lørdag 30. mars 2013
2013) ዓ.ም. (ይኸ ታሪክ ከሆነ ሰው ታሪክ ጋር ቢመሳሰል፣ በአፍ እላፊ)
አባባሱባት!
ወንድሙ መኰንን፣ አይልስበሪ፣ እንግላንድ መጋቢት ፲፰ ቀን ፪ሺ፭ (26 March
2013) ዓ.ም. (ይኸ ታሪክ ከሆነ ሰው ታሪክ ጋር ቢመሳሰል፣ በአፍ እላፊ)
አልጠየቅም!
መግቢያ
ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌ ጥቃት እንደተሰነዘረባት ነው። ክፉ
ክፉው መዘዝ የሚመዘዝባት፣ ሁዳዴ ጾም አካባቢ ነው። በዙ አሳልፋለች። ይንከባከቧታል ተብለው ታምነው የነበሩ ትላልቅ
አባቶች እየመዘበሯት ስላስቸገሩ፣ መነኲሴ አንዴ ሙቶ ተገንዟልና አደራ አይበላም ለገንዘብና ለሥልጣን አይጓጓም ተብለን
ለመነኲሴ ነኝ ባዩ ግለሰብ ቢያስረክቧት፣ እንኳን ሊሻላት እንዲያውም አባባሱና፣ አረፉ። በገንዘባችን የገዛናትን ቤተክርስቲያን
በሯን ጥርቅም አድርገው ዘግተው ሜዳ ላይ አፈሰሱን። ይኸ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ኃጢአት ነው፣ በሰው ፊት በሕግ
የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ያም ብቻ አይደለም። እንደምንሰማው ከሆነ አንድ ከአዲስ አበባ ተሾመው ለመጡት፣ የታጋይ
ጳውሎስ አቡን፣ ቁልፉን ለማስረከብ እየተደራደሩ እንደሆነ እንሰማለን። አይ መነኲሴ! አይ አባ! እኔን ያመንኲሰኝ። ለካንስ
ለእንዲህ ዓይነቱቹ ሕመም አባባሾች ነበር፣
ይሻላት እንደሆን፣ ገዳም ቢወሰዷት
ታማለች እያሉ፣ አባባሱባት።
ተበሎ የተገጠመው!
ከሥረ-መሠረቱ
የሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያናችን፣ ወያኔ ከገባ ጊዜ ጀምራ አንድም ጊዜ ሰላም አግኝታ አታውቅም።
እንዲሁ እንደታመሰች ነው። ምዕምኑ ቁም ሥቅሉን እንዳየ ነው። ሁሌ ግን አምላካችን እንደታደጋት፣ ዛሬን ደርሰናል።
የሚመጣላት እረኛ ሁሉ የጌታን መንጋ የሚበትን እንጂ የሚሰበስብ ሁኖ አልተገኘም። በተለይ ሹመት ብጤ ያላቸው፣ አቡን በሉ፣
ቆሞስ በሉ፣መነኲሴ በሉ፣ ሊቀ ካህናት በሉ፣ ... ሁሉም የጌታን በጎች የሚበትኑ የበግ ለምድ የለበሱ ተኲላዎች እንጂ የሚሰብስቡ
እረኞች ሁነው አልተገኙም። ገንዘብና ሥልጣን የማይበክለው ሰው ባይኖርም፣ የአሁኑ ይባስ!
ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ፣ መጋቢት ፬ ቀን ፪ሺ፭ በተለያዩ ድረ-ገጾች (ኢቲዮሜዲያ፣ ኢካዲኤፍ) በጻፉት ጦማር መነሻ ምንጩን
ቅልብጭ አድርገው አስቀምጠውልናልi
። ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም (24th
October 1993)፣ አሁን በቅርቡ መልአከ ሞት የገላገለን (አፈር ይክበዳቸው)
የወያኔ ሹመኛ ታጋይ ፓውሎስ፣ የሎንደን ሕዝብ እንዳይመጡብን እያለ፣ ሆድ
አደር፣ ሙሉጌታ አሥራተ እየመራቸው አመጣቸው። ከሰማይ በታች፣ ማንም
ሊደፍረኝ የሚችል ኃይል አይኖርም ባዩ ቀኖና አፍራሹ፣ የወያኔ ፓትሪያርክ
ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ሲመጡበት፣ የሎንደን ሕዝብ ተንጫጫ። ከምንም
ሳይቆጥሩት ገብተው ቀድሰው ሊወጡ ሲሞክሩ፣ በጀግኖቹ የኢትዮጵያውያ ልጆች
እጅ ድብድብ ተደረጉ። የ$50,000 ዶላር ሮሌክስ ሰዓታቸውን ወልቆ ወደቀባቸው።
አንዱ በቦክስ ሲያቀምሳቸው፣ ቆባቸው ከራሳቸው ላይ በረረች።ቆሌያቸውም አብሮ
ተገፈፈ። ደጋፊዎቻቸው “ምንስ ቢሆን፣ ጳጳስ እንዴት ይመታል!” እያሉ ተንጫጩ። ጌታ ኢይሱስስ ቢሆን፣ የአባቱን ቤት
ነጋዴዎች፣ ሌቦችና ቀማኞች ተንሠራፍተውበት ባየ ጊዜ ተናዶ፣ ጂራፍ ገምዶ እየገረፈ አልነበር ያባረራቸው! ምን አዲስ ነገር መጣ?
ሌባ ተይዞ ለመሆኑ ዱላ ይጠየቃል? ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ ባይኖር፣ ግብዐተ መሬታቸው በዚያን ዕለት በተፈጸመች ነበር። ያ
ተሳክቶ ቢሆን ኑሮ፣ እስከአሁንም በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱትን ውጥንቅጥ ጥፋቶች ባልደረሱ ነበር።
ዋልድባ ገዳምም ባልተደፈረ ነበር። ሮሌክሳቸውን እንኳን ከወደቀበት ሳያነሱ “ሾፌሬ አውጣኝ” ብለው ከዚያች ቦታ በርረው ጠፉ።
ለመሆኑ፣ ሮሌክስ ሰዓት መነኲሴ ያስራል ብላችሁ ገምታችሁ ታውቃላችሁ! ጉድ እኮ ነው! ሎንደኖች የዚያን ጊዜ አደጋ በዚሁ
ሁኔታ ተገላገሉት። አሁን ካጋጠመን አደጋ ግን አይብሰም! ያመኑት ፈረስ በደንደስ ይባል የለ? እንዲያ ሆኑበን አረፍነው። ያ ያኔ
ነበር። ዘንድሮስ በቤተክርስትያኗ አባብሰውባታል።
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar