onsdag 7. mai 2014

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች

(ተመስገን ደሳለኝ) 

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው 
ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” 
ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን 
እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-
መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን 
የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ራሱ መለስ ዜናዊ በድህረ 
ምርጫ 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ዘብጥያ ወርደው የነበሩትን የቅንጅት አመራሮች “ከእስር 
እንዲፈቱ ብፈልግም አክራሪው ኃይል ተቃወመኝ” ማለቱን ዊክሊክስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የአሜሪካ 
አምባሳደርን ጠቅሶ ይፋ ማድረጉ ይህንኑ ያስረግጣል፡፡ የአምባሳደሩ መረጃ የተጋነነ፤ አሊያም “ተጋግሮ 
የቀረበለት ነው” ሊባል ቢችል እንኳ “ጭስ በሌለበት…” እንዲሉ፤ በግንባሩ ውስጥ አክራሪ ኃይል ለመኖሩ 
በጠቋሚነት ሊወሰድ ይችላል፡፡
 

ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ መለስን ከተካበት ዕለት አንስቶ፣ ያደረጋቸው ዲስኩሮችም ሆኑ ለቀረቡለት ጥያቄ የሰጣቸው ምላሾች በአክራሪው 
ኃይል ተጽእኖ ሥር ማደሩን ያሳያል፡፡ የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ቢሆን፣ በአቅመ ደካማ የመጠቀም የፖለቲካ ጨዋታው የሰነበተ 
መሆኑን ያመላክታል፡፡ ኃይለማርያም ከሹመቱ በኋላ ከባሕሪው አፈንግጦ፣ ዝነኛዋን የመለስ ዜናዊን ሕዝባዊ ሽብር መፍጠሪያ ‹‹ቀይ 
መስመር››ን፤ ‹‹እሳት መጨበጥ›› በሚል ተክቶ የተቃውሞ እንቅስቃሴን በሙሉ እስከማስፈራራት መገፋቱም የዚሁ ውጤት 
ይመስለኛል። በተቀረ እርሱ ወደ ሥልጣን በመጣበት መጀመሪያ አካባቢ፣ ‹‹ኃይማኖተኛ››ነቱን ብቻ በመጥቀስ ‹‹ቤቴን የወንበዴዎች ዋሻ 
አደረጋችሁት›› በሚል ሥርዓታዊ ማፍያነትን ባደራጁ ጓደኞቹ ላይ ጅራፍ እስከማወናጨፍ ይደርሳል ተብሎ መገመቱ፣ በግንባሩ ውስጥ 
የተንሰራፋውን አክራሪ ኃይል በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እዚህ ጋ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ጥቅምት 10 ቀን 
2005 ዓ.ም የወጣው ‹‹ሪፖርተር ጋዜጣ›› በልዩ እትሙ፣ ኃይለማርያም ‹‹ቄስ›› ተብሎ ሊቀባ አንድ ወር ሲቀረው በትምህርት ምክንያት 
ከሀገር እንደወጣ ካስነበበበት ጋር የሚያያዘው ነው፡፡ ወደ ፖለቲካው ከመቀላቀሉ በፊት የሚያመልክበትን ‹‹የኢትዮጵያ ሐዋርያት 
ቤተክርስቲያን›› ቄስ ህዝቅኤል ጎዴቦን ‹‹ፖለቲካ ውስጥ መግባት ሀጢአት አይሆንብኝምን?›› ሲል መጠየቁን ጋዜጣው አትቷል፡፡ ግና፣ 
ምን ዋጋ አለው? ባልተጠበቀ ፍጥነት ከተራ ፖለቲከኝነት አልፎ የሀገሪቱ መሪ ለመሆን በመብቃቱ፣ ‹‹ቅስና››ው በመንገድ ሊቀር ተገደደ 
እንጂ፡፡ እርሱም ቢሆን ዛሬ እንዲህ አይነት ጥያቄ አያነሳም፤ በፈሪሃ እግዚአብሔሩም ቦታ፣ ፈሪሃ ኢህአዴግ ተተክቷል፡፡ እናም 
ከእስልምና መንፈሳዊ መሪዎች እስከ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ያሉ ንፁሀን፣ በራሱ አነጋገር ‹‹እሳት በመጨበጣቸው›› ወደ 
‹‹ቃሊቲ›› ተላልፈው ምድራዊውን ገሀነም ይቀበሉ ዘንድ ቡራኬ ሰጥቷል፡፡ 

 ሰሞነኛው ጉዳይ 
አቶ ኃይለማርያም በስድስት ወር (በጥር) ለተወካዮች ም/ቤት ማቅረብ የነበረበትን ሪፖርት በዘጠኝ ወሩ ባለፈው ሳምንት ባቀረበበት 
ወቅት፣ ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ማሻሻያ መጠበቁ የዋህነት እንደሆነ የጠቆመን፣ የም/ቤቱ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የጠበበው 
ምህዳርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ‹‹ዲሞክራሲ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ አይጠጣም (ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ በቀጣዩ ወር ሃያ 
ሁለተኛ አመቱን መድፈኑን ልብ ይሏል)፣ ዲሞክራሲ ህልውናችን ነው፣ ቀይ ምንጣፍ አናነጥፍም...›› ጅኒ ቁልቋል በሚሉ የእብሪት 
ገለፃዎች ማለፉ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ሪፖርቱ በሀሰተኛና በማደናገሪያ ዘገባዎች የታጀለ እንደነበረ መታዘብ ተችሏል፡፡ ለማሳያነትም 
ያህል ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡- 

 ‹‹ዕድገት›› ሲባል… 
የኢኮኖሚ ዕድገትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፖርቱ ላይ ‹‹የሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ሂደት ሲታይ ላለፉት አስር ዓመት 
(ከ1996-2005) በየዓመቱ በአማካይ 10.9 በመቶ በማደግ ከፍ ባለ የእድገት ጉዞ (Trajectory) ውስጥ መሆኑን አመላክቷል›› ሲል 
ነግሮናል፡፡ ይሁንና አስሩን ዓመት ትተን የዘንድሮውን በመሬት ላይ ያለውን እውነት እንኳ ብንመለከት የሚያሳየው ተቃራኒውን 
ስለመሆኑ ለራሱም ቢሆን ይጠፋዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በአገሪቱ ሥራ-አጥነት (በከተሞች 40 በመቶ መድረሱን ጥናቶች 
ይጠቁማሉ) በአስከፊ መልኩ ተንሰራፍቶ፣ ስደት ዕጣ-ፈንታ ተደርጎ ኩብለላ የዕለት ተግባር በሆነበት፣ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ በኑሮ 
ውድነት እንደ ከባድ ማዕበል ወደላይ ጎኖ፣ ቁልቁል በአናት እየተተከለ በሚንገላታበት፣ ጎዳናዎች ቀን ቀን ልመና በወጡ ምንዱባን፣ 
ማታ ማታ ደግሞ ነፍሳቸውን ለማቆየት የሚውተረተሩ በዕድሜም በአካልም ትናንሽ የሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ተጥለቅልቆ… ባለበት በዚህ 
ዘመን ‹በየዓመቱ በአማካኝ 10 በመቶ እያደግን ነው› የሚልን አላጋጭ ሪፖርትን ሰምቶ በቸልታ ማለፉ ሰው የመሆን ጉዳይንም ፈተና 
ላይ መጣሉ አይቀርም፡፡ 

 በዚህ ለሶስት ወራት በዘገየው ሪፖርት የዋጋ ንረትን ከአንድ አሃዝ እንዳያልፍ እየተሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡ ከ1987 ዓ.ም 
ጀምሮ ከየምርጫው አንድ ዓመት በፊት በመለስ ዜናዊ ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶች እንዲህ አይነት የዋጋ ንረት እንደሚቀንስ የ‹‹ሚያበስሩ›› 
እንደነበር ይታወሳል፡፡ የኃይለማርያምም ሪፖርት፣ ፓርቲው በምርጫ ዘመቻው ወቅት ሁሌ እንደ ስልት የሚጠቀምበትን ይህንን ጉዳይ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar