fredag 1. mars 2013
በስደት ላይ ከሚገኘው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን ሕገ ወጥ የፓትርያርክ ምርጫ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።
«ወይኩን ፥ ነገርክሙ፥እመሂ ፥ እወ ፥ እወ ፥ ወእመሂ ፥ አልቦ ፥ አልቦ ፤ ወፈድፋደሰ ፥
እምእሉ፥ እምእኩይ ፥ ውእቱ ።
ቃላችሁ እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለት ይሁን ከዚያ የወጣ ግን ከክፉው ነው» /ማቴ 5 ፥ 37/
መግቢያ
ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ቢንቀሳቀስም
፥ ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን አደራ ለምድራዊ ገዢዎች ያስረከቡ በአዲስ አበባ ያሉ ጥቂት
ጳጳሳት በሥልጣን ካለው መንግሥት ጋር በመተባበርና የሕዝበ ክርስቲያኑን ድምፅ በማፈን
የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በር በመዝጋት ላይ መሆናቸው ይታወቃል ። ያ አልበቃ
ብሎ ከቤተ መንግሥት ተረቅቆ በመጣላቸው መግለጫቸው ፥ ትላንት ከትናንት ወዲያ ቅዱስ
ፓትርያርኩ እያሉ በተናገሩበት አንደበት ፥ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ሕጋዊ
ፓትርያርክነታቸውን ለማስተባበል ሲሞክሩ ታይተዋል ። እነዚህ ራሳቸውን በከንቱ ለሚያልፍ
ነገር ያስገዙ ጥቂት ጳጳሳት ፥ በሃይማኖታቸው ጽኑ በሆኑት በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን
ፊት ተመዝነው የቀለሉና ፥ ታላቂቱን ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን የማይወክሉ ስለ ሆነ የአዲስ
አበባው መግለጫ ከትዝብት በስተቀር ምንም ቁም ነገር የለውም ።
በስደት ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲል የሚችለውን ሁሉ
አድርጓል ። ልዑካኑን ሰይሞ ቤተ ክርስቲያን አንድ ልትሆን የምትችልበትን መንገድ ለመፈለግ
ጥሮአል ። ነገር ግን በአዲስ አበባ በኩል የሰላሙ በር መዘጋቱን በመላው
ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ በልዩ ልዩ የዜና አውታሮች ይህንን ሁኔታ
እንደተገነዘባቻሁት ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል ። ለዚህም
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar