fredag 29. mars 2013


እስከመቼ 

t n s&
መጋቢት ፳ ፻ ፬ ዓ. ም. ቁጥር ፻፪ 
March 2012, No. 102 
ባሁኑ ሰዓት በአማራው ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለው አማራን የማጥፋት ሴራ፤ 
ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚካሄደው ተግባር ዋናው አካል ነው። ክፍል ፪ 
( ethnic = ትስስረ - ትውልድ፤ politics = ነገረ 
አስተዳደር፤ economy = ቀመረ ንዋይ፤ ትርጉሞቹ የኛ )
አማራው ያለበትን ዕለታዊ የስቃይ ሁኔታና ይህ 
በአማራው ላይ ለምን እየተፈፀመ እንደሆነ ባለፈው 
ዕትማችን አሳይተናል። ይኼን በአማራው ላይ እየተፈፀመ 
ያለውን በደል፤ እኛ የወገን ( ዘር ) ማጥፋት በደል ብለን 
ፈርጀነዋል። በዚህ የዛሬው እስከመቼ እትማችን በዘር 
ማጥፋት መወንጀላችን በምን ተመርኩዘን እንደሆነ 
እናሳያለን።
እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር የ ፲፱፻፵፰ ዓመተ 
ምህረት የዘር ማጥፋት ወንጀልን የመከላከልና 
የአጥፊዎችን መቅጣት ጉባዔ፤ አንቀፅ ፪፤ የዘር ማጥፋትን 
እንዲህ ሲል ይዘረዝረዋል፤ 
“. . . ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ድርጊቶች፤ ሆን ብሎ 
ለማጥፋት፤ በጥቅል በሁሉም ላይ ሆነ በከፊሉ ወገን፤ 
በብሔር፣ በትስስረ-ትውልድ፣ በዘር ወይንም በሃይማኖት 
ቡድኖች ላይ፤ ለምሳሌ፤ 
ሀ) አባላትን መግደል
ለ) ከፍተኛ የሰውነት ወይንም የአእምሮ ጉዳት ማድረስ
ሐ) በዕቅድ፤ በቡድኑ የኑሮ ሁኔታ ላይ አጠቃላይ
ውድሚያ ወይንም ከፊሉን ከምደረ ገፅ ጠራረጎ
ለማጥፋት ጉዳት ማድረስ
መ) የቡድኑን የመራባት ሂደት ለማምከን የመውለድ
ዕርባታን ለማገድ እርምጃ መውሰድ
ሠ) የተወለዱ ሕፃናትን ከቡድኑ ነጥሎ ወደሌላ ቡድን
በግድ ማዛወር”
እዚህ ላይ ዋናው በትኩረት መታየት ያለበት፤ “ሆን ብሎ
ለማጥፋት” የሚለው ቃል ነው። እናም፤
 በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ምሥረት መርኀ ግብር
ውስጥ አራት ነጥቦች በግልፅ ሠፍረዋል። ትግራይን ነፃ
ለማውጣትና በሰላም የራሷ መንግሥት አቋቁማ
እንድትኖር በቁጥር አራት የሠፈረው፤ በአማራው
መቃብር ላይ የትግራይን የበላይነት እናቋቁማለን
ይላል። ከዚህ መመሪያ ሌላው ነገር ሁሉ ይመነዘራል።
 የአማራ መኖሪያ የሆኑትን የወገራ፣ የጠለምትና የዋግ
ክፍሎች ወደ ትግራይ ከልሎ፤ የዚሁ ቦታ ነዋሪዎች
የሆኑትን፤ ሀብታቸውን ዘርፎ እነሱን ከቦታቸው
አፈናቅሎ አባሯቸዋል። የሱዳን ደንበሩንም እንዲሁ።
 አማራው እስከዛሬ የበላይ ስለነበረ፤ ካሁን በኋላ ወደ
ሥልጣን እንዳይመጣ በሩን ለአማራው መዝጋት
አለብን ይላል። በተግባርም ፈፅሞታል።
 አማራው ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ተጠራርጎ ወጥቶ
በሠጠነው ክልል ብቻ ተዘግቶ ይኑር ይላል
ተግባራቸው። ይህም ደግሞ፤ ንብረታቸውን
በመንጠቅ፣ በእስር በማንገላታት፣ በመግደልና
በማባረር ተግብሮታል።
 የአማርኛ ተናጋሪ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ከሥራቸው
አባሮ፤ ሌላም ቦታ ሠርተው እንዳይበሉ አድርጓቸዋል።
በየመሥሪያ ቤቱ የነበሩትን አማራዎች በተመሳሳይ
መንገድ ከሥራ አፈናቅሏቸዋል።
 ደርግን አማራ እያለና የደርግን አረመኔነት የአማራ
አረመኔነት አድርጎ፤ አማራን የትግራይ ወገናችን
እንዲጠላው ማድረጉ፤ አማራውን የትግራይ ወገናችን
እንዲያጠፋው ሆን ብሎ ማዘጋጀቱ ነው። በትግራይ
ትምህርት ቤቶች፤ ይህ የደርግን አማራ ብሎ
ማስቀመጡ፤ ትምህርት ተብሎ እየተሠጠ ነው።
 የአማራ ድርጅት ብሎ ባቋቋመው፤ “ብሔራዊ አማራ
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” እንኳን፤ የሌላ ክፍል
ወገኖቻችንን የሆኑትን አባላት በአመራር አስቀምጧል።
 የአማራው ክልል ብሎ ባካለለው ቦታ የትግሬዎች ነፃ
አውጪ ግንባር ንብረት የሆነው EFFORT ቁልፍ
የልማት ቦታዎችን ከመውሰዱም ሌላ፤ በክልሉ በሙሉ
የበላይነት ያላቸው ትግሬዎቹ ናቸው።
 በዚሁ ክልል ተብየው የተቀመጠው የአማራው
ወገናችን፤ በማንነቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ
እየተደረገ፤ በያለበት በማንነቱ እየተሰደበና እየተዋረደ
ይገኛል። ስድቡን እዚህ ማስፈሩ ማራባት ይሆናል።
 በዚህ ሁሉ በሚደርስበት የዕለት ከዕለት በደል የተነሳ፤
ቦታውን ለቆ፣ ሀገሩን ጥሎ፣ ለበረሀ እንግልትና ለባህር
አሣ ምግብ ሆኖ፤ ብልቶቹ እየተቸረቸሩበት፣
በውርደትና ሀፍረት እየተሸማቀቀ ለስደት የተዳረገው
አብዛኛው የአማራው ወገናችን ነው።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar