onsdag 29. mai 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ፣ ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!

ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙና የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ለመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዚያት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ጥሪውን ከፍ ባለ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማሰማት በወሰነው መሰረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲሁም ግንቦት
Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞውን ለመግለጽ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚሁም መሰረት ዜጎች በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስት በሚፈፅማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አባላቶቻችን ላይ ወከባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጋፋት የተፈፀሙ ድርጊቶችን እንቃወማለን፤ የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 17 ቀን ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊደረግ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ሰልፉ የሚደረግ መሆኑን የማሳወቂያ ደብዳቤ ፓርቲው ቢያደርስም የቢሮው ኃላፊና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤአችንን አንቀበልም ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነቱን ሕገ ወጥ አሰራር በማውገዝ ሰልፉን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በመግለጫ ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡
በመጨረሻም የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ በአዋጁ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀንና ቦታ እንዲለወጥ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ሁለታችንም አካላት ባደረግነው ድርድር ሰልፉ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲሆንና የሰልፉ መነሻ ቦታ የፓርቲው ፅ/ቤት መድረሻ ቦታ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ወይም ጥቁር አንበሳ ዋናው ፖስታ ቤት ፊለፊት እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚሁም መሰረት፡-
1ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተጠቀሱት ጥያቄዎች እንደተጠበቁ መሆናቸውንና የግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን፣
2ኛ. ለረጅም ጊዜ ያለ ህግ ተነፍገን የቆየነውን ሃሳባችንን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብት በትግላችን ያረጋገጥን በመሆኑ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍበትና በሰልፉ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ማሳሰብ ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንድንወጣና ለሰልፉ መሳካት በምንችለው አቅም ሁሉ አስተዋፅኦ እንድናደርግ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑ፣
3ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ሰላማዊ ታቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና ዜጎች ላደረጋችሁልን ድጋፍ ፓርቲው ምስጋናውን ማቅረብ የሚፈልግ መሆኑንና የፓርቲያችንን ጥሪ ለህዝቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲዳረስ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋፅዖ እጅግ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን መሆኑን ፣
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Photo: ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙና የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ለመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዚያት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ጥሪውን ከፍ ባለ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማሰማት በወሰነው መሰረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲሁም ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞውን ለመግለጽ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚሁም መሰረት ዜጎች በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስት በሚፈፅማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አባላቶቻችን ላይ ወከባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጋፋት የተፈፀሙ ድርጊቶችን እንቃወማለን፤ የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 17 ቀን ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊደረግ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ሰልፉ የሚደረግ መሆኑን የማሳወቂያ ደብዳቤ ፓርቲው ቢያደርስም የቢሮው ኃላፊና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤአችንን አንቀበልም ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነቱን ሕገ ወጥ አሰራር በማውገዝ ሰልፉን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በመግለጫ ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡ በመጨረሻም የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ በአዋጁ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀንና ቦታ እንዲለወጥ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ሁለታችንም አካላት ባደረግነው ድርድር ሰልፉ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲሆንና የሰልፉ መነሻ ቦታ የፓርቲው ፅ/ቤት መድረሻ ቦታ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ወይም ጥቁር አንበሳ ዋናው ፖስታ ቤት ፊለፊት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በዚሁም መሰረት፡-
1ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተጠቀሱት ጥያቄዎች እንደተጠበቁ መሆናቸውንና የግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን፣
2ኛ. ለረጅም ጊዜ ያለ ህግ ተነፍገን የቆየነውን ሃሳባችንን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብት በትግላችን ያረጋገጥን በመሆኑ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍበትና በሰልፉ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ማሳሰብ ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንድንወጣና ለሰልፉ መሳካት በምንችለው አቅም ሁሉ አስተዋፅኦ እንድናደርግ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑ፣
3ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ሰላማዊ ታቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና ዜጎች ላደረጋችሁልን ድጋፍ ፓርቲው ምስጋናውን ማቅረብ የሚፈልግ መሆኑንና የፓርቲያችንን ጥሪ ለህዝቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲዳረስ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋፅዖ እጅግ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን መሆኑን ፣
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar