lørdag 30. mars 2013
አይልስበሪ፣ እንግላንድ መጋቢት ፲፰ ቀን ፪ሺ፭ (26 March 2013) ዓ.ም. (ይኸ ታሪክ ከሆነ ሰው ታሪክ ጋር ቢመሳሰል፣ በአፍ እላፊ)
ኸ ሁሉ ሲሆን አንድ ጥሩ አጋጣሚ ለቤተክርስቲያናችን መጣ። ይኸውም፣ የተከራየናትን የቤተክርስቲያኗን ሕንጻ እንድንገዛ፣
ባለቤቶቹ መከሩን። አተካሮው ሁሉ ቆመና፣ ሁሉም ቤተክርስቲያኗን ለመግዛት መሯሯጥ ተጀመረ። አባም እዚህ ላይ ሊረሳ
የማይቻል ወሳኝ አዎንታዊ ሚና መጫውት ጀመሩ። ያን አድመኛ ጸባያቸውን በጉያቸው ወሽቀው፣ ትንሹንም ትልቁንም “አንቱ!”
እያሉ፣ ሁሉም ገንዘብ ማዋጣቱ ላይ እንዲረባረብ፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የማግባባት ችሎታቸውን ለደግ ነገር አዋሉት። ፍቅር
አሳዩን! እሳቸውም በሚገርም አኳኋን የተለወጡ መሰሉ። የታመመን ጠያቂ፣ ለተቸገረ አዛኝ፣ ለተበደለ ተቆርቋሪ ሆነው ተገኙ።
ሰላም ተገኘ። ፍቅር ታሸንፋለች ይባል የለ? በቃ አባ አውራ ሆኑ። ሰይጣን ፍቅር ቢያሳየን እንወደው ይሆን? እኛ እኮ ሞኞች ነን።
ከአባ በኋላ ፈራሁት! አድነነ፣ ከመዓቱ ሰውረነ!
ምርኮኞች!
ሁለተኛውን የቅዱስ ፓውሎስ መልዕክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፲፬ አንብቤ በጣም ገረመኝ። እንዲህ ይላል።
“ይኸ ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ፣ የብርሀንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” ወቸ ጉድ! ለዚህ ኑሯል ለካ ከኔ
ጀምሮ የኃጢአተኛው ቁጥር እንዲህ እንደ አሸዋ የሚበዛው! እየተታለልን፣ እየተሳብን መቀመቅ ገባን!
የአገራችን፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ፺፯ ሰባት መጣ። ወያኔ ወገናችንን ኢትዮጵያውያንን በጠራራ ጸሐይ ጨፈጨፈ። ከዚህ በፊት፣
(የቀሲስ አስተራዬን ቃል ልዋስናiii) አንድ ሁሌ የሚከዱን ሊቀ-ሊቃውንት “ደፍተራ” (ሆድ አደር ሙሉጌታ አሥራተ ካሳ
ቤተክርሲቲያን ሲያዘጋብን እሳቸውም ተባባሪ ነበሩ) “ፖሊቲካና ሀይማኖት አብረው” አይሄዱም እያሉ፣ “ወያኔን የምትቃወሙ
ቤትክርስቲያኗን ጥላችሁ ሂዱ” እስከማለት ደርሰው ስለነበረ፣ አንድም ቄስ አገራችን ውስጥ ለሚፈጸመው ጭፍጨፋ በግልጽ
መቃወሙ የማይታሰብ ነበር። አባ ያንን ግድግዳ፣ በምርጫ ፺፯ ወቅት ደረመሱት። ሎንደን ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ የሕዝብ
ወገንነታቸውን ያለማወላውል አውደ ምሕረቱ ላይ አወጁ! የተደረገውን ጭፍጨፋ አወግዙ! ምን???? ብዙዎቻችን ልባችን
ተተርትሮ ተፈታላችሁ። “እንዲህ ነው እንጂ አባት!” አልን። ከዚያም አልፈው ተርፈው፣ ከዚያ በፊት የማይታሰበውን፣ አባ፣
ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በድፍረት ሰተት ብለው መጥተው ተቀላቀሉን! እኔ ከዚያ በፊት ስሸሻቸው የኖርኩት ሀጢያተኛ፣
ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሳያቸው፣ ተንደርድሬ ሂጄ ነበር እግራቸው ሥር ተነጥፌ መስቀላቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳለምኩት! እጄን
ሰጠሁ። ተማረኩላቸው። ሌሎችም እንዲሁ! አሁንም ፍቅር ያሸንፋሉ ያሉት ይኸን ነበር ልካ! ከዚያ ወዲያማ ተውት! አባን
የሚያክል ካህን ከየት ሊመጣ! የሳቸውን ክፉ ነገር የሚያነሳብኝን ሁሉ የማርያም ጠላት ነበር አድርጌ የማየው። ቤተክርስቲያኗም
ጭፍጨፋውን በግልጽ አወገዘች። እሳቸውን ተከትለው፣ አንዳንድ ካህናትም ሰልፍ ላይ መገኘት ጀምሩ።እልልል!
የቤተክርስቲያኒቷ አስተዳዳሪ ምርጫ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2006 ላይ ደረሰ። አንድ እጃችንን ሳይሆን ሁለቱንም አውጥተን፣(ነውር
ባይሆን እግሮቻችንንም በጨምርን) አባን መረጥን። በሕዝብ ይሁንታ፣ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ሆኑ። ትዝ ይለኛል፣ አንድ
ወንድማችን፣ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር፣ የአባ የብዙ ጊዜ ወዳጅ፣ እሳቸው ሲመረጡ፣ እንዲህ ነበር ያላቸው።
“ቤተክርስቲያኑን እንዲያስተዳድሩ፣ በዲሞክራሲ (እኛ ሳናውቀው “በቴዎክራሲ” ይሆን የተመረጡት?) የመረጠዎት ይኸ ምዕምን
ነው። እዚህ ቦታ የሚቀመጡት፣ ለሶስት ዓመት ብቻ ነው። ከሶስት ዓመት በኋላ፣ ሌላ ምርጫ ይደረጋል። ሕዝቡ ከፈለገዎት
እንደገና ይመርጥዎታል። ይኸ ምዕምን እስከፈለገዎት ብቻ ነው ሥልጣን ላይ የሚቆዩት። መውረድ ሲገባዎት በሰላም ይወርዳሉ።
እስከዚያው ግን ደብራችንን ያስተዳድሩልናል።” ያስታውሰው ይሆን? ዳሩ ምን ያደርጋል! ነበር ሁኖ ቀረ እንጂ! ለማንኛውም አባ
ከተመረጡ በኋል ጥሩ ጥሩ ሥራዎችን አከናውነዋል። ቤተክርስቲያኗ እንደትገዛ ብዙ ጣሩ። አስተባበሩ። እኛም ገንዘባችንን
ዘረግፍን። ሴቷ የወርቅ ሀብሏን አውጥታ፣ የጆሮ ጌጧን አውልቃ ለቤተክርስቲያን አስረከበች። ደመውዝተኞቹ፣ በየዓመቱ አንዳንድ
ሺ ፖወንድ ለመስጠት ቃል ገብተን፣ ገፈገፍናት። ከሁሉ ከሁሉ የሚያሳዝነው፣ ሴቶች በየሳምንቱ፣ እንጀራ ጋግረው፣ ወጥ
ወጥውጠው ያመጡና ለቤተክርስቲያን መግዣ ተብሎ በብርድ እየተንቀጠቀጡ ቁመው ይሸጡ ነበር። ምን እሱ ብቻ! ያመጡትን
እንጀራ ሲርባቸው አይበሉም። ገንዘባቸውን አውጥተው የሠሩትን ምግብ ገዝተው ነበር የሚመገቡት። ዕውነቴን ነው!
ሎንደን ውስጥ የነበሩ አርቲስቶች በነቂስ ወጥተው ተአምር ሠሩ። “ያንተን ላንተ” የሚል መንፈሳዊ የመዝሙርና የድራማ ፕሮግራም
ሠርተው ሕዝቡን ቀስቀሰው ብዙ ሺ ብር አስገኙ። ያ ሲዲ/ዲቪዲ ከሎንደን አልፎ፣ አሜሪካን አገር እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤት
ገብቶ እስከዛሬ ይባርካል።
የአባ ዝነኛነት፣ ለአንዳንድ ካህናት አልተዋጠላቸውም። የሕዝብ ወገንተኛነታቸውንና፣ በጣም ተወዳጅ (popular) እየሆኑ
መምጣታቸውን ያዩ፣ ጨርሶ ማንም ካህን ከነሱ ቁጥጥር ውጪ እንዲሆን የማይፈልጉት፣ በፊት ከሳቸው ጋር አድመው
ለአስተዳዳሪነት ያበቋቸው አንዳንድ ካኅናት፣ አባን በነገር መጎነታተል ጀመሩ። አባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሕዝቡ መሀል ሥር
በመስደዳቸው እሳቸውን ነክቶ ማን በሰላም ሊኖር! ያ መሀይም ብለውት የነበረው ሕዝብ ይከላከልላቸው ገባ። ዕውነትም
መሐይሞች ነን። የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በትራፋልጋር ስኩዌር ሲከበር፣ አባ ቤተክርስቲያኗን ከጎናችን አሰለፏት። በዚያ ምክንያት
ከካህናት ተቀናቃኞቻቸው የተሰነዘረባቸውንም ጥቃት ሕዝብ ግድግዳ ሁኖላቸው ተከላከለላቸው። አባ ሕዝቡን ይዘው
ተቃዋሚዎቻቸውን ድባቅ መቱ። ይገርማል፣ አንዴ ካህናቱን ይዘው ይወቁናል፣ ሌላ ጊዜ እኛን ይዘው ያደበዩአቸዋል። እንደ አባ
ሰው ተጥቅሞ እንደማስቲካ የሚተፋ፣ ወያኔን ብቻ ነው ያዩት። ቤተክርስቲያኗን የመግዛት አቅማችንም እያደር ዕውን ሆነ።5
በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2005 ዓ.ም. ቤተክርስቲያኗ እጃችን ልትገባ ወራት እንደቀሯት፣ ሻጮቹም ረድተውን፣ የምንገዛበትን መንገድ
ሲያመቻቹልን፣ የውስጥ ቦርቧሪዎች ዜናውን አዲስ አበባ አደረሱት። የአዲስ አበባው ታጋዩ የወያኔ ፓትሪያርክ አንድ የሚያሳፍር
ነገር ሠሩ። እንደምንም የሻጮቹን አድራሻ ቆፍረው አግኝተው፣ “እኔ የማላውቃቸው፣ ከኔ ትዕዛዝ ውጭ ያፈነገጡ ክርስቲያን
ያልሆኑ አረመኔዎች ናቸውና፣ ለነሱ እንጻውን እንዳትሸጡት” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ያዘለች ደብዳቤ ጻፉላቸው። ድብዳቤዋም
ይኽቻት! 6
ደግሞ አያፍሩም “peace in Christ” ብለው ይፈርማሉ። ለመሆኑ የሰላምን ትርጉም ያውቁት ነበር? ከዚህ በኋላ፣ እንደገና አባ
አንድ ጀግንነት ፈጸሙ። ካህናትን አሰተባብረው ከዚያች ደቂቃ በኋላ፣ የአባ ፓውሎስን ስም ቤተክርስቲያኗ “ብጹዕ ወቅዱስ” ብላ
ላትጠራ አስወሰኑ! በአድራጎታቸው ተደስተን ተንጫጫን። የፊት ጉዳችንን መች አውቀን!
አባና ካኅናቱ ይኸን ሲያደርጉ፣ አንድ የታጋይ ጳውሎስ ወገን የሆኑ አባ ሙሴ የተባሉ አቡን፣ አባ ጳውሎስን አውግዘው፣ ጥገኝነት
ጠይቀው ድምጽ አጥፍተው፣ አድፍጠው አባን ሊፈነግሉ፣ አመቺ ቀን እየጠበቁ እመሀከላችን ይገኙ ነበር። ለካስ አባ ጳውሎስን
ያወገዙት፣ በጥገኝነት ሰበብ ነጻ ሕክምና ለማግኘት ኑሮ “የታጋይ ጳውሎስ ስም አይጠራም” ሲባል፣ “እንዴት ተደርጎ፣ ቡራ ከረዩ!
ፋሲካ ነጩ!” ብለው ደነፉብን። ውሳኔውን ያነበበውንም ወጣት ቄስ “አውግዤሀለሁ” ብለው ዓይናቸውን አጉረጠረጡበት። ሕዝቡ
ግን ጮኸባቸው። በዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያኗ ተከፋፍላ አደጋ ላይ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም ነበር። አደገኛ ቢሆንም፣ ከአሁን
የባሰ አልነበረም። አሁን ነው አባ ሆዬ ሕዝቡ ላይ ዙረው ያባባሱባት! የያኔው ችግር በቀላሉ ተፈታ። ያኮረፉት ወጋኖች አባ ሙሴን
ተከትለው ሌላ ቤተክርስቲያን፣ “ሥላሴ” ብለው መሠረቱ። ሥላሴም ለሁለት ተክፍሎ፣ ስላሴና ገብርኤል ተባሉ። የራሳቸው ጉዳይ!
ሰበካ ጉባዔው ከተመረጠ ሶስት ዓመት ቢያልፈውም፣ የቤተክርስቲያኗ ግዢ ስላልተጠናቀቀ፣ ሕዝቡ፣ የቤተክርስቲያኗ ግዢ
እስኪጠናቀቅና የተጀመረው መተዳደሪያ ደንብና የአደራ ሰነድ (ትረስት ዲድ - Trust Deed) የማሻሻል ሥራ ተጠናቆ በአባላት
አስከሚፀድቅ ድረስ ሰበካ ጉባዔው እንዳለ እንዲቀጥል፣ ወሰነ። እግዚአብሔር ረድቶን የቤትክርስቲያኗ ሙሉ ዕዳ ተከፈለ። በማን
እጅ በአደራነት ትቀምጥ የሚለው ጥያቄ ሲመጣ፣ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤው፤ እንደበፊቱ እንዲቀጥል፤ አባላትን ሳያማክር ወሰነ!
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2007 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያናችን፤ ስትገዛ፤ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በሙሉ
በጝዥዉ ላይ ቢፈርሙም ንብረቱን፤ በእንግሊዝ አገር ሕግ መሠረት፤ በግል ሰማቸው፤ ሕጋዊ ባላቤት በመሆን በአደራነት መያዝ
የሚችሉት አራት ግለሰቦች ብቻ ነበሩ። ቤተክርስቲያኗ እንደትገዛ በሙያቸውና በአርቆ አስተዋይነታቸው በዘዴ ዕውን ያስደርጉ
ወንድሞች (ዛሬ አባ በስልጣናችው አባረዋቸዋል) በጣም ጎበዞች ስለነበሩ፣ ሁለት ካህን እና ሁለት የሕዝብ ተወካዮች እጅ
የቤተክርስቲያኗ ንብረት በአደራ ይቀመጥ በሚል ሀሳብ ነገሩ በዚያ ተፈጸመ። ፈላጭ ቆራጩ አባ እኔ አንዱ መሆን አለብኝ ብለው
ቁልፏን ያዟት።
አባ በደንብ አብዛኞቻችንን በዲፕሎማሲ ከያዙን ብኋላ፣ ኢየሩሳሌም ሂደው በቆረጣ፣ የቆሞስነትን ማዕረግ፣ ከደብሮች አስተዳዳሪ፣
ከአሁኑ ፓትሪርክ፣ ከአባ ማቲያስ እጅ፣ ተቀብለው ተመለሱ። “ይደልዎ” አልን። “ቆሙስ” ከጳጳስነት አንድ እርከን ወረድ ብሎ ያለ
ማዕረግ ነው። አባ፣ ሁኔታቸው ገና ያልተሠበሩ ጎረምሳ ቢሆኑም፣ ዕድሜአቸውም ሆነ ግንፍልተኛነታቸው (unpredictable)
ባሳዩት ጀግንነት አድንቀን ዝም አልን። በተፈጥሮአችን የዋሆች አይደለንም? ሰሎሞን ተካልኝ፣ “ወይ ያኔ! ወይ ያኔ፣ አንተን አያርገኝ
የዚያን ቀን መጥኔ” ሲለን፣ በጫንቃችን ልንሸከመው ምን ቀረን? ልደቱ አያሌውንስ ቢሆን፣ አንድ ሰሞን ጸረ ወያኔ ሁኖ
እንደትንታግ ሲንጣጣ፣ ዕውነተኛ መሪ መስሎን፣ “ማንዴላ!” ብለን አውራችን አደርገነው አልነበር? ጉድ እና ጅራት ከወደኋላ ነው
እንዲሉ፣ ከተኛንበት የምንነቃው ከተበላን በኋላ መሆኑ አንዳንዴ ያናድደኛል። አባ በዚያ ሳይወሰኑ፣ አንድ አፍቃሪ ወያኔ አቡንም
በቀጥታ ዘው ብለው፣ የታጋይ ጳውሎስ ስም የማይጠራበት ማርያም ቤትክርስትያን መጥተው፣ “መልአክ ጽዩን” ብለው ሾሟቸው።
“ሊቀ-ሊቃውንቱንም” ደፍተራ “ሊቀ-ጠበብት” አሏቸው። አሁንም “ይሁን” ብለን ዝም አልን። ማን ደፍሮ አባን ሊቃወም!
በፊት፣ ከአባ ጋር ሁነው የተሳካለት መፈንቅለ መንበር ያደረጉት የተወሰኑ ዲያቆናት፣ ወደ ጎን ገሸሸ ስለተደረጉ፣ አባ ላይ አመጹ።
ለሥልጣን እንዳበቋቸው ሁሉ፣ በዚያው መንገድ ሊያወርዷቸው ሸራቸውን ሸረቡ። ወይ ካህናት! ምነው ባላውቃችሁ ኑሮ! ጉደኞች
አይደላችሁም እንዴ! በአንድ ዲያቆን መሪነት፣ ጎራ ለዩና የአባን ምትክ ማፈላለግ ጀመሩ። ሕዝቡን ከመጤፍ አለመቁጠራቸው
ገብቶን፣ “ተዉ” ብንላቸው አሁንም እንደበፊቱ “አሻፈረን! እናንተ ምን ታውቃላችሁ! አንሰማችሁም” አሉን። ሁለት ስሕተቶች
ሠሩ። አንዱ ስሕተት፣ አባን ለመገልበጥ በዋናኛው ሲታገል የነበረ ሊቀ ዲያቆን፣ አዲስ አበባ ሂዶ ከታግይ ጳውሎስ ጋር የተነሳው
ፎቶና ቪዲዮ መገኙቱ ነበር። እሱም አባ እጅ መግባቱ! ያም ባልጨነቀን ነበር፣ ምክኒያቱም ሌሎችም ዲያቆናት በሥፍራው ነበሩና!
ትልቁና ይቅር አይባሌው ስሕተት፣ ያ ዲያቆን ወደ ሎንደን ከተመለሰ በኋላ፣ እራሱ በበተነልን ደብዳቤ፣ "ተገንጥለው ከሂዱት
የሥላሴና የገብርዔል ቤተክርስቲያናት ጋር ታርቀን ተመልሰን አንድ እንሁን" ማለቱ ነበር። የታጋይ ጳውሎስ ስም እንደገና ሊጠራ?
ያ እንዴት ይሆናል ብለን ተቃወምን። እኔም አባን ከነዚህ ሿሚ-ሻሪዎች (king makers) ለመከላከል በስተመጨረሻ የሚታየውን
ማጣቀሻ ጻፍኩiv። አንዳንዴ ከሰው ጋር ቢጋጩም፣ “አባ ግልፈተኛ ናቸው እንጂ ክፉ አይደሉም” እያልን ተሟገትንላቸው። አይ
የዋህነታቸን! እነዚያ ወጣቶች አካሄዳቸው ለቤተክርስቲያኗ አደገኛ ነበር። እንዳሁኑ ግን አላሰጋትም። አሁን እራሳቸው አባባሱባት።
እብድ ቢጨምት እስከ እኩለ ቀን ነው።
የቤተክርስቲያኗ ዕዳ ተከፍሎ ካለቀ በኋላ፣ አባ ለየት ያለ ጸባይ ማምጣት ጀመሩ። የግል ነብረታቸው አደረጓት። ቤተክርስቲያኗን
በተመለከተ አንዳንድ ክሶች በጠላቶቿ መምጣት ጀምሯል። የውስጥ አዋቂ ተቀናቃኞቻቸው ብለውት እንደነበረው አባ
እንደፈለጉ፣ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ መበደር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሥን-ሥርዓት ይኑር እያሉ ቀድሞ የተነሱባቸው ሰዎች
የጻፉት፣ ከታጋይ ጳዎሎስ ጋር መተሳሰራቸው ከፋ እንጂ፣ አባን በተመለከተ ያሏቸው ነገሮች ትክክለኞች ሁነው ተገኙ። መተዳደሪያ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar