀው? ከዚህ በላይ ምን ስቃይ አለ? ሀገር የጠፋች እለት ምን ሊውጠን ይችላል።
እማማ ኢትዮጵያ ለልጆቿ ህልውናዋን ከመፍረስ አደጋ እንዲጠብቋት፣ ከወያኔ የዘርና ዘረኝነት አደጋ እንዲታደጓት ስትማጸን፤ ልጆቿ ደግሞ አንዳች ሃይል መጥቶ ነጻነታቸውን ያጎናጽፋቸው ዘንድ የኢትዮጵያ አምላክ እያሉ ሲጠባበቁ እስከ መቼ? ስለዚህ ወጣት ጎልማሳ አዛውንት ሽማግሌ ዘር ጾታ ሳይለይ የዛሬ የነጻነትህ ትግል ጅማሮ እጅህ ላይ ነው። ሀገራችንየዛሬውንየወያኔን ጨለማሸኝታ  የነገውንየነጻነት ብርሃንእየጠበቀችብቻሳይሆንእየናፈቀችአለች።ያንንድቅድቅጨለማሰንጥቆየሚወጣ የወጣት ጀግኖች ልጆቿንብርኃንትናፍቃለች።እናም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ  የብርሃኑመታያችቦ ሆኖ ታሪክ ይሰራ ዘንድ ለነጻነቱ የሚታገልበትና ትግሉን የሚቀላቀልበት ሰአት እየፈጠነ፣ እየቆጠረ፣ እየቀረበ ነውና ተነስ ባለህበት ያለህን አንሳና ወርውር፣ አቀብል።
ቋንቋችን አንድ ነው ለነጻነትህ ታገል! በማንነትህ በብሄር ምክንያት በተወለድክበት ሀገር፣ ቀዪ አትሰደድ! በሀገርህ ምድር እንደ ሁለተኛ ዜጋ የመኖሪያ ፈቃድ ጠያቂ አትሁን!  ወንድምህ፣ እህትህ፣ አባትህ እናትህ ባልሰሩት ወንጀል ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ፣ ሲገደሉ ዝም ብለህ አትይ! በሀገርህ ስብእና ክብርህ ተዋርዶ አትመልከት! ተነስና መብራቱን አብራ! ጀግኖች መከታ ሊሆኑህ ከጎንህ ተሰልፈዋል።
በአሁኑወቅትአያሌኢትዮጵያዉያንወያኔንለመታገልመሳሪያካነሱከነጻነት ታጋዮችጋርበየቀኑእየተቀላቀሉቢሆንም፤ ሀገር ውስጥ ያላችሁ እለታዊ ኑሮን ለማሸነፍ ስትሉ በየፋብሪካው በመንግስት ሴክተሩ እና ሌሎች ተቋማት የምትገኙ ሁሉ በድጋሜ ግንቦት 7 እንደሁሌው ሁሉ የውስጥ አርበኛ ሆናችሁ የነጻነት ትግሉን መቀላቀል፣ ራሳችሁንና ሀገራችሁ ከወያኔ የዘረኛ ማዳፍ እጅ ነጻ ትወጣ ዘንድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ትግሉን ቀጥሉበት። ፍርሃታችሁን በጥሳችሁ በመደራጀትና መረጃ በማስተላለፍ ግዴታችሁን ተወጡ። ለሀገራችሁ ቅርብ ሁኑ! ለነጻነት ትግሉ፤ የትግልስልትናየተለየየትግልቦታሳትመርጡወያኔንያስወግዳልበምትሉትስልትናይመቸናልበሚሉትቦታሁሉእስከመጨረሻው ትታገሉ ዘንድ አደራችን ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬም ቢሆን የህዝባችን ሰበአዊ መብትና ነጻነትንገፈውሕግንያፈረሱ ህገ አራዊት የሆኑትን ወያኔዎች ከሀገራችን ምድር ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባትን ሀገር ለመመስረት የሚያደርገውን የትግል ጉዞ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!