fredag 1. mars 2013

! ………… የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤና መዘዙ ……………! Source : Abraha Desta , Mekelle by freedomofspeech4 የኢህኣዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ እንደገና በኣንድ ወር ተራዝሞ በሚቀጥለው መጋቢት ወር እንደሚካሄድ ሰምተናል። ለምን ተላለፈ ብለን እንጠይቅ። የኢህኣዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ለማካሄድ መጀመርያ ኣራቱን ኣባል ድርጅቶች የየራሳቸውን ጉባኤ መጥራት ይጠበቅባቸዋል።



 ኣሁን የዘገየበት ምክንያት ታድያ በህወሓት ኣመራር ኣባላት መስማማ ት ስለጠፋ ነው። ህወሓት በሁለት እንደተከፈለ ሰምተን ነበር። ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ከካድሬዎች ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ዘመቻው ኣንዱን ቡዱን ሌላውን ቡዱን በሚቀጥለው የህወሓ ት ድርጅታዊ ጉባኤ ስብሰባ ከስራ ሃላፊነት (ከተመራጭነት) ለማስወገድ ያለመ ነበር። ነገር ግን በሚገርም ሁነታ ሁለቱም ቡድኖች በካድሬዎቻቸው ድጋፍ ኣላገኙም።
የፓርቲው ኣባላት በሁለቱም (ባጠቃላይ በህወሓት) እምነት እንደሌላቸው ኣስረግጠው ገልፀውላቸዋል። እናም ኣሁን ሁለቱም ቡድኖች ኣብረው ተሸብረዋል። እንደ መፍትሔም ከጉባኤ በፊት እርቅ እናስቀድም በሚል ሓሳብ የተስማሙ ይመስላሉ። (ሁለቱም ድጋፍ ስላጡ)።
እንደዉጤቱም ትናንት ለመታረቅ ስብሰባ ይዘው ዉለዋል። ግን ከሽፈዋል (ያለ ምንም ተስፋ ሰጪ ዉጤት ተበትነዋል)። ዛሬም ጥረቱ ቀጥሎ ውለዋል። ኣሁን የተለያዩበት (ግን ለመስማማ ት የሚፈልጉበት ) ኣስቸኳይ ኣጀንዳ ምንድነው?
መጀመርያ ግን ቡድኖቹ (ኣሁን ተሸምጋዮቹ):
(1) በኣባይ ወልዱ የሚመራ (በዋናነት እነ ኣዜብ መስፍን፣ ትርፉ ኪዳነማርያም፣ ተክለወይኒ ኣሰፋ፣ ሳሞራ ዮኑስ፣ በየነ መክሩ፣ ንጉስ ገብረ፣ ሓድሽ ዘነበ፣ ዓለም ገብረዋህድ ……) ሲሆኑ ልዩ ኣማካሪ : በረከት ሲሞዖን
(2) በደረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራ (እነ ኣርከበ ዕቁባይ፣ ፀጋይ በርሀ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ኣድሳለም ባሌማ፣ ፈትለዎርቅ ገ/ሄር፣ ተክለብርሃን ና ሌሎች ኣብዛኞቹ የማእከላይ ኮሚቴ ኣባላት) ሲሆኑ ል ዩ ኣማካሪ: ስብሃት ነጋ
ኣስታራቂ ሽማግሌዎች : ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ ቴድሮስ ኣድሓኖም፣ ኣዲሱ ለገሰ
መሃል ሰፋሪ (ግራ የተጋቡ): ስዩም መስፍን፣ ኣባይ ፀሃዬና ሌሎች በመከላከያና ደህንነት ያሉ፣ እንዲሁም መካከለኛ ኣባላት
ለሽምግልና የጋበዘ ኣጀንዳ: ለኢህኣዴግ ጉባኤ የሚሳተፉ ለመለየት የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ መጥራት ያስፈልጋል ወይስ የድሮ ኣባላት (ኣሁን በጉባኤ እንደተመረጡ በማስመሰል መላክ ) የሚል ነው።
የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ጉባኤ መጥራት የለብንም ብሎ በጥብቅ ይከራከራል። ምክንያቱ ጉባኤ ከተጠራ ምንም ድጋፍ እንደማያገኙና እነሱ እንደማይመረጡ እርግጠኛ ሁነዋል።

የነ ደብረፅዮን ግን ጉባኤ እንጥራ ባዮች ናቸው። በዚ ዙርያ ሁለቱም ቡድኖች ሊግባቡ ባለመቻላቸው ይሄን ለሽምግልና በቅተዋል። ግን ሁለቱም ድጋፍ ስለማያገኙ ለመታረቅ እየመኮሩ ነው። ከተስማሙ (ከታረቁ) ህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ ሳይጠራና ሳይመረጡ ወደ ኢህኣዴግ ጉባኤ ይገባሉ። (ባለፈው ጉባኤ የተመረጡ ማለት ነው)። ካልተስማሙ ግን ጉባኤ ይጠራሉ።
የኔ ኣባይ ወልዱ ቡዱን የቀድሞ የህወሓት የነበሩ ወደ ህወሓት እንዳይመለሱ ሲከራከሩ የነ ደብረፅዮን ደሞ መልሰን እናስገባቸው የሚል ኣቋም ይዘዋል።
ወጣት የህወሓት ኣባልት ግን ኣጠቃላይ ድርጅታዊ ግምገማና ተሃድሶ (reform) ያስፈልገናል፣ መተካካት ይኑር፣ ካልሆነ ግን ለኣሁኑ የህወሓት መሪዎች እውቅና ኣንሰጥም በሚል ኣቋማቸው ፀንተዋል።
ስለዚ በሽምግልና ምክንያት ሊራዘም ችሏል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar