tirsdag 23. april 2013

አንድነት ፓርቲን ግለሰቦች በሚያናፍሱት የተዛባ መረጃ ከረጅሙ ጉዞው ሊገታ አይችልም!!

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ በሀገራችን መሰረት ያለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው የሚል ከፍተኛ እምነት አለን። ፓርቲያችን በሀገራችን ፖለቲካ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቁርጠኛ የሆኑ አባላቱ፣ አመራሩና ደጋፊዎቻችን የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደረጉ ያሉት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህ ሂደትም አንድነት ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት ከፍሏል። ወደፊትም ይህንን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። ይቀጥላል…
Posted: 22 Apr 2013 08:11 AM PDT
ነጻነት እኛ ሰዎች በልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ። ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲለየን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ። ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበት፤ እንዳንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግለን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ። ዛሬ 21 የወያኔ አመታት በኋላ እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ  ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ።  መፈናቀላችን፤ ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ ህዝባዊ ትግሉን መቀላቀል ብቻ ነዉ።
ነጻነታችንን የቀሙን የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን እንደቀሙን ለረጂም አመታት ለመግዛት እንዲመቻቸዉ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልልና በሐይማኖት ከፋፍለዉን ከሃያ አንድ በፊት በኢትዮጵያ ሀዝብ ላይ ጀመሩትን እስራት፤ ስደት፤ ግድያና ዝርፍያ አሁንም እንደቀጠሉ ነዉ።  የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን ቀምተዉ እየገዙን ቢሆንምገዛናቸዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም። ዜጎች ነጻነታቸዉንና መብታቸዉን እንዳይጠይቁ አፋቸዉን ያዘጋሉ፤ አንዱ ለሌላዉ አንዳይቆም አገር፤ ባንዲራና ኢትዮጵያዊነት የሚባሉ ትላልቁቹን የጋራ እሴቶቻችንን በየቀኑ ያፈርሳሉ። ይህ የሚያሳየን ዜጎች ትልቅተስፋይዘዉ፤ ቤተሰብ መስርተዉ ለራሳቸዉና ለአገራቸዉ የሚኖሩበት ግዜ እየጠፋ ተስፋ መቁረጥ፤ ስደትና የመከራ ኑሮ ዘመን እየከበበን መምጣቱን ነዉ።  ይህ ከሆነ የነገዋንየነጻነት፣ የፍትህ፣ የዴሞክራሲባለጸጋ ኢትዮጵያንለማየትእያንዳንዱዜጋበቻለው አቅሙሁሉጠንክሮበመታገል እና ከራሱባለፈሌላውዜጋ  የነጻነት ትግሉንጎራእንዲቀላቀል ብሎም የዚህትግልባለቤት እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡የሀገራችን ህዝብ የነጻነት ችቦ አቀጣጣይ የትግሉአካልበመሆንመስራት እንጅ፣ ከቶ ሌላ አካል፣ ሌላ ሃይል መጦ ነጻ ያወጣኛል በሚል በባርነት እየተገዛ መጠበቅ የለበትም። ነጻነትናዴሞክራሲ በችሮታ አሊያም ከሰማይ እንደሚወርድ መና የሚጠበቅ ስጦታ አይደለም። ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል። አለበለዚያ “ላምአለኝበሰማይወተትዋንምአላይ እንዳይሆን ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት፣ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ስደት፣ እንግልት በራሱ በህዝቡ ላይ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው። ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የወያኔ የጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?
ወገንሁሉለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊግዴታውንእንዲፈጽምጥሪ እናደርጋለን፡፡ለአገሩ፣ ለማንነነቱ መሰዋእትነት ለመሆንእንደሚኮራሁሉአገሩም በሱ ትኮራለች ፡፡
በርግጥ ነው በህወሃት/ኢህአዴግ የአሰቃቂ ዘመናት ስለአገራችንየፖለቲካጉዳይማሰብና መናገር ወንጀልና ሽብርተኛ አስደርጎበጠራራፀሐይ የሚታሰሩበትናበግፍየሚገደሉበትጊዜነው።ይህንንአድርገሃልተብሎሳይሆንይህንንሳታስብአትቀርምተብሎያለምንምህጋዊናበቂምክንያትወጣቶች፣ አረጋውያንያለጊዜያቸው፣ያለዕድሜያቸውበከንቱአልቀዋል።በቅርቡም ደግሞ በአማራው ተናጋሪ የተጀመረው ዘርን የማጥፋት ዘመቻ አንዱ ነው። ስለዚህ እስከ መቼ ነው ለራሳችን ነጻነት ሌላ አካል ነጻ እስኪያወጣን የምንጠብቀው? ከዚህ በላይ ምን ስቃይ አለ? ሀገር የጠፋች እለት ምን ሊውጠን ይችላል።
እማማ ኢትዮጵያ ለልጆቿ ህልውናዋን ከመፍረስ አደጋ እንዲጠብቋት፣ ከወያኔ የዘርና ዘረኝነት አደጋ እንዲታደጓት ስትማጸን፤ ልጆቿ ደግሞ አንዳች ሃይል መጥቶ ነጻነታቸውን ያጎናጽፋቸው ዘንድ የኢትዮጵያ አምላክ እያሉ ሲጠባበቁ እስከ መቼ? ስለዚህ ወጣት ጎልማሳ አዛውንት ሽማግሌ ዘር ጾታ ሳይለይ የዛሬ የነጻነትህ ትግል ጅማሮ እጅህ ላይ ነው። ሀገራችንየዛሬውንየወያኔን ጨለማሸኝታ  የነገውንየነጻነት ብርሃንእየጠበቀችብቻሳይሆንእየናፈቀችአለች።ያንንድቅድቅጨለማሰንጥቆየሚወጣ የወጣት ጀግኖች ልጆቿንብርኃንትናፍቃለች።እናም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ  የብርሃኑመታያችቦ ሆኖ ታሪክ ይሰራ ዘንድ ለነጻነቱ የሚታገልበትና ትግሉን የሚቀላቀልበት ሰአት እየፈጠነ፣ እየቆጠረ፣ እየቀረበ ነውና ተነስ ባለህበት ያለህን አንሳና ወርውር፣ አቀብል።
ቋንቋችን አንድ ነው ለነጻነትህ ታገል! በማንነትህ በብሄር ምክንያት በተወለድክበት ሀገር፣ ቀዪ አትሰደድ! በሀገርህ ምድር እንደ ሁለተኛ ዜጋ የመኖሪያ ፈቃድ ጠያቂ አትሁን!  ወንድምህ፣ እህትህ፣ አባትህ እናትህ ባልሰሩት ወንጀል ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ፣ ሲገደሉ ዝም ብለህ አትይ! በሀገርህ ስብእና ክብርህ ተዋርዶ አትመልከት! ተነስና መብራቱን አብራ! ጀግኖች መከታ ሊሆኑህ ከጎንህ ተሰልፈዋል።
በአሁኑወቅትአያሌኢትዮጵያዉያንወያኔንለመታገልመሳሪያካነሱከነጻነት ታጋዮችጋርበየቀኑእየተቀላቀሉቢሆንም፤ ሀገር ውስጥ ያላችሁ እለታዊ ኑሮን ለማሸነፍ ስትሉ በየፋብሪካው በመንግስት ሴክተሩ እና ሌሎች ተቋማት የምትገኙ ሁሉ በድጋሜ ግንቦት 7 እንደሁሌው ሁሉ የውስጥ አርበኛ ሆናችሁ የነጻነት ትግሉን መቀላቀል፣ ራሳችሁንና ሀገራችሁ ከወያኔ የዘረኛ ማዳፍ እጅ ነጻ ትወጣ ዘንድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ትግሉን ቀጥሉበት። ፍርሃታችሁን በጥሳችሁ በመደራጀትና መረጃ በማስተላለፍ ግዴታችሁን ተወጡ። ለሀገራችሁ ቅርብ ሁኑ! ለነጻነት ትግሉ፤ የትግልስልትናየተለየየትግልቦታሳትመርጡወያኔንያስወግዳልበምትሉትስልትናይመቸናልበሚሉትቦታሁሉእስከመጨረሻው ትታገሉ ዘንድ አደራችን ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬም ቢሆን የህዝባችን ሰበአዊ መብትና ነጻነትንገፈውሕግንያፈረሱ ህገ አራዊት የሆኑትን ወያኔዎች ከሀገራችን ምድር ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባትን ሀገር ለመመስረት የሚያደርገውን የትግል ጉዞ ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

1 kommentar:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    SvarSlett