ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በግፍ ሕይወታቸው ባጡ ዜጎች መርዶ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጭት ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል። ህወሓት እና አጋፋሪው ኦህዴድ በነዙት ሽብር ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ፣ የተደበደባችሁ እና ለእስር የተዳረጋችሁ ወገኖቻችንም ህመማችሁም እስራችሁም የሁላችንም ነው። መላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ከእናንተ ጋር ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ተደብድቧል፣ ተግዟል፣ ታስሯል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ግንቦት 7 ደጋግሞ ያስገነዝባል።
በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ ያልተበደለ የኢትዮጵያ ክፍል የለም። የወያኔ አጋፋሪ የሆነው አህዴድ የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ሕፃናትንና አዛውንትን ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ፣ ሌላው አጋፋሪ ብአዴን ደግሞ በጎንደርና አካባቢው ተመሳሳይ ጭፍጨፋዎችን አካሂዷል። ወያኔ ከፋሺስት ኢጣልያ ወርሶ ለሃያ ዓመታት በትጋት ያራመደው “የከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ ምርት እነሆ ዛሬ በዓይኖቻችን እያየን ነው። ፋሽስት ጣልያን ጀምሮት የነበረውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ስትራቴጄ ለማጠናቀቅ ህወሓት በጥድፊያ ላይ ነው። ይህን እኩይ ዓላማ ማስቆም የሁላችን ኃላፊነት ነው።
የመከላከያ ሠራዊት እና የፊደራል ፓሊስና አባላት ሆይ፣ ለዘረኛው ወያኔ መሣሪያ ሆናችሁ ወገናችሁን አትፍጁ! እናንተ የምታገለግሉት ሥርዓት፣ ከእናንተ መካከል ኦሮሞ ያልሆኑት እየመረጠ ኦሮሞዎች ወገኖቻችንን እንዲገሉ፣ አማራ ያልሆኑት ተመርጠው አማሮችን እንዲገሉ የሚልክ መሠሪ መሆኑን የምታውቁት ነው። ወኔን አንዳችንን በሌላችችን ላይ እያዘመተ እርስ በርስ ሊያፋጀን ቆርጦ መነሳቱን አስተውሉ። ይህን እኩይ ዓላማ የማክሸፍ ሥራ የናንተም ኃላፊነት እንደሆነ ግንቦት 7 ያስገነዝባል።
በወያኔ የስለላ መዋቅር ውስጥ ያላችሁ ህሊና ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን የምትሠሩት ሥራ አገራችን ወደየት ሊወስዳት እንደሚችል ቆም ብላችሁ አስተውሉ። እናንተ ዛሬ የምትወስዱት ቆራጥ እርምጃ የበርካታ ሕዝብ ሕይወት ሊታደርግ ይችላል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተከፋፍላችሁው ወያኔን መቃወም የትም አያደርስም። በኦሮሞው መገደል አማራው፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ጉራጌው ካላመመው፤ አማራው ሲበደል ኦሮሞውና ሌላው እንዲያመው እንዴት መጠበቅ ይቻላል። እናንት ወጣቶች ከዘውግ ቆጠራ በላይ ሁኑ። ዛሬ የሚደረጉ ትናንሽ ነገሮች እንኳን የረዥም የወደፊት ውጤት እንዳላቸው ተገንዘቡ። የወደፊቱ ኢትዮጵያ የእናንተ ናት፤ የምትመኟችን ከራሷ ጋር የታረቀች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቅድሚያ እናንተ መታረቅ ይኖርባችኋል። የሁላችንም ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ነው ትኩረታችሁን እሱ ላይ አድርጉ።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!!!! አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በወያኔ ዘረኛ ፕሮፖጋንዳ ተጠልፈው ንግግራቸው ሰው ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያቃቅሩ ሰዎችን አትስማ። የመረረ፣ የሚያስቆጣ ንግግር እንኳን ቢናገሩ ንቀህ ተዋቸው። በወያኔ ውስጥም ሆነ ከወያኔ ውጭ ሆነው ብሔርና ዘርን እያነሱ ተማረው ማስመረር የሚሹ ሁሉ ግባቸው አንድ ነው። በየትናቸው ወገን ቢሆኑ እነሱ የጥፋት ኃይሎች ናቸው፤ እነሱ የኢትዮጵያና የሕዝቧ ጠላት የሆነው የህወሓት መጠቀሚያ ናቸው።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ህወሓት እና ህወሓት የዘረጋው ሥርዓት ነው። የጋራ ትኩረታችን በጋራ ጠላታችን ላይ ብቻ ይሁን። ወያኔ ትኩረታችን ለመበተን ብዙ ነገሮችን ይጀምር ይሆናል፤ ርስ በራሳችን ከማባላትም አልፎ ጎረቤቶቻችንን መጎነታተል ይጀምር ይሆናል። በእንዲህ ዓይነት ድርጊት ትኩረታችን መበተን ፈጽሞ የለበት።
እኛ ኅብረታችንን ስናጠናክር የተዳከመው ወያኔ ይበልጥ ይዳከማል። ሊበታትኑን የዳከሩትን አሳፍረን ኅብረታችን እናጠነክራለን። ይህ ደግሞ የወያኔ ውድቀት እና የኢትዮጵያ ትንሣኤን ያፋጥናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar