onsdag 4. september 2013

ወያኔ የሚገነፍል ድስት ነዉ

ኤፍሬም ማዴቦ 
ስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ
ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . . ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ
እየከፈትኩ አብዳለሁ። አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ
እየከፈትኩ አብዳለሁ። ምን ላድርግ ተሰድጄ ልበድ እንጂ በወያኔዋ ኢትዮጵያማ እነ በረከት ካልፈቀዱ ማበድም አይቻልምኮ! አደራ
እንግዲህ እንደኔ ጠንካራ ቆዳ የሌላችሁና በትንሹም በትልቁም እየተበሳጫችሁ ዕቃ የምትወረዉሩ ሰዎች ኢቲቪን ከመክፈታችሁ በፊት
ባንካችሁ ዉስጥ ቴሌቪዥን መግዢያ ትርፍ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጡ፤ አለዚያ እዉነትም ማበዳችሁ ነዉ።
ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የወያኔን ፀባይ በተከታታይ እንዳየሁት የወያኔ ፀባይ ከበቅሎ፤ ከድስት ወይም ከሁለቱም ጋር ተመሳስሎብኛል።
በቅሎ የታሰረችበትን ገመድ በጠሰች ቢሉት “በራሷ አሳጠረች” ብሎ መለሰ አሉ የበቅሎዋ ጌታ። በቅሎ መታሰሪያዋን በበጠሰች ቁጥር
የምትጎዳዉ እራሷን ነዉ፤ ግን በቅሎ በጭራሽ ከስህተቷ አትማርምና ሁሌም ገመዷን እንደበጠሰች ነዉ። አምባገነኑ ወያኔም እንደዚሁ
ነዉ። ድስት ሁሉም ባይሆንም አንዳንዱ በጣዱት ቁጥር ይገነፍላል፤ የሚገነፍል ድስት ደግሞ የሚያበላሸዉ እራሱን ነዉ። ወያኔ ድስትም
በቅሎም የሚሆነዉ ዕድሜዉን ለማራዘም ነዉ፤ ሆኖም ሲገነፍልም ሆነ ገመዱን ሲበጥስ እድሜዉ ያጥራል እንጂ አይረዝምም።
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሐይማኖቶች ጉባኤ ይካሄዳል ሲባል ሰምቼ ባለፉት ሁለት አመታት ካልጠፋ ነገር አገራችን የምትታመሰዉ
በሐይማኖት ጉዳዮች ነዉና እስኪ ዜናዉን ከምንጩ ልስማ ብዬ ኢቲቪ ላይ አፈጠጥኩ። መቼም ኢቲቪ በብዙ ነገሮች ሊያበሳጫችሁ
ይችላል ግን ዛቻ፤ ዉሸትና፤ ዘራፊ ባለስልጣኖች ሲሞገሱ መስማት ከፈለጋችሁ ግን ሌላ ዬትም ቦታ መሄድ አያስፈልጋችሁም በዚህ ኢቲቪ
የልባችሁን ያደርስላችኋል።
ወያኔ ስልጣን ይዞ በቆየባቸዉ አመታት ሁሉ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ ጨንቋት ያላማጠችበትና ግራ ግብቷት ድረሱልኝ ያላለችበት አንድም
ግዜ የለም። ወያኔ ባለፉት ሃያ አመታት ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ለማድረግ ያልቆፈረዉ ጉድጓድና ያልሸረበዉ ደባ
ባይኖርም ባለፉት ሁለት አመታት ይዞብን የመጣዉ ሸርና ተንኮል ግን የክርስቲያኑንና የሙስሊሙን ማህብረሰብ የአንድ ሺ አራት መቶ
አመታት በሰላም አብሮ የመኖር ባህል የሚያደፈርስና አገራችንን አስከፊ የሐይማኖቶች ግጭት ዉስጥ የሚከት አደገኛ ሴራ ነዉ።
ለወትሮዉ ፖለቲካዉን በዘር፤በቋንቋና በክልል ቋጥሮ ማዶ ለማዶ የለያየን ወያኔ ዘንድሮማ ጭራሽ የፓርቲ አባልነታችንን ብቻ ሳይሆን
የምናመልክበትን የእምነት ቦታና አለም በቃኝ ብለን የምንመንንበትን ገዳም ጭምር አኔ ነኝ መርጬ የማድላችሁ ማለት ጀምሯል።
በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጳጳስ አዉርዶ ጳጳስ ሾሞባቸዋል፤ የወንጌላዉያን ቤ/ክርሲቲያኖችን ፓስተር አንዴ አስታራቂ አንዴ
አማላጅ እያደረገ ቤ/መንግሰትና ቃሊቲ መሃል ተላላኪ አድርጎታል፤አሁን በቅርቡ ደግሞ ፊቱን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በማዞር የራሱን
መጅሊስ ሾሞባቸዋል።
ወያኔ ጥንታዊቷን የኦርቶዶክስ ቤ/ክርሰቲያናችንን የአገር ዉስጥና የአገር ዉጭ ሲኖዶስ በሚል በመከፋፈል ወንጌላዉያኑን አብያተ
ክርስቲያናት ደግሞ እኔ ነኝ የማምለክ ነጻነት የሰጠኋችሁ እያለ በማስፈራራት የክርስቲያኑን ህብረተሰብ ለግዜዉም ቢሆን ጭጭ አሰኝቶ
እንዳሰኘዉ መቆጣጠር ችሏል። በድርጅታዊ ጥንካሬዉ፤ በምዕመኑ መካከል በገነባቸዉ የግንኙነት መስመሮችና በእምነት ቀናኢነቱ
ከክርስቲያኑ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን የወያኔን ፈላጭ ቆራጭነት አልቀበልም ብሎ ወያኔንና
ዘረኝነቱን ፊለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል። ሰለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ሐይማኖቴን አትንካብኝ በሚለዉ በሙስሊሙ ህብረተሰብና
አጎንብሰህ ተገዛ በሚለዉ ወያኔ መካከል በተፈጠረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመታመስ ላይ ትገኛለች። እኔም ሞኝ ይመስል ኢቲቪ ላይ
ያፈጠጥኩት ይካሄዳል የተባለዉ የሐይማኖት ጉባኤ ይህንን አገራችን ላይ የተደቀነዉን አደጋ ተመልክቶ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ብዬ
ነበር። ግን የወያኔ ነገር ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነዉና የሐይማኖት ጉባኤ ተብሎ የቀረበዉ ጉድ እንደ አኬልዳማና ጂሃዳዊ ሐረካት ሆን ተብሎ
ህዝብን ለማደናገር የተሰራ ድራማ ነዉ እንጂ በችግሮች ላይ ተወያይቶ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ጉባኤ አይደለም። በአኬልዳማ ድራማና
ሰሞኑን በተካሄደዉ የሐይማኖቶች ጉባኤ መካከል ልዩነት ቢኖር አንዱ የቴሌቪዥን ድራማ ሌላዉ ደግሞ የመድረክ ላይ ድራማ መሆናቸዉ
ብቻ ነዉ።
በዚህ የሐይማኖቶች ጉባኤ ተብዬዉ የአዳራሽ ውስጥ ድራማ ላይ የተገኙት አብዛኛዎቹ ተዋንያን የዚያ “የድንጋይ ማምረቻ” ተቋም
ዉጤቶች የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች፤ የወያኔ ባለስልጣኖችና ኤሳዉ ታላቅነቱን ለምግብ እንደሸጠ የሐይማኖት አባትነታቸዉን ለጥቅም የሸጡ
ካህናት ለመሆናቸዉ ምስክር የሚያሻ አይመስለኝም፤ ቴሌቪዥኑ መስኮት ዉስጥ አንደተከበበ አዉሬ የሚቁለጨለጨዉ አይናቸዉ ምስክር
ነዉ። ድራማዉን በኢቲቪ ስመለከት ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ የወያኔ ባለስልጣኖች እንዳሰኛቸዉ እንደሚናገሩ ስለማዉቅ
እነሱ ተናገሩም አልተናሩ ከነሱ ብዙም የምጠብቀዉ ነገር አልነበርም። ይልቁን ጉባኤዉን ስከታተል እጅግ በጣም የገረመኝና የራሴኑ ጆሮ
ማመን ያቃተኝ አንድ በሰማይም በምድርም ተጠያቂነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባትና በዋሸ ቁጥር ኩራት የሚሰማዉ በረከት ስምኦን

ያደረጉት እንደ ብርሀንና ጨለማ የተቃረነ ንግግር ነዉ። መቼም እርግጠኛ ነኝ የበረከትንና የአባዉን ፊት ሳያይ ንግግራቸዉን ብቻ
ያዳመጠ ሰዉ የቱ ነዉ በረከት የትኛዉ ናቸዉ የሀይማኖት አበት ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ለሁሉም እኚያ የሐይማኖት አባትና በረከት
እንዲህ ነበር ያሉት፤

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar