lørdag 1. juni 2013

የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንቁም አለ

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያዊ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) “በሀገር ቤት በመጭው አሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) በሙሉ ልብ ይደግፋል። በዚህም ጸረ ወያኔ ህዝባዊ ተቃውሞ በሀገር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ አንዲሳተፉ ጥሪያችንን አናሥተላልፋለን።” ሲል በበተነው መግለጫ አስታወቀ።
“ኢሕአፓ ወከንድ ለአምባገነንነት መወገድና ለሕዝብ መብት መከበር በአመቺው መንገድ ሁሉ ከመደራጀት ባሻገር በድርጅት አጥር ታስሮ ከመቀመጥ ይልቅ ትከሻ ለትከሽ ተደጋግፎ የህዝብን የነቃ ተሳትፎ ለማረጋገጥ መስራት እንደሚያሻ ለአፍታም አይጠራጠርም።” ያለው ወክንድ “የኢትዮጵያ የመከራ ዘመን ሊያጥር የሚችለው በጥቂት ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ሳይሆን አምርረው ፀረ ወያኔውን ትግል በጋራ በመታገል መሆኑን ኢሕአፓ ወክንድ አጥብቆ ያምናል።” ብሏል።
ወክንድ በጋዜጣዊ መግለጫው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፈው ጥሪ “ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጋራ ሀገራችን በጋራ እንቁም በሕዝብ የነቃ ተሳታፊነት አምባገነንነት ተወግዶ ሕዝብ ወሳኝ የሚሆንበት ሥርዓት እውን ይሆን ዘንድ በእሁዱ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንቁም::” ብሏል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=3818

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar