የስላማዊ ስልፉ አላማ በሁለት ዋና ምክንያትቶች ሲሆን የመጀመሪያ ረዳት ፓይለት ሐ/መድህን አበራ ለሲውዘርላንድ መንግስት ያቀረበውን የጥገኝነት ጥያቄ በመደገፍ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ተገኝቷል በሰልፉ የተለያዩ መፍክሮችን በማስማት አንደዚሁም በዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ተወካይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለአምባስደሩ በእጃችው በማስረከብ በኢንባሲው የተደረገው ዝግጅት በኖርዌ ሰዓት አቆጣጠር 12;00 ሰዓት ተጀምሮ በ13;00 ሰአት ተጠናቆል;;
በመቀጠል ወደ ኖርዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ በመሄድ የወያኔ መንግስት ለሱዳን በሚስጥር አሳልፎ የኢትዮጵያን መሬት ለመስጠት ያደረገውን ህገወጥ ውል በመቃወም የድሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ተወካይ ንግግር ካደረጉ በሗላ ተጋባዥ እንግዶችም በየተራ ተቃውሞዋቸውን በንግግር ያሰሙ ሲሆን የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችም አሰምተዋል በመጨረሻም ለውጭ ጉዳይ ሚኒሥተር የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በመስትጠት ዝግጅቱ በታሰበው ሰዓት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆል፥
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar