lørdag 25. mai 2013
ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ ከመዝገብ ቤት ሰራተኛነት እስከ ሚንስትሮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊነት
ወለላዬ (ከስዊድን)
ዛሬ ብቻ ኖረው- በዛሬ ያልቀሩ
ነገንም አስበው- ለነገ የሠሩ
ለራሳቸው ሳይሆን- ለህዝብ የኖሩ
ግዴታ ሆነና ሞት- ቢሆን ዕጣቸው
ሲበራ ይኖራል- አይጠፋም ሐቃቸው
ግጥም
አስራት ዳምጠው
ስድስተኛ ዓመቴ መጨረሻ ግድም አንድ ቀይ እንግዳ እቤታችን መጣ። ከናትና አባቴ ጋር ሆኜ
ከሰውየው ጋር የመቀመጥ እድል አገኘሁ። ቀዩ ሰውዬ ሳቂታ ፊት፣ የሚቁለጨለጩ አይኖች፣ ሰልካካ
አፍንጫና፣ የሞሉ ጉንጮች አሉት።ያም ሆኖ ሙሉ ፌቱ ስትታይ አነስተኛ ነች።
ይህን ሰው ከዛን በፊት ስለማወቄ እርግጠኛ አይደለሁም።እንኳን እሱን ሌሎች አብረውኝ ያሉትንም ዝምድናቸውን ለይቼ ለመናገር እቸገራለሁ።
ያን ቀን ያንን ሰው አይነ ህሊናዬን ምን እንዳበራው አላውቅም ቀረብኩት። አንድ አይነት የሚአስተሳስረን ነገር እንዳለን ገባኝ። ነፍስ ማወቅ ይሄ
ይሆን? ይሄ ካልሆነ ሌላ ምንም ሊሆን አይችል?።
ከዛ በፊት ያለውን ምኑንም የማላውቅበት እድሜዬ በኔ ላይ መቆጠሩ ይቆጨኛል። እንዴ! ምኔን እስከምናምኔ ጠራርገው ያኖሩኝ እያሉ እንዴት
አድርጎ ነው ያ እድሜ በኔ ላይ የሚቆጠር? ለሚሰጡት ይስጡ እንጂ ያ የእድሜ ዓመት የኔ አይደለም።
እንደውም ያኔ የሚሉት ልጅ እኔ መሆኔን እጠራጠራለሁ። ”ሀይለኛ ነበርክ” ይሉኛል ። ”እናቴን ስንት ልጅ ወለዱ”? ሲሏት እንደቀኑ ያበጣበጤ
ሁኔታ አንድ እራሴን አራትም አምስትም የምታደርገኝ ጊዜ ነበር አሉ። ታዲያ አሁን እንዲህ የበረድኩ ዝምተኛና ኮሽ የማይልብኝ ስው እንዴት
እድርጌ ያን ልጅ ልሆን እችላለሁ? እንጃ!
አንድ ቀን ከዛ ቀይ ሰው ጋር አብሬ ቁጭ ብያለሁ። አሁን በደንብ አውቄዋለሁ። ለነገሩ ማን ልብ ይበልልኝ እንጂ ፎቶው እቤታችን በትልቁ
ተለጥፎ ከርሟል።
አሁን እያዋራኝ ነው። የተለመደች ንግግራችን ቀጥለናል። ዜማ ባላት አባባል ”ጋሽዬ.. ጋሽዬ...”በማለት ጀመረ
”አቤት አቤት”
”የት ይኖራል?”
”ጌታ ቤት”
”ምን ይበላል?”
”ፍትፍት”
”ምን ይጠጣል?”
”ወተት”
”የት ይተኛል?”
”ግርጌ”
”ምን ይለበሳል?”
በ”ቡትቶ”
”እህህ...”
”ይነቀኝ...”
ይቺ የዘወትር ንግግራችን ናት። እናቴ ነበረች ያስለመደችኝ። ከዚህ በኋላ ጥያቂዬ አያቋርጥም። ሆፕ አድርገኝም አለ ... በቀላሉ መላቀቅ የለም።
ሲወጣ ሱሪውን ጨምድጄ እሪ ነው። በስንት ኡኡታ ነበር የሚሄደው። ያውም ቸራልያ ብስኩት ከሰዓት ከረሜላ ጋር ሊአመጣ ቃል ገብቶ
በዚህ አይነት ሁኔታ ተለማምደን እንደቆየን እንዴት እንደሆን ባላወኩት ምክንያት ከቤተሰባችን ጋር ከአዲስ አበባ ለቀን ወጣን ። ከዛ ቀይ
እንግዳም ለረጅም ጊዜ ተለያይተን ከረምን::
በሚቅጥለው ጠቅልለን ወደ አዲስ አበባ ስንመለስ ትልቅ ልጅ ሆኛለሁ ማለት ይቻላል። ከአምስተኛ ወደ ስድስተኛ ክፍል ያለፍኩባትን
የምስክር ወረቀት ይዜ ነበር። አንድ ቀን ከምጫወትበት ወደቤት ተጠርቼ ስመጣ አ.አ 27894 የሚል ታርጋ የለጠፈች ሰማያዊ ማርቸዲስ
እቤታችን ግቢ ቆማ አየሁ።እንግዳውን ለማየት አልቸኮልኩም። መኪናዋን ወደድኳት፣ ዞርኳት፣ ነካኋት፣ ያላደረኳት ነገር የለም። የሳምኳት ሁሉ
ይመስለኛል።
እናቴ ስትጣራ ሰማሁና እሮጨ ወደቤት ገባሁ። ቀዩ ስውዬ እግሩን አጣምሮ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ተመለለትኩ። ጥቁር ሙሉ ሱፍ ለብሷል::
ሹል ጫማው እንደመስታዋት ያበራል። እናቴ ልጅ አበራ እያለች ደጋግማ ስታነሳው ሰምቻለሁ። ትልቁን ሰውዬ ለምን ልጅ አበራ እንደምትለው
ይገርመኝ ነበር።
ሳሎኑ በራፍ ላይ ትንሽ ቆም ብዬ ካደፈጥኩ በሗላ ወደ ውስጥ ዘለኩ።ጋሽ አበራ በፈገግታ ተቀብሎ እየሳመኝ ስለማደጌ ይናገር ጀመር።”እንዴ!
እንዴ!... ጎረመሰ አይደል እንዴ? ካየሁት ብዙ ቆየሁ ማለት ነው? በጣም አድጓል...”
”አዎን! ይሄውልህ ቁመቱ ተመዞ ተመዞ የት ሊደርስ እንደሆን እንጃ። ሸንበቆ መስሎልሃል። በዚህ ላይ እህል ያባቱ ገዳይ ነው:: በአጥንቱ ነው
የሚወዛወዝ። እንደው ምን እንደሚሻለኝ አላውቅም...” እናቴ የዘውትር ምሬቷን ጀመረች።
”ትምህርትህንስ ስንተኛ ክፍል ደረስክ?” ጋሼ አበራ ሲናገርም ሲጠይቅም በፈገግታ ነው። ትናንሽ ፍንጭት ጥርሶቹ ነጫጭና የሚአምሩ ናቸው።
ዝም አልኩ፣ እኔ ስለመኪናዋ ነበር የማስበው፣ ሲወጣ ውስጥ ገብቼ ለመቀመጥ ቸኩያለሁ።
”አትናገርም እንዴ? ምን ይዘጋሃል?” እናቴ ተቆጣች።
”ከአምስተኛ ወደ ስድስተኛ አልፌአለሁ”።
”ጎሽ! በርትተህ የለም እንዴ!”
ሮጨ ሄጄ ሰርተፍኬቴን አምጥቼ ሰጠሁት። እያገላበጠ ካየ በኋላ ደረጃው ”ጥሩ ነው። ደህና ውጤትም ነው ያመጣው። ለመሆኑ የት ትምህርት
ቤት ነው የሚጀምረው?” አያይዞ ጠየቀ
”እንግዲህ አንዱጋ ወሽቅልኝ። ወደዚህ ወደታች ስቢስቴ የሚሉት ትምህርት ቤት አለ ሲሉ ስምቻለሁ። ወደዛ ወደገብርኤልም መውረጃም አንድ
ትምህርት ቤት አለ ይባላል። ወደ ጨርቆስም አንድ ጥሩ ትምህርት ቤት ተከፍቷል አሉ። ሲአስተምሩ ደህና ናቸውም ይላሉ”።
”የለም እዚሁ እቅርቡ አይሻለውም?” ጋሼ አበራ ስቢስቴን መረጠ።ለዳሪክተሩ የሚሰጥ አንድ ወረቀት ላይ ጻፍ ጻፍ አድርጎ ለናቴ ሰጣት።
በላብ በወረዛ እጄ ጨብጨ ለዳሪክተሩ የሰጠኋት ወረቀት ያን ያህል ክብደት እንዳላት አልተረዳሁም ነበር።ፊታቸውን እንዳኮሳተሩ የተቀበሉኝን
ወረቀት ሊአነቡ የቆዩት ዳሪክተር አንገታቸውን ቀና ያደረጉት የመገረምና የመደናገጥ ስሜት አዝለው ነበር። ቀጥ ብለው ቆመው ሲያዩኝ ከቆዩ
በኋላ ”ስንተኛ ክፍል ነህ?” ብለው ጠየቁኝ።
”ወደ ስድስተኛ አልፌአለሁ”።
”ሰርተፍኬት ይዘሃል?” ደብተሬን እስካገላብጥ አልጠበቁም። እጄን ይዘው በቀይ ሸክላ ወደተሰራ ህንጻ አመሩ። ኮሪደር ዘልቀው ገብተው 6ኛ
ክፍሎችን በሙሉ አዳረሱ። ሁሉም ሞልተዋል። ቦታ የለም ብለው ሊመልሱኝ አልደፈሩም ።አንዱን አስተማሪ ጠርተው ”አንተ ክፍል ይማር”።
ብለው ትዛዝ ሰጡ።
አስተማሪው ቅሬታውን መደበቅ አልቻለም።ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ
ከመዝገብ ቤት ሰራተኛነት እስከ ሚንስትሮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊነት

አስተማሪው ቅሬታውን መደበቅ አልቻለም።
http://www.ethiomedia.com/abc_text/abera_jembere.pdf
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar