onsdag 7. mai 2014

በኖርዌይ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያኖች ዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ና የሰራትእኞች ከባለፉት ዓመታት ለየት ባለ መልከ አክበርን

 ያለመታድል  ጉዳይ ሆኖ በሀገር ውጭም ያለነው ኢትዮጵያን አልፎ አልፎ ያለመጣማም፡ሁኔታውች ይታዩብናል በዚህም  ክናየት ሳናውቀው  የዋያኔን የቤት ስራ  ስንሰራ እንገኛለን  ማለትም  ወያኔ ያስቀመጠልን  የማይሻር የርስ በርስ ብጥብጥ በዘርና በጉጥ መለያየትን  እንደጥሩ ተግባር ስንተገብር እንታያለን ..፡፡
የ2014 ሜይ ደይ ከባለፈት ዓመታት ለየት የሚያደርገው የወያኔ መንግስት የስርዓቱ ደጋፊወች በዝህ ባዕል ላይ መሳተፋቸው ነበር ፡፡በዝህ ስርዓ ላይ ትልቁን ሚና የተጫወቱት  አክቲቢስ  አቶ አምሳል ካሳየ ናቸው   በዝህ ስርዓት ምንም ዓይነት ልዮለት ሊኖረን አይገባም  በማለት ከሁለት ቦታላይ የነበረውን እውነተኛ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የሚያወለበልቡትን  ሕዝቦች  በአንድላይ  በማጣመር  ሰልፉ የኦስሎን ከተማ እንዲያጥለቅልቅ  አድርገዋል እኔም ከሰልፈኞቹ ፡አንዱ ስሆን  ዳርላይ ቆም በማለት አንዳንድ የታዘብኳቸው  ነገሮች ነበሩኝ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅትኖርዌይ አባላት መፍክር ሲያሰሙ በኢሃፓሰም የተቀላቀሉት የውያኔ ጀሌወች  መፈከሩን ላለመቀበል ሰልፉን  የሽምጥ ግልቢያ አስመስለውት   ነበር ፡ አንዳንዶቹም  የማይሰማ  የርስበርስ ጉርምርምታ እርስበርስ  ሲለዋወጡ ይታዮ ነበር  እኔ ሰልፈን የትካፈልኩት  የአቶ አምሳልን  የድፕሎማሲ ሲስተም  ለመቀበል እንጂ  የህጻን ነብዮ እና የሽብሬ  ደም ከጁላይ  ካለሰው ጋር ምንም አይነት  ድርድር አላደርግም ፡፡
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅትኖርዌይ በዛሬው ቀን በኖርዌይ በተከበረው አለም አቀ የሰራተኞች ቀን ላይ በመገኛት አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጉትን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነቱን አሳ::

 አለም አቀፍ የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን በየአመቱ በመላው አለም በተለያዩ አህጉራት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርይታወቃል:: ይህ መከበር ከጀመረ ከመቶ ሃያ አመት በላይ የሆነው የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን ዘንድሮም ሜይ 1 ቀን2014 (ሚያዚያ 23 ቀን 2006 . ) በተለያዩ አህጉራት ተከብሮል::

በዛሬውም ቀን ሜይ 1 ቀን 2014 በኦስሎና በኖርዌይ በተለያዩ ከተሞች በደማቃ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የተለያዩ  የፖለቲካድርጅቶች፣  በሰብአዊ መብትድርጅቶች፣  ሌሎችም ድርጅቶች እንዲሁም በኖርዊይ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት  ማህበረሰብክፍሎች (community) የየሀገራቸውን ባንዲራ እና የየድርጅታቸውን አርማ በመያዝ የሰራተኛውን መብት መከበርየሚጠይቁና ሌሎችንም የተለያዩ መፈክሮችን፣ አርማዎችን መያዝ  በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል::


 በኦስሎ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች የድጋፍ ድርጅቱለአባሎቹ ባደረገላቸው የሰልፍ ጥሪ መሰረት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዚሁ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዊ መብትእረገጣ የተቃወሙ ሲሆን ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውንም ድጋፍ አሳይተዋል:: በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስትበኢትዮጵያሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የሰበሃዊ መብት እረገጣ ፣አፈና፣ እስራትና ግድያ በመቃወም አንድነት ለዴሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ (አንድነትእና ሰማያዊ ፓርቲ ሰለማዊ ትግል እያደረጉ እንዳለና በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስትእየተፋለሙት እንደሆነ ይታወቃል::

 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎችና አመራሮች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማትለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውን የድጋፍ አጋርነታቸውን በማሳየት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል:
:  
 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar