fredag 1. mars 2013
የዕርቀ ሰላሙን ውጤት በጸሎትና በታላቅ ተስፋ ሲጠባበቅ ለቆየው መላው
ሕዝበ ክርስቲያን ታላቅ መርዶ ሆኗል ።» ሲል ገልጦ ጽፎታል ። በዚህ አጋጣሚ ቅዱስ
ሲኖዶስ እውነቱን እውነት በማለት ምስክርነቱን የሰጠው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ታሪካዊ
ግዴታውን በመወጣቱ ያመሰግነዋል ።
በራሱ ነጻነት የሌለውና ራሱ ተዋርዶ ታላቋን ቤተ ክርስቲያን ወደ ጥፋትና ወደ ውርደት
የሚመራው በነውርና በሥነ ምግባር ጉድለት ባሉ ጥቂት ጳጳሳት የሚመራው ይህ የአዲስ
አበባው አካል «በውጭ ያሉ አባቶች በጀርባቸው ሌላ ነገር አለ ፤ ይህም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ
ነው”ሲል በመግለጫው ላይ ቅዱስ ሲኖዶስን ሳይሆን በሥልጣን ላይ ያለውን ገዢ
ፓርቲ ወክሎ ለመናገር ጥረት ማድረጉን አሳይቷል ። እጅግ ጠባብ የሆነ የዘረኝነት ዓላማን
አንግበው የተነሡ ኃይላትና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን አከርካሪዋን ሰብረናል የሚሉ
ፖለቲከኞች አዛዥ ናዛዥ በሆኑበት አካል ዘንድ ይህ ሲነገር የሚያስደንቅ ነው ።
ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ከወንጌል የተለየ አላማ የለውም ፤ የተለየ ዓላማ የሚሉት ፥ በገዛ
ሀገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ስለሚቆጠሩት መናገርን ነው ። የተለየ ዓላማ የሚሉት ጥረው
ግረው ያፈሩትን የግል ሀብታቸውንና ቤታቸውን ጊዜ ባነሣቸው ጉልበተኞች እየተነጠቁ
ስላሉት መናገርን ነው ። የተለየ ዓላማ የሚሉት ፥ ብዕራቸውን አንሥተው ስለ እውነት በጻፉ
አሸባሪዎች እየተባሉ በየእስር ቤቱ ስለሚማቅቁት ጋዜጠኞች መጮህን ነው ። የተለየ ዓላማ
የሚሉት ፥ ጉዲት ፥ ግራኝና ፋሺስት ጣሊያን እንዳደረገው ፥ የተወለዱበትን ምድር ክደውሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ - 510.530.3681 - www.eotcholysynod.info 3
ገዳማቱን ለማፍረስ የተነሡትን መገሠጻችንን ነው ። ይህ ደግሞ ልዩ ቅዱስ ንጹሕ ከሆነው
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ዓላማ ነው ። ስለ ሀገር ፥ ስለ ወገን ፥
ስለ ታሰሩ ፥ ስለ ተሰደዱ መናገር ደግሞ ከክርስቶስ ያገኘነው ከቅዱሳን ሐዋርያት
የተማርነው በመሆኑ አሁንም ስለ እውነት እንመሰክራለን ።
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አስጠብቀን ለትውልድ አንዲት ቅድስት ቤተ
ክርስቲያንን እናስረክብ ብንልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳለው በልዩ ልዩ
መንገድ የሚናገረው ፀረ ሰላም የሆነው የኢሕአዴግ መንግሥት ቅን አሳብ ያላቸውን አባቶች
በማፈን ፥ የሱ መሣሪያ የሆኑትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የመበቀል ተግባሩን
ገፍቶበታል ። በዚህ ሁሉ በሀገራችን ያለችው ቤተ ክርስቲያንም ነጻነቷን በመሣሪያ ኃይል
ተነፍጋ የመንግሥት ፈቃድ ፈጻሚ ብቻ ሁና ትገኛለች ። ስለ ገዳማቶቿ መናገር አትችልም ፤
ምእመናኖቿ በአደባባዮቿ ሲገደሉ ፤ ወጣቶቹዋ ከቅጽርዋ ታፍሰው ሲወሰዱ ፥ የዋልድባ
መናንያን መነኩሳት ከገዳማቸው ሲፈናቀሉ ፥ ገዳማቸው ሲታረስ ፥ ምእመናን ሲንገላቱ ፣
የቅዱሳን መካነ መቃብር ሲታረስ አንዲት ቃል ለመተንፈስ አልቻለችም ።
ይህ አገሪቱን እስር ቤት አድርጎ ሕዝቡን በባርነት ለመግዛት የተነሣው ኃይል የቤተ ክርስቲያንን
ሐዋርያዊና የነጻነት አንደበት ለመዝጋት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች ተቀዳሚውና ዋነኛው ለሕገ
ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ ፈቃድ ተገዥ የሆነ ሰው በፓትርያርክ ስም በቤተ ክርስቲያን
መንበር ላይ በማስቀመጥ ቤተ ክርስቲያንን መድፈር ነው ።
ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የአንድነት ጥሪውን በተደጋጋሚ ቢያስተላልፍም በኢትዮጵያ ያለው
አንባ ገነን መንግሥትና ሲኖዶሱ ግን ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለማፈራረስ ከበደል ወደ
በደል በመገስገስ ላይ ናቸው ። ስለዚህ በመላው ዓለም የምትገኙ ማኅበረ ካህናት ፣ የሰንበት
ትምህርት ቤት ወጣቶች ፣ ሕዝበ ክርስቲያንና ቤተ ክርስቲያንን የምትወዱ ሁሉ ከዚህ
የሚከተለውን መልእክት ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላልፋል ።
1. በአዲስ አበባ የሚካሂደው ኢቀኖናዊ ሢመተ ፓትርያርክ የቤተ ክርስቲያንን ክብር
ዝቅ የሚያደርግ ፣ ሥርዐት አልበኝነትን የሚሰብክ ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍልሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ - 510.530.3681 - www.eotcholysynod.info 4
በመሆኑ በጥር ወር በሎስ አንጀስ ከተማ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ
«ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በመንግሥት አስተባባሪነትና ደጋፊነት በሕገ ወጥ መንገድ
በተቀመጡት አባት ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን ክፉኛ የጎዳው መከፋፈል እና መለያየት ሳያንስ ፥
አሁን ደግሞ እነዚህ ጥቂት ጳጳሳት በሥልጣን ያለውን የመንግሥት ኃይል መከታ አድርገው
ፓትርያርክ ብለው የሚሰይሙትም፥አባትነቱ የሐሰት አባት ፥ ሹመቱም የሲሞን መሠርይ ስለ ሆነ
ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ያወግዘዋል ። በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ታዘዘው ፥
እውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች እስከ መጨረሻው ጸንተው በአንድነት እንዲቃወሙት ፥
እውቅና እንዳይሰጡትና እንዳይታዘዙት ቅዱስ ሲኖዶስ አስቀድሞ የአደራ መልእክቱን
ያስተላልፋል ። በተለይም ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ከፍተኛ መሥዋዕትነት በመክፈል
የቆሙ እውነተኛዎቹም አባቶች በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊዎች ሁነው በታሪክም
በእግዚአብሔርም ተወቃሾች እንዳይሆኑ ጥሪ ያደርጋል ።» ሲል ያስተላለፈውን ቃለ ውግዘት
በማክበር የሚሾመውን እንዳትቀበሉት በድጋሜ ጥሪውን ያቀርባል ።
2. በመላው ዓለም ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ሰላምና አንድነት ይቅደም ፣
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ብሎ ቢጮሁም ፣
የሕወሀት መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን የደገሰላት የማዳከምና የመከፋፈል መርሕ እንዲቀጥል
ስለ ፈለገ የቤተ ክርስቲያንን የልዩነትና የመከራ ዘመን ለማራዘም መንግሥት ግብረ - አበሮቹን
ይዞ በመሥራት ላይ ይገኛል ፤በቃልና በጽሑፍም የሐሰት መልእክት በማዘጋጀት በስደት ላይ
በሚገኙት አባቶች ላይና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየበተነ እውነቱን ወደ ሐሰት ፥ ሐሰቱን
ወደ እውነት ለመለወጥ ሲወድቅ ሲነሣ ይገኛልና ፤ አንድ ሁነን በእግዚአብሔር ስም
እንድንቃወመው፤ ቅ/ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል ።
3. በተለይ በውጪው ዓለም ተበትነን ያለነው በአገር ቤት በከባድ ቀንበር ሥር ያሉትን
ለእውነትና ለአንድነት የቆሙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፥ ካህናትና ምእመናንን ልናስብ ይገባል ።
በነጻነት ለመናገርና ለመጻፍ ለማይችሉት በሀገራችን ላሉት ሊቃነ ጳጳሳት ፥ ካህናት ፥ ገዳማውያን
አባቶችና እናቶቻችን ፣ ምእመናንና ምእመናት አንደበት በመሆን ስለ እነሱ እንድንናገር ፤ አንድ
ሆነን የአንድነትን ጠላት እድንቃወመው ፤ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ - 510.530.3681 - www.eotcholysynod.info 5
4. ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በመላው ዓለም ለማካሄድ ባቀደው ዓለም ዓቀፋዊ ጉባኤ
በመሳተፍና የሚመለከታቸውንም ሁሉ በማሳተፍ ስለ ቤተ ክርስቲያናችሁ ወቅታዊ ሁኔታ
ተገቢውን ግንዛቤና ትምህርት ለማግኘት በሚዘጋጁት ጉባኤያት እንድትሳተፉ ጥሪውን ያቀርባል ።
5. ስለ ፍትሕና ስለ እውነት እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሁነን ስለ
ሀገራችንና ስለ ሕዝባችን ሰላም ፣ ፍቅርና አንድነት እንድንሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን
ያቀርባል ። ቅዱስ ሲኖዶስም በልዩ ልዩ ምክንያት ተበታትኖ የኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን አንድ
ለማድረግና በአንድነት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ስለ ሀገራችንም ነጻነት ሠርቶ
ለማሠራት የማደራጃ መምሪያዎችን በማጠናከርና በማስፋት ፣ መንበረ
ፓትርይርኩን በማደራጀት ከፍተኛ ጥረት ላይ ይገኛል ። ስለዚህ እውነቱን እውነት ፥ ሐሰቱን
ሐሰት በማለት በእውነት አብረነው ልንቆም ይገባል ። መድኃኒታችን በወንጌል እንደ ተናገረ
እውነቱን ከመቀበል ሐሰቱን ሐሰት ከማለት መቆጠብ ከጠላት ዲያብሎስ ጋር ያስቆጥራልና ።
በመሆኑም በገለልተኛነት የቆዩትንና በአዲስ አበባ ሲኖዶስ ሥር የነበሩትን አብያተ
ክርስቲያናትም ሁሉ አንድ ሁነን ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ፣ በሕዝባችን ላይ የሚደርሰውን
እስራትና እንግልት እንዲወገድ በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታችንን ለመወጣት አቅም እንዲኖረን
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አብረው ይሠሩ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል ።
6. እንሚታወቀው አንድነታችንን የማይፈልገው ኃይል በስደት ያለችውን ቤተ ክርስቲያን
ለመከፋፈል ብዙ ሲሠራ እንደ ቆየ ሁሉ ፣ አሁንም ከሀገሩ ሰላም አጥቶ የተሰደደውን ሕዝብ
ለመከፋፈል በከፍተኛ ደረጃ እንደ ዘመተ ይታወቃል ። የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆችም በቤተ
ክርስቲያኒቱ ላይ በገሀድ በጠላትነት ለተነሣው ለዚህ ኃይል፥ መጠቀሚያ በመሆን
እግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያኑንም እንዳያሳዝን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል
። በግፍ በተሰደዱት ቅዱስ አባት አቡነ መርቆሬዎስ ላይም ሆነ አብረው በተሰደዱት አባቶች
ላይ የወንድሞች ከሳሽ የወደቀው እባብ የስድብ አፉን መክፈቱን እናውቃለን ። ነገር ግን መቼም
ቢሆን የቤተክርስቲያን አምላክ ከተሰደዱት አባቶች ተለይቶ አያውቅምና ሐሰተኛው አካል
አልተሳካለትም ፤ አይሳካለትምና እንደ ትናንቱ ዛሬም ነገም ጸንተን በእምነት እንቃወመው ።ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ - 510.530.3681 - www.eotcholysynod.info 6
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar