onsdag 29. mai 2013

“ኢትዮጵያ የሻለቃ ጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብላ አታውቅም፤ ልትቀበልም አይገባትም” – አቶ አገኘሁ መኮንን (የታሪክ ባለሙያ

ኢትዮጵያ ዛሬ የያዘችውን ቅርጿንና ስፋቷን ከመያዟ በፊት ጥንታዊ ግዛቷ እንደ ንጉሥ ኢዛናና ካሌብን የመሳሰሉ ጠንካራ ነግሥታት በነበሯት ጊዜ የት ድረስ ይደርስ እንደነበረና ደካማ
መሪዎች በነበሯት ጊዜ ደግሞ ምን ያህል ይሸበሸብ እንደነበር በማስረጃ አስደግፈው በማቅረብ የንግግራቸው መንደርደሪያ አደርገውታል። በማከልም ግብጽ ዘላለማዊ ህልሟን ማለትም አባይን ከምንጩና ቤኒ ሻንጉል አካባቢ አለ የሚባለውን የወርቅ ማዕድን ለመቆጠጠር ስትል ታደርግ በነበረው ተደጋጋሚ ሙከራና በኋላም በድርቡሾች የበቀል ወረራ የሰሜንና የሰሜን ምዕራቡ ድንበራችን ምን ያህል በተደጋጋሚ ይታወክ እንደነበር አብራርተዋል።
(ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል
ኢትዮጵያ የሻለቃ ጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብላ አታውቅም፤ ልትቀበልም
አይገባትም” - አቶ አገኘሁ መኮንን (የታሪክ ባለሙያ)
(ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል)
“ኢትዮጵያ የሻለቃ ጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብላ
አታውቅም፤ ልትቀበልም አይገባትም” ሲሉ አቶ አገኘሁ መኮንን
የተባሉ የታሪክ ባለሙያ በቅርቡ ሲልቨር ስፕሪንግ (ሜሪላንድ) 
በተደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሜቴ ጉባኤ ላይ ገለጹ።
አቶ አገኘሁ መኮንን በጥልቀት ያጠኑትንና በ7 ምዕራፎች
የተከፈለውን ጥናታቸውን ለጉባኤው አባላት ግንቦት 10 እና 11 
2005 ዓ.ም. ያቀረቡት ላለፉት ዐራት ዓመታት ያለመታከት
ባሰባሰቧቸው የሰነድና የካርታ ማስረጃዎች በማስደገፍ ነበር።
ኢትዮጵያ ዛሬ የያዘችውን ቅርጿንና ስፋቷን ከመያዟ በፊት
ጥንታዊ ግዛቷ እንደ ንጉሥ ኢዛናና ካሌብን የመሳሰሉ ጠንካራ
ነግሥታት በነበሯት ጊዜ የት ድረስ ይደርስ እንደነበረና ደካማ
መሪዎች በነበሯት ጊዜ ደግሞ ምን ያህል ይሸበሸብ እንደነበር በማስረጃ አስደግፈው በማቅረብ የንግግራቸው መንደርደሪያ
አደርገውታል። በማከልም ግብጽ ዘላለማዊ ህልሟን ማለትም አባይን ከምንጩና ቤኒ ሻንጉል አካባቢ አለ የሚባለውን የወርቅ
ማዕድን ለመቆጠጠር ስትል ታደርግ በነበረው ተደጋጋሚ ሙከራና በኋላም በድርቡሾች የበቀል ወረራ የሰሜንና የሰሜን ምዕራቡ
ድንበራችን ምን ያህል በተደጋጋሚ ይታወክ እንደነበር አብራርተዋል።
ያኔ ሱዳንን በቅኝ ገዥነት ትገዛ ከነበረችው ከእንግሊዝ ጋር በ1902 (እ.አ.አ.) አፄ ምኒልክ ውል ከመፈራረማቸው በፊት
የኢትዮጵያ ግዛት የት - የቱን ያጠቃልል እንደነበርና ዛሬ ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋት ምን ያክል የበለጠ እንደነበር አፄ ምኒልክ
በ1891 (እ.አ.አ.) አሠርተው ድንበሬን እወቁልኝ በማለት ለዓለም መንግሥታት በትነውት የነበረውን ካርታ በማቅረብ
አስረድተዋል።
አቶ አገኘሁ በመቀጠልም እንግሊዞች በምን ሁኔታ የግብጽ የሞግዚት አስተዳዳሪ ለመሆን እንደበቁና ከዚያም ተነስተው ያኔ በግብጽ
ሥር የነበረችውን ሱዳንን በመቆጣጠር የግብጽን ህልም ዕውን ለማድረግ እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እየቀረቡ እንደመጡና የ1902ቱን
(እ.አ.አ.) የድንበር ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር እንዴትና በመን ሁኔታ ለመፈራረም እንደበቁ በዝርዝርና በሚመስጥ ሁኔታ
አቅርበዋል። በዚህ ጥልቅና ዝርዝር ገለፃቸው አቶ አገኘሁ በ1902 እንግሊዞች ከአፄ ምኒልክ ጋር ውል ከመፈራረማቸው በፊትም
ሆነ ከተፈራረሙ በኋላ የኢትዮጵያን የግዛት ክልል በአምስት የተለያዩ ጊዜያት (ሁኔታዎች) ወደ ምሥራቅ እየገፉ ከኢትዮጵያ
ከፍተኛ መሬት ያለአግባብ ወስደዋል ይላሉ። እነዚህንም ሁኔታዎች ሲዘረዝሩ፦
1. ምንም እንኳን ተኩስ ክፍተውና በጦርነት አሸንፈውም ባይሆን የኢትዮጵያ ሠራዊት የዟቸውና ሰንደቅ ዓላማችን
ይውለበለብባቸው የነበሩትን ቦታዎች የኢትዮጵያን ባለይዞታነት ባለማክበር እየሄዱ ከኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ አጠገብ
የእነርሱን ሠንደቅ ዓላማ በመስቀልና ዙሪያ ከበባ በማድረግ፣
2. ሻለቃ ጉዊንና ሻለቃ ኦስቲን ሠርቬይ በሚሠሩበት ወቅት አፄ ምኒልክና ሐሪንግተን ቅድመ ፊርማ አድርገውት የነበረውን
ስምምነት ከእንግሊዝ ጥቅም አኳያ በማየት ኢትዮጵያን እየጎዱ ለእንግሊዝ በሚጠቅም ሁኔታ ካርታውን ነደፈዋል። እዚህ
ላይ ሮን አደለር የተባሉ የድንበር ክለላ ባለሙያን ዋቢ በማድረግ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሲሰጡ አቶ አገኘሁ እንዲህ ይላሉ፦
“ምንም እንኳን አንድን የድንበር ውል የሚዋዋሉትና በፊርማቸው የሚያፀድቁት ፖለቲከኞች ቢሆኑም፣ ፖለቲከኞቹ
ራሳቸው የሚወስኑበትን ዋናውንና ወሳኙን ሰነድ ማለትም ካርታውን የሚያቀርቡላቸው የመስክ ሥራውን የሚሠሩት
እንጅነሮች ናቸው። ይህንን ስናይ ታዲያ በእንደዚህ ያለው ወሳኝ ሥራ ላይ የተሳተፈ አንድም ኢትዮጵያዊ የለም። ከሱዳን
ቅኝ ገዥና ከአንድ ወገን በመጡት ሁለት የእንግሊዝ መኮንኖች ለእንግሊዝ በሚጠቅም ሁኔታ በተሠራ ካርታ ላይ ነው
አፄ ምኒልክ እንዲፈርሙ የተገደዱት።” ሌላም መታወቅ ያለበት ነግር ይላሉ አቶ አገኘሁ እንግሊዞች ድርቡሾችን ሱዳን
ውስጥ ካሸነፉ በኋላና ደቡብ አፍርካ ውስጥ ትራንስ ቨአል ውስጥ የነፃ ናታል ንቅናቄን (Free Natal Movement) 
ከመቱ በኋላ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ኢትዮጵያ ላይ በማሳረፍ ምንሊክ እነርሱ ያሏቸውን ተቀብለው ካልፈረሙ ሊመቱ
እንደሚችሉ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች በአማራጭ እቅድነት ይዘው ሃሳቡን ከወዲያ ወዲህ ሲያንሸራሽሩት እንደነበር
በአፅንዖት ገልፀዋል። በመሆኑም አፄ ምኒልክ ጉልበተኛ እየሆነችና “ሰጥቶ መቀበል” የሚለውን የድንበር ድርድር መርህ
አቶ አገኘሁ መኮንን (በስተግራ) እና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በጉባኤው
ወቅት (ፎቶ - ኢትዮሚድያ) ተከትላ ሳይሆን የኢትዮጵያን መሬት ለመንጠቅ ዓልማና አስባ የመጣቸውን የእንግሊዝን ቃል አክበረው ባይፈራረሙ ኖሮ
ነፃ የነበረቸው ኢትዮጵያ ነፃ ሆኖ የመቀጠሏ ሁኔታ እየመነመነ መጥቶ እንደነበር ስለታያቸው ነበር እየጎመዘዛቸውም
ቢሆን የፈረሙት።
3. የሠርቬዩ ሥራ ካለቀና አፄ ምኒልክና ኮሎኔል ሐሪንግተን አጠቃላይ ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ካይሮ፣ ሱዳን፣ ኬንያና
ኡጋንዳ የነበሩ የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎችና ዌስት ሚኒስቴር የሚገኙ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣናት ከሚገዟቸው የቅኝ
ግዛት ክልሎች ጥቅም አኳያ በመመርመር ኢትዮጵያን ጎድቶ እንግሊዝን በሚጠቅም ሁኔታ ብዙ መሻሻያዎችን
አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የአፄ ምኒልክንና የሐሪንግተንን ቅድመ ፊርማ ስምምነት ከ1891፣ 1894 እና
1901 የሚስጠር ስምምነታቸው ውል አኳያ በመገምገም ኢትዮጵያን እየጎዱ የቅድመ - ፊርማውን ስምምነት በራሳቸው
ስልጣን አሻሽለውታል። ውሉ እ.አ.አ. ግንቦት 15 ቀን 1902 ከተፈረመም በኋላ በጣሊያን ጥያቄና ጣሊያንን
ለመጥቀም ሲባል ድንበሩ ሰቲት አካባቢ ወደ ምዕራብ ፈቀቅ እንዲል ሲስማሙ ይህ ግን ለምኒልክ እንዳይነገርና
በተፈረመበት የውል ሰነድ ላይም ይህ መሻሻል እንዳይታረም ተስማምተዋል።
4. ለአራተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ መሬቷን በግፍ የተዘረፈችው ይላሉ አቶ አገኘሁ ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን በ1903 (እ.አ.አ) 
በከለለበት ጊዜ ነበር። ከላይ እንዳየነው ጣሊያንን ለመጥቀም ሲባል እንግሊዝና ጣሊያን በሚስጥር ተስማምተው ሰቲት
አካባቢ ድንበሩ ከሰቲትና የኦም ሀገር ወንዞች ከሚገናኙበት መጀመሩ ቀርቶ የሰቲትና የራውያን ወንዞች ወደ እሚገናኙበት
ወደምዕራብ ትንሽ ፈቀቅ እንዲል ተደርጎ ነበር። ይሁን እንጅ እንግሊዞች ለጣሊያን ጥቅም ሲሉ ሰቲት አካባቢ ኢትዮጵያን
መርፌ አውጠው መተማ አካባቢ ማረሻ አስወልደዋታል ይላሉ አቶ አገኘሁ። በመቀጥልም አቶ አገኘሁ ሲያብራሩ ምንም
እንኳን ኢትዮጵያ ስለሰቲቱ መሻሻል ምንም እንዳታውቅ በሚስጥር ቢያዝና ለጣሊያን ጥቅም ተብሎ የተደረገ ቢሆንም
መተማ አካባቢ ከመድረሱ በፊት ሰቲት አካባቢ ላገኘችው መሬት ምትክ ሻለቃ ጉዊን በስልጣኑ ተመጣጣኝ የሆነ መሬት
ለሱዳን መስጠቱን የጉዊንን ችካል የሚያሳየውን ካርታ በማሳየት አቶ አገኘሁ የገለፁ ሲሆን፣ ከዚያ ወረድ ብሎ ከመተማ
በስተደቡብ በኩል ግን ራሱ ሻለቃ ጉዊን “ከተሰጠኝ ስልጣን አልፌ በመሄድ የውሉን መሥመር ቄይሬ ለሱዳን ከፍተኛ
መሬት ሰጥቻለሁ” ያለበትን ሠነድ በመጥቀስና ምን ያህል መሬት ሻለቃ ጉዊን ከእትዮጵያ ዘርፎ ለሱዳን እንደሰጠ
የጉዊንን የከለላ ካርታ ለጉባኤው አባላት በማሳየት የጉዊንን ዓይን ያወጣ ዘረፋ አጋልጠዋል።
አቶ አገኘሁ ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሄዶ የሠራውን ሌላውን ግፍ ሲገልፁ የንዴት ሳግ እየተናነቃቸው
እንዲህ ነበር ያሉት፦ “በተፈረመበት ካርታ ላይ ድንበሩ ቤኒ ሻንጉል ውስጥ በጀሮክ ተራራ አናት ላይ ማለፍ ነበረበት።
ይህ የጀሮክ ተራራ ደግሞ አሶሳ ውስጥ ከነበሩት የጎሣ መሪዎች ውስጥ አንዱ የነበሩት የኢብራሒም ዋድ ሞሐመድ ዋና
ከተማ ነበር። ኢብራሒም ዋድ ሞሐመድ ፍፁም ኢትዮጵያዊነቱን በመግለፁ፣ ግን ድንበር እያለፈ የፋዙሊን መንደሮች
ይወርራል የሚል ሰበብ ተለጥፎለት የሱዳን መንግሥት በሥሩ አድርጎ እንዲቆጣጠረው ሲል ሻለቃ ጉዊን ስምምነቱን ጥሶ
ጀሮክ ተራራን አልፎ ሦስት ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ይከልለዋል። ይህንን ግፍ መቀበል ያቃተው ጀግናው
ኢብራሂም ያምፃል። ከተላከበት ሥራ እጅግ በመውጣት ድንበር ከላዩ ሻለቃ ጉዊን ተዋጊ ሆኖት አረፈና ከካርቱም ጦር
አስመጥቶ ኢብራሂምን እንዲወጉት ትዕዛዝ ይሰጣል። ኢብራሂምም በጀግነነት ከተዋጋ በኋላ በመሸነፉና በመያዙ ካርቱም
አስወስዶ እንዳሰቀለው ጆርናል ኦፍ አፍሪካን ሶሳይቲ በተባለ ጆረናል ላይ በ1937 በጻፈው መጣጥፍ ሳያፍር ገልጿል።” 
ከዚህም አልፎ ኢታንግ አካባቢ አሁንም “ከስልጣኔ አልፌ ምሥመሩን ቀይሬያለሁ” ብሎ ሻለቃ ጉዊን ራሱ በራሱ ላይ
እንደመሰከረ አቶ አገኘሁ አጋልጠዋል።
5. ከ9ነኛው ዲግሪ ላቲቲዩድ ሰሜን አንስቶ እስከ 10ኛው ዲግሪ ላቲቲዩድ ሰሜን ድረስ ሻለቃ ጉዊን መጠነኛ መሬት
ለኢትዮጵያ ሰጥቶ ነበር። ግፍ የማይፈሩት እንግሊዞች ግን በወታደራዊ የደህንነት ክፍላቸው አማካኝነት የጉዊንን ችካል
ብቻ ሳይሆን የስምምነቱንም መሥመር እጅግ ወደ መሥራቅ አልፈው በመግባት እንዳሠመሩት አቶ አገኘሁ በካርታ ላይ
አስደገፈው አቅርበዋል።
ይህንን በዚህ መልኩ ከስምምነቱ ውጭ የተከለለውን ወሰን የሚያሳይ ሌላ ካርታ በመሳል እንግሊዞች በላዩ ላይ በመፈረም አፄ
ምኒልክ ማኅተማቸውን እንዲያሳርፉበት ልከውላቸው እንደነበርና አፄ ምኒልክ ግን ከስምምነታቸው ውጭ በመከለሉ
ማኅተማቸውን ሳያስቀምጡበት እንደቀሩ አሁንም በካርታ አስደግፈው ገለፃ አድርገዋል። ያም ማለት “ሁለት ሀገራት የተስማሙበት
የድንበር ውል በአንዱ ከተጣሰ ሌላው ሀገር ከውሉ የመውጣት መብት እንዳለው የዓለም አቀፍ ሕግ ይደነግጋል። በልማዳዊ ሕግም
(Common Law) ቢሆን ሁለት ተዋዋዮች ከተዋዋሉ በኋላ አንዱ ውሉን ቢያፈርሰው ሌላኛው የማክበር ግዴታ የለበትም። አፄ
ምኒልክም ፈርመውበት የነበረውን የድንበር ስምምነት (ምንም እንኳን ተገድደው ቢሆንም) እንግሊዞች ደግመው ደጋግመው
ስላፈረሱት አፄ ምኒልክ የተከለለውን ድንበር የሚያሳየው ካርታ ላይ መኅተማቸውን ለማሳረፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህም
መሠረት ይላሉ አቶ አገኘሁ ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ብንሄድ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ የሚጠይቀው የመጀመሪያ ጥያቄ
የተስማማችሁበትን ሰነድ አምጡ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከስምምነቱ ተለወጠ የምትሉት ምኑ ነው? የሚል ነው።
የስምምነቱ ካርታና የክለላው ካርታ ምን ያክል እንደሚለያዩና ልዩነቱንም ያመጣቸው እንግሊዝ መሆኗን ኢትዮጵያ ከበቂ በላይ
በሆነ ሁኔታ ማስረዳት ስለምትችል ድሉ ያለጥርጥር የኢትዮጵያ ይሆናል። ባለመታደል ግን ይህንን ከሥራ ላይ የሚያውልናለኢትዮጵያ ጥቅም የቆመ መንግሥት ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማጥፋት የቆመ መንግሥት ስለሆነ ስልጣን ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ
መንግሥት ስልጣን ላይ እስከሚወጣ መጠበቅ ግዴታ ይሆንብናል” ይላሉ አቶ አገኘሁ።
አዎ! የአቶ አገኘሁ ገለፃ የማይጠገብ ነበር። የተሰጣቸው ሁለት ሰዓት መገባደዱ ሲነገራቸው ተደናገጡ። ምክንያቱም ገና ወደ አዲሱ
ግኝታቸውና ምዕራፍ ስድስት አልገቡምና። በመሆኑም አስፈቅደው ትንሽ ጊዜ በማስጨመር ወደ ስድስተኛው ምዕራፍ ማለትም
“ዕውን የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብሏል?” ወደሚለው ርዕሣቸው በፍጥነት ገቡ።
ምንም እንኳን ከላይ እንዳየነው እንግሊዝ ውሉን ብታፈርሰውም የወያኔ መንግሥት “የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከሱዳን
መንግሥት ጋር በሀምሌ 18 ቀን 1972 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) ባደረገው የደብዳቤ ልውውጥ የጉዊንን የወሰን መሥመር ተቀብሏልና
እኔም እቀበላለሁ” በማለት ከፍተኛና ለም መሬታችን በሚስጥር በመዋዋል ለሱዳን ማስረከቡ ይታወሳል። አቶ አገኘሁ ግን እስከ
አሁን ድረስ በማንም በጥልቀት ያልታየውንና ትክክለኛ ግንዛቤ ያላገኘውን የ1972ቱን የደብዳቤ ልውውጥ በጥንቃቄ
በመመርመርና ወያኔ በተሳሳተ ወይም ኢትዮጵያን ከመጉዳት እኩይ ባህሪው በመነጨ ሥውር ተልዕኮው ምክንያት ሆን ብሎ አሳስቶ
የተረጎመውን ፉርሽ አድርገውታል።
አቶ አገኘሁ ይንን ርዕሥ ሲጀምሩ ያደረጉት የደብዳቤ ልውውጡን ወሳኝ አንቀጽ ማለትም አንቀጽ አንድን እስክሪን ላይ
በፕሮጀክተር በማሳየት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ እንድንተረጉም መላው የጉባኤ አባላትን ጋበዙን። ሁላችንም ይሆናል ያልነውን
ትርጉም ሰጠን። ቃል በቃል አንድ ባይሆንም ሁላችንም የሰጠነው ትርጉም ተመሳሳይነት ነበረው። ቀጠሉና ከሚኖሩበት ከለንደን
ጀምሮ ኢትዮጵያ ድረስ ያሰባሰቧቸውን ትርጉሞችና ወያኔ በሰነዱ ላይ የሰጠውን ትርጉምም ጨምረው ግን የትኛው ትርጉም የማን
እንደሆን ሳይገልጡ ሰሌዳው ላይ በፕሮጀክተር ደረደሩልንና የትኛው ትርጉም በይበልጥ ለአንቀፁ ትርጉም ይስማማል ብለው
ጠየቁን። በቁጥር አንድ ላይ ያስቀመጡት በፍፁም ለአንቀፁ እንደማይስማማና ተጣምሞ የተተረጎመ ነው አልናቸው በአንድ
ድምፅ። እርሳቸውም ሲመልሱ ያ የወያኔ ትርጉም ነው አሉን። ሌሎቹ እኛው ከሰጠናቸው ትርጉም የሚመሳሰሉና ተመሳሳይነት
ነበራቸው። አንደኛው ግን ከሁሉም ትርጉሞች የበለጠ ተመራጭነት ነበረው፤ በተለይም በታወቁት የሕግ ባለሙያ በፕሮፌሰር
አለም አንተም ተመረጠ። አቶ አገኘሁም ያ ትርጉም የራሳቸውም ምርጫ እንደሆነ ገልፀው ትርጉሙም አንድ የቋንቋና አንድ የሕግ
ባለሙያ ጓደኞቻቸው በአንድ ላይ ሆነው የተረጎሙት መሆኑን ገለፁ። ጉባኤውም ያንን ትርጉም ለዚያ አንቀጽ ኦፊሺያል ትርጉም
አድርጎ ወሰደ። በዚህ በኦፊሺያል በተቀበልነው ትርጉምም ሆነ ከወያኔ ትርጉም በስተቀር በሌሎቹ ትርጉሞች የአፄ ኃይለ ሥላሴ
መንግሥት በፍፁም የጉዊንን ክለላ እንዳልተቀበለ አቶ አገኘሁ በአፅንዖት አስረዱ። ወያኔ ግን አንድም በተሳሳተ ትርጉም
አለበለዚያም ኢትዮጵያን ከመጉዳት ባህሪው አኳያ “የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የጉዊንን የክለላ መሥመር ተቀብሎ ሊያስፈፀም
ሲል ተገለበጠ፣ ደርግም እንዲሁ ተቀብሎ ተግባራዊ ሊያደርግ ሲል ከስልጣን ተባረረ። በመሆኑም እኔ ተግባራዊ አደርጋለሁ” ብሎ
በሕገወጥነት የኢትዮጵያን ለም መሬት ለሱዳን አስረክቧል፤ በማስረከብም ላይ ነው በማለት አቶ አገኘሁ በቁጭት አስረድተዋል።
ወያኔ ሊለጥፍባቸው የሚሞክሩት ከእርሱ በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ መንግሥታት ግን ወያኔ እንደሚላቸው ሳይሆኑ እኛ
ኢትዮጵያውን ሳንሆን የወያኔ ወዳጅ በሆነው የሱዳን መንግሥት ሥር ያለው የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ኖቬምበር 19 2007
ያወጣውን ጽሑፍ መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፦ “The relations between Sudan and Ethiopia were 
empoisoned by the issues of border demarcations in the past. The government of the ruling 
EPRDF is the first Ethiopian government to be willing to talk with Sudan on the border issue.”
ሻለቃ ጉዊን በ1903 ድንበሩን ሲከልል ስምምነቱን በመጣሱ ምክንያት አፄ ምኒልክ ራሳቸው ክለላውን የሚያሳየው ካርታ ላይ
ማኅተማቸውን ባለማድረግ ውድቅ ያደረጉትን የ1902ቱን ስምምነትም ሆነ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በ1972 ያደረገው
የደብዳቤ ልውውጥ ሆን ተብሎ በተሳሳተና ኢትዮጵያን በሚጎዳ ሁኔታ በወያኔ ተተርጉሞ ለሱዳን የተሰጠው መሬት ሕገወጥ
መሆኑን ለጉባኤው ያስረዱበት የአቶ አገኘሁ ጥናት በጉባኤው አባላት በሙሉ ድምፅ ተቀባይነት አግኝቷል።
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.co

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar