onsdag 3. juli 2013
አማራው ያሬድ አይቼህ” ደግሞ ምን ፍጠሩ እያለን ይሆን?
አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል፡፡ የወደቀም ግንድ ምሣር ይበዛበታል፡፡ ኢትዮጵያም ቀን ጣላትና፣ ቀን ጣላትናም በጠላቶቿ እጅ ወደቀችና፣ በጠላቶቿ እጅ ወደቀችናም የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሳትና ይሄውላችሁ በየቀኑ ተነግሮ የማንሰማው ተጽፎም የማናነበው ነገር የሌለን ሆነን ዐረፍነው፡፡ የገዛ ልጆቿም እየከዷት አንዱ ወግጂልኝ ይላታል ሌላው ለርሷ ለመሞት ቆርጦ ተሰልፎላታል፡፡ ደርግ ጥሩ አማርኛ ነበረቺው፡- ‹የእናት ጡት ነካሽ› የምትል፡፡ ዛሬ ዛሬማ የእናት ጡት ነካሽ ብቻ ሳይሆን ባት ቆራጭም፣ ማጅራት ገትርም ማለቴ ማጅራት መቺም፤ አነጣጥሮ አናት በርቋሽም ልጅ ሞልቶናል – የልጅ በያይነቱና ማኅበራዊ በብፌ መልክ በሽበሽ ብሎ ፊታችን ላይ ተዘርግቶልናል (የምግብ ስሞች ናቸው)፡፡ የበዓሉ ግርማ የምናብ ፍጡር የሆነው የካድማስ ባሻገሩ አበራ፣ ገነት ሆቴል የፋሲካ ዋዜማ የጦፈ ዳንስ ላይ የአምቦዋ ሳዱላ ሉሊት ታደሰ ስሟን እንድትነግረው ሦስቴ ጨቅጭቆ ላለመንገር ደጅ ስታስጠናው ‹ከነስምሽ ገደል ልትገቢ ትችያለሽ› እንዳላት ዓይነት ጃዋር ሲራጅን ዓይነቱ ወያኔ ዘራሽ ጎረምሳ በ‹ጤፍ ብድር ሳይቸግር› እንዲያው ከሜዳ ይነሣና ‹ኦሮሞነቴን ካልተቀበላችሁ ከነኢትዮጵያችሁ ገድል ልትገቡ ትችላላችሁ› እያለ ይዝትብናል – ከነገር አባቶቹና አሰልጣኞቹ (አሰይጣኞቹ ብልም ያው ነው) ከነሌንጮ ለታ የቀሰመውን እንጂ እርሱማ በጥቂቶች ጥፋት የተነሣ ያን በክፉነት የሚታማውን ዘመን የት ደርሶበት፡፡ እኛ የኢትዮጵያዊነትን መቁነን የምንሰጥ ወይ የምንነሣ ይመስል በማናውቀው ነገር በትዝታና በታሪክ ዋሻ ውስጥ መሽገውና በአስተሳሰብ ላለማደግ ምለው ትናንትም ዛሬም እዚያው የሚኖሩ በሽተኞች ይነተርኩናል፡፡ ‹ጌታውን ቢፈሩ ገበር ገበሩን› ይባላል፡፡
ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ
በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች
መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው
እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው
እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት
ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ - ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣
አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና
መጠላለፍ ነው ብለዋል።
“አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ
mandag 1. juli 2013
የአብዬን ወደ እምዬ

የወያኔ ዘረኞች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች በሙሉ በፀረ-ኢትዮጵያዊነትና የአገርን ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ በመሸጥ ሲከስሱ ስንሰማ አይናቸዉንና ፊታቸዉን ታጥበዉ አይነ ደረቅ ለመመሰል ስንት ኪሎ ጨው እንደፈጀባቸዉ መገመት ያዳግታል።
በአገራችን ታሪክ ውስጥ እንደወያኔ በኢትዮጵያ ህልውናና በወሳኝና ዘላቂ ጥቅሞቿ ላይ የዘመተ ኃይል ኖሮም ተፈጥሮም አያውቅም። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀግኖች አባቶቻችን አጽም ያረፈበትን መሬት በስጦታ ለጎረቤት አገር እናካችሁ ብሎ የሰጠ ማነዉ? ማነው በሽፍትነት ዘመኑ ለተደረገለት ውለታና ተቀናቃኞቹን እንዲጠብቁለት በማሰብ የኢትዮጵያን ድንበር እንደ ዳቦ እየገመሰ ለባዕዳን የሸጠው?
ማነው የገዛ ወገኑን ከአያት ቅድመ አያት አጽመ ርስቱ ላይ እያፈናቀለ አንድ ሲኒ ቡና በማይገዛ ገንዛብ ለምለም መሬታችንን ለባእዳን የሚያቀራምተው? ማነው በህዝብ ስም በልመናና በችሮታ የተገኘን ገንዘብ እየዘረፈ ከአገርና ከህዝብ ደብቆ የባእድ አገር ባንኮችን የሚያደልበው? ኢትዮጵያ በሶማሊያ በተወረረችበት በ1970ዎቹ አመታት የሞቃዲሾን ፓስፖርት ተሸክመው ይንጎማለሉ የነበሩት የዛሬዎቹ የወያኔ አለቆች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ገና አልረሳዉምኮ!
የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎች ትናንት የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ማየት ከማይፈልጉ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር እጅና ጓንት ሆነዉ የኛን የጎሳ ድርጅት እስከረዳችሁ ድረስ ኢትዮጵያን እናደክምላችኋለን የሚሉ ጸረ አገርና ጸረ ህዝቦች ነበሩ።እነዚህ የለየላቸዉ ከሀዲዎች ዛሬ አይናቸዉን በጨው አጥበዉ እራሳቸዉን የኢትዮጵያ ጥቅም አስከባሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ለአገር አንድነት መከበር የሚታገሉትን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች የአገር ጠላት ብሎ ለመጥራት የሚያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል የሞራል ብቃት የላቸውም።
ወያኔዎች ስልጣን በያዙ ማግስት በጻፉትና እነሱን ሲጠቅም በሚጠቅሱት አገርንና ህዝብን ሲጠቅም ግን እየዳጡ በሚያልፉት ህገመንግስት ዉስጥ ደደቢት በረሃ የወሰዳቸዉን ዋነኛ አላማ መገነጣጠልን እንደ አገር ጥቅም በጹሁፍ ካልሰፈረ ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የነበሩበትን ጊዜ እኛ የኢትዮጵያ ነገር የሚቆረቁረን ወገኖች አልረሳነውም። ለመሆኑ ሌሎችን በጸረ-ኢትዮጵያዊነት የሚከሰው ወያኔ እውነት ኢትዮጵያን ከወደደ መገነጣጠልን ለምን ተመኘላት? መገነጣጠልን የመሰለ አደጋ እንደ ብሔራዊ የአገር ጥቅም አይቶ የራሱን ምኞት በህግመንግስት ደረጃ ያጸደቀዉ ወያኔ እንዴት ሆኖ ነው ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር የሚጋደሉና የሚታገሉ ልጆቿን በሀገር ጠላትነት የሚከስሰው? የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ጋር የሚደረገዉን ትግል ከመብትና ከነጻነት ትግል ባሻገር እንደ አገር አድን ትግል አድርጎ የሚመለከተዉ ይህንኑ ወያኔ በአገራችን ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ በተደጋጋሚ ያሳየዉን ጠላትነት በመገንዘብ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎችን በጅምላ የአገር ጠላት ለማስመሰል በሚቆጣጠራቸዉ የመገናኛ አዉታሮችና በታማኝ ሎሌዎቹ በኩል የጀመረዉን የስም ማጥፋት ዘመቻ ከወዲሁ ተረድቶ “የአብዬን ወደ እምዬ” ብሎ ትግሉን ከቀጠለ ዉሎ አድሯል። ወያኔና ለሆዳቸው ያደሩ ሎሌዎች ሁለመናቸውን የወረሰውን የፀረ-ህዝብና ጸረ ኢትዮጵያዊነት እከክ ማንም ላይ ማራገፍ አይችሉም። ድፍን ኢትዮጵያ ማንነታቸውን አሳምሮ ያውቃልና።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል
(ከኢየሩሳሌም
አርአያ)
የብረታ
ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ
በኋላ
በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች
መካከል
አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው
እንደነበር
አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው
እንደሆነ
ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት
ስር
እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ - ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣
አክለውም
ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና
መጠላለፍ
ነው ብለዋል።
ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ
ከስልጣን
ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት
ስልጣኑ
በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም - በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ
ከመሆኑ
በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን
መሆኑን
ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር
ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-
ወጥ
በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል።
ይህ
በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን
ምንጮች
ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም
፥
« ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ
ተቃዋሚዎች
ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን
እንዲሁም
« አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ
ያለውን
ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በሌላም
በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር
ረቀቅ
ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ
መሆኑን
ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ
የእንቅስቃሴው
ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም
ለመንግስት
ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።
በዚህም
ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ
እንደሆነ
ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም
የሚያውቁት
እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ - መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ
ቢደነግግም፣
ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና
ማሳያ
መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።
በመጨረሻም፥
የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ
ንግድ
መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።
ኢትዮሚድያ
- Ethiomedia.com
June 29, 2013
በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀው መከላከያ ሂሳቡ እንዳይመረመር ታዘዘ
እንዳይመረመር ታዘዘ
-የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት የመከላከያና የደህንነት ተቋማት
የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ
እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማው ባቀረቡት የ2004 ዓ.ም
የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ ሪፖርት በተለይ በዘጠኝ መ/ቤቶች 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር
ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኖ መገኘቱን፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑን
መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህ ተቋማት ላወጡት ገንዘብ ትክክለኛ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቀውም ማቅረብ አለመቻላቸውን ለፓርላማው
ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈረጌሳን ጨምሮ የተለያዩ ሹማምንት ሪፖርቱን
በአደባባይ እስከማብጠልጠል የደረሰ ትችት ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ዋናው መከራከሪያቸውም የመከላከያ ወጪ ሚስጢር
ነው የሚል ነበር፡፡
የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ
እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማው ባቀረቡት የ2004 ዓ.ም
የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ ሪፖርት በተለይ በዘጠኝ መ/ቤቶች 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር
ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኖ መገኘቱን፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑን
መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህ ተቋማት ላወጡት ገንዘብ ትክክለኛ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቀውም ማቅረብ አለመቻላቸውን ለፓርላማው
ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈረጌሳን ጨምሮ የተለያዩ ሹማምንት ሪፖርቱን
በአደባባይ እስከማብጠልጠል የደረሰ ትችት ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ዋናው መከራከሪያቸውም የመከላከያ ወጪ ሚስጢር
ነው የሚል ነበር፡፡
ይህንን ተከትሎ የፓርላማ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በቴሌቪዥን ቀርበው “ባልተሟላ ሰነድ
ወጪ ተደረገ ማለት ብሩ ተበላ ማለት አይደለም” በማለት ማብራሪያ ለመስጠትና ተቋሙን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡
ወጪ ተደረገ ማለት ብሩ ተበላ ማለት አይደለም” በማለት ማብራሪያ ለመስጠትና ተቋሙን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያቸው የሆነውን መግለጫ ትላንት ጠዋት
በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት በተመሳሳይ መንገድ መከላከያን ኦዲት ማድረግ
ሚስጢር ማባከን መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ሁኔታውን ለማስተካከል አዲስ ሕግ እንደሚወጣ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በአዋጅ ቁጥር 669/2002 መሰረት የፌዴራል የመንግስት ተቋማትን ኦዲት የማድረግና የማስደረግ ሙሉ ሥልጣን
በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት በተመሳሳይ መንገድ መከላከያን ኦዲት ማድረግ
ሚስጢር ማባከን መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ሁኔታውን ለማስተካከል አዲስ ሕግ እንደሚወጣ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በአዋጅ ቁጥር 669/2002 መሰረት የፌዴራል የመንግስት ተቋማትን ኦዲት የማድረግና የማስደረግ ሙሉ ሥልጣን
እንደተሰጠው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አስታውሰው በዚህ ሕግ መሰረት ባለፉት ዓመታትም መከላከያን ጨምሮ ሁሉንም ተቋማት ኦዲት ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በሚያዚያ ወር 2004 ዓ.ም የ2003 የሂሳብ ሪፖርት ለፓርላማው ቀርቦ እንደነበር በዚህም ሪፖርት መሰረት
ከተወቀሱት ተቋማት መካከል መከላከያ አንዱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት በመከላከያ 133 ነጥብ
8 ሚሊየን ብር ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩን፣ የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በወጪ
ተመዝግቦ መገኘቱን ሪፖርት አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ገንዘብ መካከል 1
ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የመከላከያ ሲሆን ፣ 54 ነጥብ 3 ሚሊየን ደግሞ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ 33
ነጥብ 34 ሚሊየን ብር የአገር ውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ መሆኑ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መ/ቤቱ
እንደዘንድሮ ከፍተኛ ቅሬታ ያላቀረበ ሲሆን የዘንድሮ ቅሬታ ምናልባትም በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ላይ ተጽዕኖ በማሳደር
ነገሩን ለመሸፋፈን የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
8 ሚሊየን ብር ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩን፣ የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በወጪ
ተመዝግቦ መገኘቱን ሪፖርት አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ገንዘብ መካከል 1
ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የመከላከያ ሲሆን ፣ 54 ነጥብ 3 ሚሊየን ደግሞ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ 33
ነጥብ 34 ሚሊየን ብር የአገር ውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ መሆኑ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መ/ቤቱ
እንደዘንድሮ ከፍተኛ ቅሬታ ያላቀረበ ሲሆን የዘንድሮ ቅሬታ ምናልባትም በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ላይ ተጽዕኖ በማሳደር
ነገሩን ለመሸፋፈን የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
ምንጮቻችን እንደገለጹት በአገሪቱ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው ተቋማት መካከል ግንባር ቀደሙ መከላከያ መሆኑን
አስታውሰው አንድ ወርሃዊ ደመወዙ 4 ሺ ብር የማይሞላ ከፍተኛ የመከላከያ ሹም በአዲስአበባ ቁልፍ ቦታዎች ጭምር
በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቪላዎችንና ሕንጻዎችን የሚገነባበት እንዲሁም ትልልቅ ንግዶችን የሚያንቀሳቅስበት ሁኔታ
የአደባባይ ሚስጢር ነው በማለት የእነአቶ ኃይለማርያም ሙግት ጥቅሙ ለሙሰኞቹ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ ሕግ በቀጣይ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዋና ኦዲተር ሕጉ እስኪጸድቅ
መከላከያና የደህንነት ተቋማትን ኦዲት እንዳያደርግ መታዘዙንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
አስታውሰው አንድ ወርሃዊ ደመወዙ 4 ሺ ብር የማይሞላ ከፍተኛ የመከላከያ ሹም በአዲስአበባ ቁልፍ ቦታዎች ጭምር
በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቪላዎችንና ሕንጻዎችን የሚገነባበት እንዲሁም ትልልቅ ንግዶችን የሚያንቀሳቅስበት ሁኔታ
የአደባባይ ሚስጢር ነው በማለት የእነአቶ ኃይለማርያም ሙግት ጥቅሙ ለሙሰኞቹ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ ሕግ በቀጣይ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዋና ኦዲተር ሕጉ እስኪጸድቅ
መከላከያና የደህንነት ተቋማትን ኦዲት እንዳያደርግ መታዘዙንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 60 ከፍተኛ ጀኔራሎች መካከል 58ቱ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሀት አባል ሆነው የመጡ ናቸው።
መከላከያን ከላይ ሆነው የሚዘወሩት 7ቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በሙሉ የህወሀት ታጋዮች ናቸው። ባለፉት 22 አመታት በዚህ ከፍተኛ
አመራር ውስጥ የሌላ ብሄር ተወላጅ ተካቶ አያውቅም።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሀይለማርያም በአባይ ግድብ ዙሪያ ከተቃዋሚዎች ጋር እንደማይነጋገሩ አስታውቀዋል።
ኢሳት ዜና
Abonner på:
Innlegg (Atom)