torsdag 23. mai 2013

(IMF) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ወደ 5 ነጥብ 5 እንደሚወርድ ተነበየ


በፀጋው መላኩ
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/05/IMF-LOGO-KNN.gifአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሰሞኑን የየሀገራቱን የኢኮኖሚ አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ወደ 5 ነጥብ 5 የሚወርድ መሆኑን አስታወቀ።
የገንዘብ ድርጅቱ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያም ሆነ አፈፃጸም ከመንግስት ጋር የሚለያይ ሲሆን የኢትዮጵያን መንግስት የባለሁለት አሀዝ እድገትን ባለአንድ አሀዝ እድገት መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል። እ.ኤ.አ በ2011/12 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሁለት አሀዝ እድገትን የሚያስመዘግብ መሆኑን በገለፀበት ወቅት የገንዘብ ድርጅቱ በበኩሉ እድገቱ ሰባት በመቶ እንደሚሆን በትንበያው ያስቀመጠበት ሁኔታ ነበር።

የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለፈው የካቲት ወር በለቀቀው መረጃ የኢኮኖሚ እድገቱን ቀመር ለመስራት ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን ብሄራዊ የአካውንቲግ ሲስተም በተሻሻለ የሂሳብ ስሌት እንዲቀየር መደረጉን በመግለፅ ብሔራዊውን የኢኮኖሚ እድገት መጠን ወደ 8 ነጥብ 5 በመቶ ያወረደበት ሁኔታ ነበር። በዚህም ወቅት የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የ6 ነጥብ 5 በመቶ እድገትና የኢትዮጵያ መንግስት የእድገት ቀመር ቢቀራረብም ሰሞኑን የወጣው የገንዘብ ድርጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ደግሞ የቀጣዩን ዓመት እድገት ወደ 5 ነጥብ 5 በመቶ አውርዶታል። የኢትዮጵያ መንግስት ለተከታታይ ዓመታት የባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ሲያስመዘገብ መቆየቱን ሲገልፅ የቆየ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነዳጅ አምራች ካልሆኑ ሀገራት መካከል ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው ተብሎ ሲጠቀስ ቆይቷል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የሜይ 22 ዕትም

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar